• ምእራፍ አንድ የቪጋን መፍትሄ አለምን ለመታደግ> ፕላኔታዊ አስቸኳይ ሁኔታ
      • I.  ፕላኔታዊ አስቸኳይ ሁኔታ


        ጊዜው አጣዳፊ ነው።



        ”ሰኣቱ ዘግይቷል የውሳኔው ጊዜ አሁን ነው፣

        ትክክለኛና የበሰለ ምርጫ እንደምታስተላልፉ እተማመናለሁ፣ አለማቀፋዊ የሙቀት መጨመር ጉዳይን በሚመለከት የሳይንስ ሊቃውንት ግልጽ መልእክት አስተላልፈዋል።”1

        —ባን ኪ-ሙን

         

        ”ፕላኔታዊ አጣዳፊ የሆነ የአየር ንብረት ቀውስ ተደቅኖብናል።”

        —አል ጎር


        ከፍተኛ የናሳ አካባቢ/አየር ንብረት ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ጀምስ ሀንሰን እንደተናገሩት “አሳሳቢ ሁኔታዎችን አሳልፈናል፤ ነገሮችን መልሰን ማስተካከል የማንችልበትን ሁኔታዎችን ግን አላለፍንም። ነገሮችን ወደ ቀድሞዉ ሁኔታዎቻቸዉ መመለስ እንችላለን ነገር ግን ይህን ለማድረግ አፋጣኝ የሆነ የአካሄድ ለዉጥ ማድረግ ይገባናል።”

        የአለም ሳይንቲስቶች ስጋት ነገሮችን መልሰን ማስተካከል ከማንችልበት ነጥብ ካለፍን የሚከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ደረጃ ፈጣን ብቻ ሳይሆን አውዳሚና ሊስተካከል የማይችል በመሆኑ ነው። ይህ አደገኛ ጊዜ እየገሰገሰ በመምጣት ላይ ለመሆኑ በሰላም በመሬት ስር ተጋግሮና ተከማችቶ የሚገኘው የሚቴን ጋዝ የመፍለቅለቅ ምልክቶች ከሀይቆችና ከሌሎች አካባቢዎች እየታዩ ናቸው

        ይህ ግዙፍና ሊገታ የማይችል ጋዝ መቼ እንደሚያመልጥና ድንገተኛ ግለት ጭሮ መመለሻ የሌለው የሙቀት መጨመር እንደሚያስከትል ማንም ሊያውቅ አይችልም። ይህ ግን ለኛ በጣም አጥፊ ነው።

        ሌሎች የአየር ንብረት አውዳሚ ውጤቶች አስቀድመውም እየታዩ ናቸው። ሙቀት አንጸባራቂ የሆነው የአርክቲክ በረዶ በፍጥነት እየቀለጠ ሄዶ ሊሟጠጥ የቀረው አንድ የበጋ ወቅት ብቻ ነው፣ ይህም የባህር ከፍታን በጨመር በርካታ የደሴት አገሮችን እያሰመጠ ነው፣ በካርቦንዳዮክሳይድ ብዛት የውቅያኖሰ አካባቢዎች ህይወት አልባ እየሆኑ ናቸው፣ ገዳይ የደን ቃጠሎዎች ተበራክተዋል፣ የዱር ዝርያዎች የመጥፋት እድላቸው ከወትሮው 100 ጊዜ በላይ ደርሷል፣ የተጠናከረ አውዳሚ የባህር ላይ ውሽንፍር እየተስፋፋ ነው፣ በሽታ አምጪ የወባ ትንኞች እየሞቁ በሚሄዱ አካባቢዎች እየተስፋፉ ናቸው፣ በረዶዎች ቀልጠው እየጠፉ ናቸው፣ የሚደርቁና የሚጠፉ ሀይቆችና ወንዞች በአስር ሺዎች ተበራክተዋል፣ በረሃነትም እየተስፋፋ ነው

        በዚህ የአካባቢያ ተጽእኖ ሳቢያ ከሁለት ቢሊዮን ሰዎች በላይ የውሃ እጥረት ገጥሟቸዋል፣ ከሃያ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ወድቀዋል — በግልጽ ያልታወቀና ጥበቃ የሌለው ስደተኛ

        በእውነት እነዚህ አሉታዊ ተጽእኖዎች የሰው ልጆች የሁከት ድርጊት ውጤቶች ናቸው  የዚህ አንድ ቁጥር ጎጂ ደርጊት ስጋ መብላት ነው።

         [በተጨማሪም፣] የእንሰሳት እንዱስትሪ ለአብዛኛው የአፈር መሸርሸር መንስኤ ነው። እንዱስትሪው ግንባር ቀደም የበረሃነት አስፋፊ፣ የብዝሃ-ህይወት አውዳሚ፣ በአየር ንብረት ሰበብ የውሃ እጥረቱ የጎላ ሆኖ ሳለ ይህ እንዱስትሪ ዋንኛ የውሃ አባካኝና በካይነቱ እንደቀጠለ ነው። ከዚህም በላይ የእንሰሳት ዘርፉ የዘይት ሃይልንና የምግብ እህልን አሟጣጭ ነው። በአጭሩ፣ ከ12 ጊዜ በላይ እህልን፣ ከ10ጊዜ በላይ ውሃንና፣ ከ8 ጊዜ በላይ የዘይት ሃይልን ስጋን ለማምረት እናጠፋለን ከተመሳሳይ ወይም ከበለጠ የቪጋን ምግብ ጋር ሲነጻጸር

         

        እንሰሳት፣ ዋነኛ የአለማቀፍ ቀውስ መንስኤ



        ያንዣበበብንን የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ “መልሰን ማስተካከል የማንችልበትን ነጥብ የማስቀሪያ መንገድ በወሳኙ አደገኛ የአየር ንብረት መንስኤ ላይ እርምጃ መውሰድ ይግባናል – በስጋ ማምረቱ ላይ። ያለን ማስረጃ/መረጃ ይህንን በርግጠኝነት እንድንናገር የሚያስችለን ነው። የእንሰሳት እንዱስትሪ ቁጭር 1 የአለም ሙቀት ጨማሪ ጋዞች ምንጭ ነው

        በቅርቡ የታተሙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግኝቶች 2006 የሚነግሩን የእንሰሳት እንዱስትሪ የአለም ሙቀት ጨማሪ ጋዞች አመንጪነቱ ከጠቅላላው የአለም ትራንስፖረት ዘርፍ ድምር—አይሮፒላን፣ ባቡሮች፣ መኪናዎች፣ ሞተርሳይክሎች፣ ወዘተ የበለጠ ነው2 በቅርቡ የተስተካከሉትና የታረሙት ቀመሮች የሚነግሩን የእንሰሳት እንዱስትሪ ቢያንስ ለ50% የአለም ሙቀት መጨመር ምክንኒያት ነው3



        “ትንታኔኣችን የሚያሳየን እንሰሳትና ተዋጽኦዋቸው ቢያንስ በአመት 32,564-ሚሊዮን ቶን
        ካርቦንዳዮክሳይድን
        ወይም 51% አመታዊ አለማቀፍ የአለም ሙቀት ጨማሪ ጋዞች አመንጪ መሆናቸውን ነው4
        የወርልድ ወች ተቋም

          

         

        ሚቴን ካርቦንዳዮክሳይድ የበለጠ ሃይለኛ ነው



        እንሰሳት መሰረታዊ የሰውሰራሽ ሚቴን አመንጪ ናቸው፣ በሙቀት መያዝ ችሎታው ሚቴን የካርቦንዳዮክሳድን 72 ጊዜ በላይ ሃይል ያለው ብቻ አይደለም፣ እድሜውም አጭር ነው። ይህ ማለት ሚቴን ከባቢ አየርን ከካርቦንዳዮክሳይድ ይልቅ ቶሎ ይለቃል፣ በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ ይችላል፣ ካርቦንዳዮክሳይድ በአንጻሩ ለሺህ አመታት በከባቢ አየር ውስጥ የሚቆይ ነው። ስለዚህ እንሰሳት ማርባትን በመተው ሚቴንን ማጥፋት ፈጣኑ ፕላኔታችንን የማቀዝቀዝ መንገድ ነው።

        አዎን፣ አውራውን አመንጪ መጋፈጥ አለብን።

        አዋቂ የአለም መሪዎች ሁሉ ይህንን አጥፊ የስጋ ልምድ ዋነኛና ወደ መልሰን ማስተካከል ከማንችልበት ነጥብ” አሳልፎ የሚሰደንን ሃይል እንዲገቱ ዘወትር እጸልያለሁ። አለበለዚያ ካርቦንን ለመቀነስ የሚደረጉ ሌሎች ጥረቶች ሁሉ ኢኮኖሚያችንን ከማጥፋታቸውም በላይ እንዲያውም የመተግበር እድሉም ፈጽሞ ላይኖረን ይችላል።

        ስጋ መብላትና ማምረትን እንዲሁም ሌሎች የእንሰሳት ምርቶችን ካላቆምን አለምን ማጥፋታችን ነው

         

         

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *