• ምእራፍ ሁለት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች > ይህ ከባሱት የባሰ የወደፊት ሁኔታ ነው
      • I.  ይህ ከባሱት የባሰ የወደፊት ሁኔታ ነው

        የወቅቱ የአየር ንብረት ለውጥ አካሄድ የተመዱ የአየር ንብረት ለውጥ በይነ መንግስታት ፓነል (IPCC) ከተነበየው ሁኔታ የባሰ ነው ይህም በተለያዩ አጥፊና አደገኛ ጫናዎች እንደ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የሙቀት ወላፈንና ማእበል(ሁሪኬን) በልክ እየተከሰተ ይገኛል።

        አለማችን የአየር ንብረት ለውጥ አመንጪ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ብንችል እንኳን፣ አሁን ከባቢ አየር ውስጥ በሚገኙ ጋዞች ምክኒያት ፕላኔቷ ለማገገም ብዙ ጊዜ ይወስድባታል።

        ይህ ትኩረታች ለምን አጭር እድሜ ላላቸው ጋዞች ማለትም ሚቴን ላይ ማድረግ እንደሚገባን ያስገነዝበናል። በአማካይ በሃያ አመታት ጊዜ ውስጥ፣ ሚቴን የካርቦንዳዮክሳይድን 72 ጊዜ የበለጠ ሙቀትን ይስባል፣ ይይዛል። ሚቴን ዋንኛ ትልቁ ምንጭ የእንሰሳት ኢንዱስትሪ ነው፣ እንደሚታወቀው ሚቴን ከዋንኞቹ የአለም ሙቀት መጨመር ምክኒያቶች አንዱ በመሆኑ ማስቆም ያለብን ጋዝ ነው።

        በመጀመሪያ ግን፣ በቅርቡ የወጡ ጥቂት የአየር ንብረት ለውጥ በሰው ልጆችና በእንሰሳት ላይ ያስከተለውን የተጽእኖና ጫና ማስረጃዎችን እንዳካፍላቸሁ ይፈቀድልኝ።



        የአርክቲክና አንታርክቲካ በረዶ መቅለጥ


        ‘የምላሽ ጥልፍልፎሽ’ እና የአለም ሙቀት መጨመር ከቁጥጥር ውጪ መሆን

        የባህር ውሃ እየሞቀ ቢሄድ በረዶው በፍጥነት ይቀልጣል። በረዶው ከቀለጠ ደግሞ ሙቀቱን አንጸባርቆ ወደ ህዋ የሚመልስ አይኖርም። ስለዚህ ሙቀቱ በረዶውን ያቀልጠዋል ውሃውንም የበለጠ ያሞቀዋል ማለት ነው። ሁለቱም እርስ በርስ በመደጋገፍ በረዶውን ያቀልጡታል እናም ፕላኔቷንም የበለጠ ያሞቋታል። የሰይጣን አዙሪቱ ይታይሃል?

        ለዚህ ነው ሳይንቲስቶች እስዛሬ ድረስ በትክክል ሊተነቢዩ ያልቻሉት፣ አሁን ግን በጣም ንቁ ናቸው። አይናቸውን በጉዳዩ ላይ ተክለዋል። የሚያሳስበው ጉዳይ ነገሩን በተፈለገው ፍጥነት እያከናወን አለመሆኑ ነው። 18


        የአርክቲክ መቅለጥ 

         

         ምንጭ፡ ብሄራዊ የበረዶ መረጃ ማእከል፣http://nsidc.org/arcticseaicenews/index.html


        የግሪንላንድና አንታርክቲካ በረዶ መቅለጥ

        እንዲሁም ግዙፎቹ ግሪንላንድና የአንታርክቲካ የበረዶ ንጣፎች መቅለጥ ከቀጠሉ አጥፊ የባህር ከፍታ መጨመርና ጠነካራ ማእበል ማስከተላቸው አይቀሬ ነው። መላው የምእራባዊው አንታርክቲካ ቋጥኝ ከቀለጠ የባህር ከፍታው ቢንያስ በአማካይ ከ3.3፣ 3.5 ሜትር (10.8 – 11.8 ጫማ) 19 ከፍ በማለት ከ3.2ቢሊዮን ሰዎች በላይ ሊጎዳ ይችላል - ይህ እስከ 200 ማይሎች ረቀት የባህር ዳርቻ ዙሪያ ውስጥ የሚኖር፣ ግማሽ የአለም ህዝብ ያህል መሆኑ ነው።

        የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ከብሄራዊ የበረዶ መረጃ እንደሚሉት ከሆነ መላው የአንታርክቲካ በረዶ ከቀለጠ የባሀር ከፍታው ከተገመተው በላይ ከፍ ሊል ይችላል። እንዳንዶች 70 ሜትር (230 ጫማ) ሊደርስ አንደሚችል ይናገራሉ። ይህ ደግሞ ለመላው አለም አስጊ ነው። 20

         

        የምድር መስመጥና የአየር ንብረት ስደተኞች

        በባህር ከፍታ መጨመር ምክኒያት፣ ደሴቶች በአሁኗ ደቂቃ በመስመጥ ላይ ይገኛሉ፣ ቱቫሉ፣ ቶንጋና ሌሎች 40 ያህል የደሴት አገሮች ለስደቱ እቅድ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

         

        እንደ የአለማቀ የስደተኞች ድርጅት International Organization for Migration ዘገባ እስከ 200-ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች፣ እንዲያውም እስከ 1 ቢሊዮን ሊደርስ ይችላል ቁጥሩ፣ አስከ 2050 ወይም በህይወት ዘመናችን በአየር ንብረት ምክኒያት ይሰደዳሉ21 እነዚ በባህር ከፍታ መጨመር ወይም በግግር መሬት (ፐርማፍሮስት)
        መቅለጥ ምክኒያት
        ደሴት አገሮቻቸውን ወይንም የባህር ዳርቻ መኖሪያዎቻቸውን ሰለሚወድምባቸው ለስደት 
        (የሚዳረጉ ሰዎች
        ናቸው።  22  (እባክዎ እዝል 1ን ለበለጠ መረጃ ይመልከቱ፤)


        የባህር ከፍታ መጨመር ትንበያ




                                                                        ምስጋና፡ 4ኛ የአይፒሲሲ የዳሰሳ ሪፖርት፣ 111፣ ምስል 1

         

        የሚቴን ሃይድሬት፡ የተቀበረ ፈንጂ ነው

        ሌላው የአርክቲክ ለውጥ የፐርማፍሮስት፣ በወትሮው በሚቴን የተሞላና የተጋገረ መሬት (ሚቴን ሃይድሬት) መቅለጥ ነው። በቅርብ አመታት የዚህ ክፍል መቅለጥ ለሚቴን መለቀቅ ምክኒያት ሲሆን መጠኑ በአየር ውስጥ ከ2004 ጀምሮ ከፍ እንዲል አድርጓል። 23

        በተጨማሪ የአለም ሙቀት መጨመር ከሁለት- ዲግሪ ሴልሸየስ በላይ መጨመር በቢሊዮኖች ቶን የሚገመት ተጨማሪ ሚቴን [ከውቅያኖስ ወለል የሚመነጭ ሃይድሬት] ወደ ከባቢ አየር እንዲለቀቅ ያደርግና በፕላኔቷ ላይ የጅምላ እልቂት ያስከትላል።

                   “የጥቂት ዲግሪዎች ሙቀት መጨመር ብቻ እነዚህን ጋዞች እንዲፈሉና ወደ ከባቢ አየር 
                   ገብተው ሙቀቱ የበለጠ ጨምሮ፣ ይህም በተራው ተጨማሪ ሚቴን ይለቅና ምድርንና ባህርን 
                    ያሞቃል፣ ወዘተ። በአርክቲክ ውስጥ 400 ጊጋ ቶን በላይ ሚቴን ተከማችቶ የሚገኝ 
                    ሲሆን ይህም ተከታታይ ውህደቶችን ይፈጥራል። አንዴ ከተጀመረ ኡደቱ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ 
                    የአለም ሙቀት ሊያስከትል ይችላል።” 24
                                                                                       
         -- ጆን አቺሰን፣ የከርሰ-ምድር ባለሙያ


        የውሃ (የባህር) ከፍታ መጨመር ብቻ አይደለም የሚያሳስበን፣ ጋዙ ነው፣ ሃድሮጂን ሰልፋይዱ፣ ሚቴኑ፣ ሁሉም በውቅያኖስ ውስጥ የሚገኙ ጋዞች። 25 እናም ከተጋገረ መሬት ውስጥ፣ ከባህር ውስጥ፣ ከእንሰሳትም የሚወጣው ሚቴን ተጨማሪ በረዶ ያቀልጣል። ይህ ሁሉ ተደማምሮ በከባቢ አየር ውስጥ ተከማችቶ ለረጂም ጊዜ ሊቆይ ይችላል።

         

         ከማይመለስበት ነጥብ ላይ ሲደርስ ከከፍታ ቦታ ላይ እንደሚንከባለል ነገር፣ ምንም ለውጥ ማምጣት አይቻልም።  የዘገየን እንሆናለን። በዚያን ጊዜ ምንም ነገር  ሊደረግ አይችልም። ማንም ላይተርፍ ይችላል፣ ምናልባት በጣም ጥቂት።አንዴ ፕላኔቷ ከጠፋች እንደ ማርስ ምንም የማይኖርባት ትሆናለች። በሚሊዮን የሚቆጠሩ አመታት፣ እንዲያውም መቶ ሚሊዮን አመታት ሊፈጅ ይችላል ፕላኔቷ እንደገና ለማገገም የሚያስፈልጋት ጊዜ፣ ያውም ማገገም ከቻለች ነው።

        ፈጥነን ከተለወጥን የተሻለ ነው፣ የአየር ንብረት ለውጡን በመግታት። ፕላኔቷን ፈጥነን በአጭር ጊዜ ውስጥ ልንፈውስ  እንችላለን፣ ይህን ካላደረግን ግን ፕላኔቷ በአጭር ጊዜ ውስጥ ልትጠፋ ትችላለች።


        የበረዶ ሽፋን መመናመንና የውሃ እጥረት


        የበረዶ ሸፋን መመናመን ተጽእኖ

        አብዛኛው የፕላኔቷ የበረዶ ሽፋን በጥቂት አመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል፣ የሁለት ቢሊዮን ሰዎችን የመኖር እድል ጥያቄ ውስጥ ከቶ። ከነዚህ አንድ ቢሊዮኑ የሂመለያ የበረዶ ሽፋን መመናመን ሰለባ ናቸው ፣ ከማንኛውም የአለም አካባቢ የበለጠ በከፍተኛ ፍጥነት እየነጎደ ያለ፣ የአካባቢው የበረዶ ሽፋን ከሶስት-አራተኛ የሚበልጠው 18,000ዎቹ እየሸሹ ናቸው። 26

        የበረዶ ሽፋኑ መቅለጥ የመጀመሪያው ውጤቶች አጥፊ ጎርፍና የመሬት መናድ ናቸው። የበረዶ ሽፋኑ እየተመናመነ ሲሄድ ዝናቡ ይቀንሳል፣ አውዳሚ ድርቅና አስከፊ የውሃ እጥረት ይከተላል። 27

         

        አሳሳቢ የአለም የበረዶ ሽፋኖች ሁኔታ

        በሞንታና ክልል [ዩኤስኤ], ዝነኛው የግላሽየር ብሄራዊ ፓርክ በረዶ ሽፋን በሚቀጥሉት አስር አመታት ውስጥ ይጠፋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። 28 የኮሎራዶ ወንዝ  [በበረዶ ላይ የሚመሰረተው] የሰባት ምእራባዊ ከተሞች የውሃ ምንጭ የሆነው ሊደርቅ ነው። 29

        ፔሩ የአገሪቱ የውሃና የሃይድሮኤሌከትሪክ ሃይል መጋቢ የውሃ ምንጭ የሆነ የመላው የአንድሪያን አካባቢ በረዶ 70% ባለቤት ናት። እነዚህ ሁሉ በጥቂት አመታት ውስጥ እስከ 2015 ይጠፋሉ ተብሎ እየተሰጋ ነው። 30 እየቀነሰ የሄደው የውሃ አቅርቦት ውጥረቶችን እያባባሰ ይገኛል፣ እንዲያውም ብዙ የተገፉ ገበሬዎችን ጨምሮ ሰዎች በቂ ውሃ ስለማያገኙ ወይም የድርሻቸውን ለማግኘት ሲታገሉ ግጭቶች እየፈነዱ ናቸው።

        (ለተጨማሪ መረጃ አለማቀፋዊ የበረዶ መመናመንን በተመለከተ እባክዎ እዝል 2ን ይመልከቱ)


        አሟጦ አሳ-ማስገር፣ የወደሙ ቀጠናዎችና የውቅያኖስ አሲዳማነት


        የዩኤሱ ፒው ኮሚሽን  እንደደረሰበት አሟጦ አሳን ማስገር፣ የእርሻ ፍሳሾችን አስከትሎ ይህም የእንሰሳት ቆሻሻንና ለእንሰሳት ምግብ ማዘጋጃ የሚውል ማዳበሪያን ጨምሮ፣ ለባህር ውስጥ ስነ-ምህዳር አስጊ ነው።31

        የአየር ንብረት ለውጥ የሞቱ/የወደሙ የባህር ቀጠናዎች የሚባሉትን የባህር ክፍል እየፈጠረ ይገኛል፤ ይህ ቁጥር አሁን 400 ደርሷል። እነዚህ [የሞቱ ቀጠናዎች] የተፈጠሩት በአብዛኛው በእንሰሳት ምክኒያት በማዳበሪያ ፍሳሾች ሲሆን ባህሩን ለህይወት አስፈላጊ የሆነውን ኦክሲጂን አልባ ስለሚያደርጉ ነው።32

        ሳይንቲስቶች እንደገመቱት ባለፉት 50 አመታት ከ90% በላይ የሚሆኑት ትልልቅ የአሳ ዝሪያዎች ከባህር የጠፉት በነጋዴ አሳ-አስጋሪዎች ምክኒያት ነው።33አሳ መስገሩ አሁን እንደተያዘው ከቀጠለ፣ ሁሉም የአሳ ዝሪያዎች እስከ 2050 ከአለም ተሟጠው ሊያልቁ እንደሚችሉ በማስጠንቀቅ፣ መልሶ የማቋቋሙ ስራ በአስቸኳይ መጀመር እንዳለበት ይመክራሉ።34






        የተወሰኑ የአሳ ዝሪያዎች በማለቃቸው የውቅያኖስ አሲዳማነት ከፍ እንዲል አስተዋጽ በማድረጉ፣ ይህም በተራው የውቅያኖሱን ካርቦን ዳዮክሳይድ ጋዝ የመምጠጥ አቅም ይቀንሰዋል።

        በዚህ ምክኒያት ሁኔታዎች እየተባባሱ አሳ-ነባሪዎችና ዶልፊኖች ከውቅያኖስ እየሸሹ ይገኛሉ፣ ያፍናቸዋላ። እንዳንዴም ሀኔታውን/መርዙን መቋቋም ተስኗቸው  በመቶዎች የሚቆጠሩቱ በአንድ አፍታ ሞተው በባህር ዳርቻ ይገኛሉ።35


        አደገኛ የአየር ሁኔታዎች


        ባለፈው አስርተ አመታት ውስጥ በታሪክ ውስጥ ያልተመዘገቡ ቢያንስ ሁለት ጊዜ፣ አመታዊ አማካይ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ በፕላኔቷ አስተናግዳለች። በ2003 በሪኮርድ የተመዘገበ ሃይለኛ ሙቀት አውሮፓን መታት፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ህይወትንም አጥፍቷል። የሙቀት ወላፈን በአውስትራሊያ ተነስቶ በታሪኳ ውስጥ ያልታየ የዱር እሳትን ለኮሰ። 36

        የፔብላ ክልል [ሜክሲኮ ውስጥ] ባለፈው ጥቂት አመታት ውስጥ እየጨመረ የመጣ የደን እሳትን ለማስተናገድ ተገዷል፣ 200ሊትር/ካሬ ሜትር የሚሆን የዝናብ መጠን ቀንሷል፤ የሙቀቱ መጠን ግን በአማካይ በ17.5 ዲግሪ ሴልስየስ ጨምሯል። አሁን የክረምቱ የሙቀት መጠን ከተለምዶው ጨምሯል።

        ባለፉት ስድት አመታት፣ ፔሩ ቢያንስ ሶስት የተለየና ጫፍ የደረሰ የሙቀት መጠንና ጎርፍ አጋጥሟት ከ500,000 ሰዎች በላይ ተጎድተውባታል። በሰላሳ አመታት ውስጥ ብቻ፣ ጎርፍ ከ60% በላይ ሲያድግ ጭቃ የቀላቀለ ጎርፍ ደግሞ  400% ጨምሯል።37 በ2009 ፕሬዝዳነት [የፔሩ] ጋርስያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥተው ነበር፣ በደቡባዊ የአንደስ አካባቢ ከባድ ብርድና ቅዝቃዜ  ወደ 250 የሚጠጉ ህጻናትን የገደለ ሲሆን፣ በርካታ ሌሎች ሰዎችን ደግሞ ለህመም የዳረገ ነበር።38

        (ለአለማቀፋዊው የወቅቱ የአየር ሁኔታ መረጃ እባክዎን እዝል 3ን ይመልከቱ)

        የአየር ንብረት ትርጉሙ አማካይ የሙቀት መጠንና ዝናብ ብቻ ማለት ሳይሆን
        የአየር ሁኔታ አይነት፣ ድግግሞሽና ብርታቱንም ያጠቃልላል። ሰው-ሰራሽ የአየር
        ንብረት ለውጥ እንደ የሙቀትና የቅዝቃዜ ወላፈንን፣ ሃይለኛ ማእበልን፣ ጎርፍና
        ድርቅን የመሳሰሉ አስከፊነትና ስርጭት የመለወጥ ሃይል አለው።
        39

                                                                                                                                 --የዩኤስኤ የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት 

        የተፈጥሮ አደጋዎች ድግግሞሽ ጨምሯል


        ድርቅ፣ በረሃማነትና የዱር ቃጠሎ

        እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በኣብዛኛው ዛፎችን በመጨፍጨፍና በእንሰሳት ግጦሽ ምክኒያት በሚከሰት ጥፋት የሚመጣው በረሃማነት፣ ከ1.2 ቢሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎችን ደህንነት ከ100 በላይ በሆኑ አገሮች ችግር ውስጥ ከቷል።40

        የውሃ አቅርቦትም እየደረቀ ነው፤ በታላላቅ ከተሞች ማለትም በቤጂንግ፣ በዴሊህ፣ በባንግኮክና በሌሎች በደርዘን በሚቆጠሩ አካባቢዎች እንደነ መካከለኛ ምእራብ ዩኤስኤ የመሳሰሉ የከርሰ-ምድር የውሃ ምንጮች እየደረቁ ናቸው፣ እንዲሁም የጋንጀስ፣ የዮርዳኖስ፣ የአባይና የያንግትዝ ወንዞች (በአመት ውስጥ ለብዙ ወራት) እያሽቆለቆሉ ወደ ጠብታነት እየተለወጡ ናቸው።

        በቻይና በአምስት አስርተ አመታት ጊዜ ውስጥ ተከስቶ የማያውቅ ከባድ ድርቅ (2009) ደርሶ ቢያንስ በአስራ ሁለት ክፍለ- ግዛቶች ሰብል አውድሞ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ በአገሪቱ ላይ አድርሷል፣ የተጎዱ ገበሬዎችን በመርዳት አኳያ።41

        በ2009 በኔፓልና በአውስትራሊያ የዱር እሳት ተነስቶ በድርቅ ተባብሶ ብዙ ጉዳት አስከትሏል።42

        በአፍሪካም የሶማሊያ የኢትዮጵያና የሱዳን ህዝቦች፣ ጥቂቱን ብቻ ለመጥራት ያክል፣ ድርቅ አሽመድምዷቸዋል።

        ተመራማሪዎች እንደሚሉት በተራሮች ላይ የሚገኘው በረዶ እየቀለጠ ከፍተኛ ውሃ በመልቀቅ ላይ ስለሆነ ምእራባዊ ዩኤስኤ አውዳሚ የድርቅ ቀውስ አርግዞ ይገኛል።

        (ለአለማቀፋዊው የወቅቱ የድርቅና የዱር እሳት አደጋ መረጃ እባክዎን እዝል 4ን ይመልከቱ።)


        የውሽንፍና ጎርፍ ድግግሞሽ መበራከት

        ባለፉት ሰላሳ አመታት ውስጥ የባህር ማእበል/ሁሪኬንና ውሽንፍር በመጠንና በጊዜ አኳያ ሲታይ በ100% እያደጉ እንደመጡ ተስተውሏል። በዩናይትድ ስቴትስ እንደሚገኘው የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም (MIT) ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ይህ ከአየር ንብረት ጋር የተቆራኘ የውቅያኖስ ሙቀት መጨመር ምክኒያት የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። እንደ የጆርጂያው ቴክኖሎጂ ተቋም፣ ዩኤስኤ ተመራማሪዎች፣ በጣም አደገኛ የሆኑት የደረጃ 4 ና 5 ሁሪኬን ማእበሎች ባለፉት 35 አመታት ውስጥ በመላው አለም በእጥፍ አድገዋል። የደረጃ 5 ሁሪኬን ማእበልና ውሽኝፍ በትላልቅ ከተሞች ላይ ከፍተኛ ውድመትን ያስከትላሉ። በመጠንና በጊዜ አኳያም ከ1970ዎቹ አመታት ጀምሮ በ75% ጨምረዋል።

        ከነዚህ ማእበሎች አንዱ የሆነው የ2005 ሁሪኬን ካትሪና ኒው ኦርሊንስን ያወደመ ሲሆን፤ ቁስሉ እስካሁንም አልሻረም።

        የዩኤስኤ ብሄራዊ የውቅያኖስና የከባቢ አየር አስተዳደር እንደሚለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበ በ2008 በተከታታይ ስድስት የሀሩር ሳይክሎን ተነስቶ በዩኤስኤ ምድር ላይ የመሬት ናዳ አስከትሏል።

        ሰሜናዊው የአትላንቲከ ውቅያኖስና የህንድ ውቅያኖስ ጠንካራ ሁሪኬን የሚታይባቸው ሁለት አካባቢዎች ናቸው።

        (ለአለማቀፋዊው የወቅቱ የጎርፍ አደጋ መረጃን በተመለከተ እባክዎን እዝል 5ን ይመልከቱ)




         

        የመሬት መንቀጥቀጥ/ርእደ-መሬት

        ርእደ-መሬት ከአለም ሙቀት መጨመር ጋር የተያያዘ መሆኑን፣ ምክኒያቱም ከዋልታዎችና ግሪንላንድ ስር የሚገኘው በረዶ እየቀለጠ በመሬት ላይ ያለውን ጫና ይቀይርና የውስጥ እንቅስቃሴ ፈጥሮ ርእደ-መሬት እንደሚቀሰቅስ የሳይንስ-ሊቃውንት ደርሰውበታል።

        የዘመናችን አሳዛኝ አደጋዎች አንዱ የሆነው ሱናሚ [በርእደ-መሬት ምክኒያት] በ2004 እንዶኔዥያን በመምታት የእንዶኔዥያና የአለምን ህዝብ ጥልቅ ሀዘን ላይ ጥሎ አልፏል።

        (ለአለማቀፋዊው የወቅቱ የርእደ-መሬት አደጋ መረጃን በተመለከተ እባክዎን እዝል 6ን ይመልከቱ)


        የነፍሳት ወረራ

        በዩኤስ አሜሪካ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሄክታር ደን መሬት በሮኪ ተራራዎች አካባቢ በአየር ሙቀት መጨመር ምክኒያት በጢንዚዛ ወረራ ጠፍቷል። ካናዳም በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠቅታለች።


        ደን ጭፍጨፋ



        የዝናብ ደን የፕላኔታችን ሳንባ ነው። ዛፎች ሲቆረጡ እጽዋት
        ይጋለጡና ይደርቃሉ፣ ካርቦንዳዮክሳይድን ከመውሰድ ይልቅ ወደ
        ከባቢ አየር ይለቃሉ። ይህ ሌላኛው የተጋረጠብን አደጋ ነው።


        በብራዚል ከ1970 ጀምሮ 90% የሚሆነው የተመነጠረ መሬት ለእንሰሳት ግጦሽ ወይም መኖ ውሏል።43  ውቡ ደን በደቂቃ 36 የእግር ኳስ ሜዳዎች በሚገመት ፍጥነት ወደ ምድረ-በዳነት እየተለወጠ በአሁኗ ወቅት በመውደም ላይ ይገኛል።44

        በደቡባዊው የሜክሲኮ ክፍልም የሀሩር ጥቅጥቅ የዝናብ ደኖች ከግማሽ የማያንስ የታባስኮ ግዛት ሸፍኖ የነበረው አሁን ወደ ከ10% በታች ዝቅ ብሏል። በአንጻሩ የእንሰሳት ግጦሽ መሬት ወደ 60% ከፍ ብሎ የግዛቷ መሬት ይዞ ይገኛል።45

        እንዲሁም እንደ አርጀንቲናና ፓራጓይ በመሳሰሉ አገሮች ለእንሰሳትና ለአኩሪ አተር እርሻ ደኖችት በብዛት እየተቆረጡ ይገኛሉ። አርጀንቲና ከነበራት ደን ከ70% በላይ አጥታለች።46

        እንዶኔዥያ ከብራዚልና ከኮንጎ ቀጥላ ከአለም በሶስተኛ ደረጃ የትልቅ የዝናብ ደን ባለቤት ናት። ሆኖም ደኗ በሚያስደነግጥ ፍጥነት (አንድ የእግር ኳስ ሜዳ/በደቂቃ) እየጠፋ ይገኛል። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት 98% የሚሆነው የዝናብ ደኗ በሚቀጥሉት 15 አመታት ሊጠፋ ይችላል።47

        የአማዞን የዝናብ ደን ብቻውን በአስር አመት ጊዜ ውስጥ የሰው ልጅ የሚለቀውን የአየር ሙቀት ጨማሪ ጋዞች ያህል ካርቦንዳዮክሳይድ ጋዝን ሊወስድ/ሊመጥ ይችላል። በተጨማሪም ጫካዎቹን ስናቃጥል 680 እጥፍ የካርቦንዳዮክሳይድን ሙቀት የማመቅ አቅም ያለውን ጥቁር ካርቦንን (ጥላ-ሼት) ወደ አየር እንለቃለን።48


        የብዛ-ህይወት መመናመን


        በዘመኑ ተወዳዳሪ በሌለው ሁኔታ የዱር እንሰሳት በመመናመን ላይ መሆናቸውን እውቅ የስነ-ምህዳር ባለሙያዎች ይናገራሉ። እንደ ሳይንቲስቶቹ ግምት 16000 ያህል ለአደጋ የተጋለጡ የምድራችን ዝርያዎች ፊት ከታሰበው መቶ እጥፍ የመጥፋት እድላቸው ፈጥኖ ይገኛል።


        እውቁ የሃርቫርዱ ባዮሎጅስት ኤድዋርድ ዊልሰን እና ሌሎች ሳይንቲስቶች እንደገመቱት
        እውነተኛው የዘር መጥፋት ፊት ከተገመተው 1,000 እስከ 10,000 እጥፍ ይደርሳል።
        2.7 እና 270 መካከል የሚገመቱ ዝርያዎች በየቀኑ ከምድረ-ገጽ ላይ ይጠፋሉ።49
                                                                       
        ጁሊያ ዊቲ

                      ሌላውን ችግር ታሳቢ ሳናደርግ፣ በአየር ሙቀት መጨመር ምክኒያት ብቻ በምድር ላይ ካሉት
                    
         20% - 40% የሚገመቱ ዝርያዎች በያዝነው ምእተ-አመት ሊጠፉ ይችላሉ።50

                                                                                                      —የተመድ በይነ-መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ መማክርት/ፓነል


        የውሃ እጥረት



        እየቀነሰ የመጣው የውሃ አቅርቦት ውጥረትን እያባባሰ፣ እንዲያውም የችግሩ ሰለባ የሆኑትን ገበሬዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በቂ ውሃ ባለማግኘታቸው ወይም ለድርሻቸው ስለሚታገሉ ግጭትን እየወለደ ነው።

        በአለም ላይ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወንዞችና ሀይቆች በመድረቅ ላይ ናቸው። በድርቅ ምክኒያት ሰዎቾ በማለቅ ላይ ናቸው። ምንም የሚጠጣ ውሃ ባለማግኘታቸው ሰዎች መኖሪያ ቄያቸውን እየለቀቁ ናቸው።51

        እንድ ቢሊዮን ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የላቸውም። እናም በተበከለ ውሃ ምክኒያት 1.8 ሚሊዮን ህጻናት በየአመቱ ይሞታሉ።52



        የምግብ እጥረት


        2009 ጀምሮ በአራት አስርተ አመታት ውስጥ ያልታየ ከፍተኛ የረሃብተኛ ቁጥር አለም እያስተናገደች መሆኑን ተመድ አስታውቋል። በአለም በቂ ምግብ የሌላቸው የሰዎች ቁጥር ወደ 1.02 ቢሊዮን ይደርሳል።53

        በፔሩ ባለፉት 12 አመታት ከመጠን በላይ በሆነ ሙቀትና ድርቅ ምክኒያት 140,000 ሄክታር የሚሆን ድንችና በቆሎ ሲበለሽ - ይህ 11ሚሊዮን ሰዎችን ሊመግብ የሚችል ነው።

        በአፍሪካ ዝንባቡዌ፣ ሶማሌ፣ ሞሪሽየስ፣ ሞዛምቢክና ሱዳን - ጥቂቶቹን ብቻ ለመጥቀስ ያህል - የምግብ እህልን ለማምረት የሚያስቸግርና ለተባባሰ ድርቅ በመዳረግ ለተጨማሪ የምግብ እጥረትና የዋጋ መናር ተዳርገዋል። 

        ከዚህም በተጨማሪ በረሃማነትና የደን መራቆት መሬቱን እያበላሸ ይገኛል። የሙቀት መጨመር ማለት የዝናብ በመጠንና ጊዜ ተስተጓጎለ ማለት ሲሆን- ይህም ያነሰ ወይም የበዛ ይሆናል ማለት ነው - ሰብልን የሚውጥ አደገኛ ጎርፍና ደንን የሚያወድም እሳት ያስከትላል።

        እነዚህ የአየር ለውጥ ተጽእኖዎች የምግብ እጥረትንና ቀውስን ያባብሳሉ።

        (የወቅቱ የአየር ንብረት ለውጥና የአለም ምግብ እጥረት መረጃን በተመለከተ እባክዎን እዝል 7ን ይመልከቱ።)

         

        የሰው ጤንነት


         በአየር ንብረት ለውጥ የሚሰቃዩ ሰዎች

        በሲዊስ በተካሄደው ጥናት መሰረት ከሆነ የአየር ንብረት ለውጥ በአመት ለ315,000 ሰዎች ሞት ምክኒያት ሆኗል።54 በተጨማሪም 325 ሚሊዮን ሰዎች በጽኑ ተጎድተዋል። ይህም በአመት 125 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የኢኮኖሚ ጉዳትን ሳይጨምር ነው።55 የባሰ የተጎዱት ታዳጊ የአፍሪካ አገሮች ሲሆኑ የደቡብ እሲያና ትናንሽ የደሴት አገሮችም  ሌሎች የችግሩ ሰለባዎች ናቸው።

        በተጨማሪም በተፈጥሮ አደጋዎች ህይወቱን ያጣው 99% የሚሆነው የእሲያ ህዝብ ነው።


        በነፍሳት የሚሰራጩ በሽታዎች

        የደንጉ  ትኩሳት የሚያመጡ የወባ ትንኞች ድሮ ወደ ማይታዩበት የፒዩራ [ፔሩ]፣ ከፍተኛ ቦታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ እየታዩ ናቸው፣ ይህም በአየር ንብርት ለውጡ ምክኒያት ነው።56

        ወባን የመሳሰሉ በሽታዎች ስጋት እየጨመረ መጥቷል፣ ምክኒያቱም በሽታውን የሚያመጡ ትንኞች ወደ ከፍተኛ ቦታዎች በመሰራጨታቸው። የተመድ ስጋት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአፍሪካ ህዝቦች ለችግር መጋለጥ ነው።57

        (ስድስት ዲግሪ፦ የእኛ የወደፊት ህይወት በሞቃት ፕላኔት በማርክ ላይነስ [Six Degrees: Our Future on a Hotter Planet by Mark Lynus] ከተሰኘ መጽሃፍ ላይ ለተወሰዱ ጥንቅሮች እዝል 8ን ይመልከቱ።)



         

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *