II. ጊዜ የለንም
የሳይንስና ፊዚካላዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ብዙ ጊዜ የለንም። ነገም ፕላኔቷን ለመታደግ ብንፈልግ እንኳን ሊሳካልን አይችልም።
በአለም የአየር ሙቀት መጨመር የተደቀነብን አደጋ አይቀሬ ነው፣ በአለም አካባቢ በሚስተዋለው ሁኔታ፣ በብዙ አደጋዎች እንደሚንጸባረቀው፣ ከመሬት ውስጥ በሚገነፍለው ነገር፣ በአየር ንብረት ስደት ስጋቱ እዚህ ከፊታችን ላይ ፈጦ ይታያል።
እውቅ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የከባቢ አየር ሙቀት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ስለሄደ ለለውጥ ብዙ ጊዜ የለንም።
“ቀዩን መስመር አያለፍን ነው። መልሰን ማስተካከል ከማንችልበት ነጥብ ግን አላለፍንም። ነገሮችን አሁንም ማስተካከል እንችላለን፣ ይህ ግን ፈጣን የአቅጣጫ ለውጥ እንድናደርግ ያስገድደናል።58
ዶ/ር ጄምስ ሃንሰን፣ የናሳ ጎዳርድ የጠፈር ጥናት ተቋም ሃላፊ
ብዙ የአለም መሪዎችና ሳይንቲስቶችም ስጋታቸው ጨምሯል። እውነቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱትንና እየተባባሱ የሄዱትን የአለም ሙቀት መጨመር ሁኔታዎችን መቆጣጠር አለመቻላችን ነው።
አንዳንድ አገሮችና ማህበረሰቦች የተባባሰ የድርቅ ሁኔታዎችን ማስተናገድ ግድ ሆኖባቸዋል። ምግባቸውን ለማምረት እንዲያውም ለመጠጥም በቂ ውሃ የላቸውም። ወንዞቻቸውና ሀይቆቻቸው ደርቀውባቸዋል ወይም እስከናካቴው ጠፍተዋል። በብዙ ቦታዎች በረዶዎች በሚገርም አኳኋን እየቀለጡ ስለሆነ ኣንድ ጊዜ ከፍተኛ ጎርፍ፣ ወዲያው ደግሞ ድርቅ ይከሰታል።
እግዲያውስ እንዴት አድርገን ነው፣ በበረሃማነት መስፋፋትና በባህር ከፍታ መጨመር ወይም በሰብል/እህል መውደም ምክኒያት በአንድ ጊዜ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ስደተኞችን መቆጣጠር የምንችለው? በጣም አስቸጋር ነው፣ እንዲያውም አይቻልም ይሆናል።
ምንም አልተዘጋጀንም። በቂ ዝግጅት አላደረግንም።
መጀመሪያ መትረፍ/በህይወት ለመቆየት፣ ይህቺን ፕላኔት ማትረፍ አለብን። ምክኒያቱም በረዶው ከቀለጠ፣ ዋልታዎቹ ከቀለጡ እናም ባህሩ እየሞቀ ከሄደ፣ ጋዙ ከውቅያኖስ አምልጦ ሊመርዘን ይችላል። ከፍተኛ ጋዝ ነው ያለው።
የሲንጋፖሩን ገለጻየን ((ሌክቸር)[መስከረም 1994 እ.ኤ.ኣ.]) ብትመለከቱት አስቀድሞውኑ የአናኗር ዘይቤያችንን መለወጥ እንዳለብን አስጠንቅቄ እንደነበር ትረዳላችሁ፣ አለበለዚያ በጣም እንዘገያለን። ይህ ከ10 እስከ 15 ኣመታት [በፊት] ነው። እንዲያውም ከዚያ ሊያልፍ ይችላል። እኔ ሁሌም የምናገረው እንዴት ደናችንን እንደምንጨፈጭፍ፣ ስለ ስጋ መብላትና እነዚህ ሁሉ ምን ያህል ምድራችንን እንደሚጎዱ ነው።
ሳይንቲስቶች ብዙ ነግረውናል። አሁን ያዳምጣሉ፣ እኔ ግን የምለው ፈጠን እንዲሉ ነው። ነገሩ ተግባርን ይጠይቃል። የሁሉም አለም መንግስታት መሪዎች አሁን ነገሩን ከምር የወሰዱት ይመስላል። ስጋቴ ዘገምተኛነታቸው ነው፣ ይኸው ነው። የጸሃይን ብርሃን በማንጸባረቅ ወደ ሰማይ የሚመልሰው በረዶ በፍጥነት እየቀለጠ የማንጸባረቅ ተግባሩን ቀንሷል፣ ባህሩም ሙቀቱን ጨምሯል፣ ይህም በረዶውን የበለጠ ያቀልጠዋል። በረዶው በመቅለጡም ባህሩ የበለጠ እየሞቀ ይሄዳል። እኔ የምለውን ታያላችሁ አይደለም? አዙሪቱን ትገነዘባላችሁን?
አሁን በተያያዝነው ሁኔታ ችግሩን መቅረፍ የምንችል አይመስልም፣ እናም በአራትና አምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ያልቅልናል። ሌላ የለም። ይህን ያህል አጣዳፊ ነው።