• ምእራፍ ሁለት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች > የችግሩን ስረ መሰረት ኣሁኑኑ ፍቱ
      • III.  የችግሩን ስረ መሰረት ኣሁኑኑ ፍቱ


        ለአካባቢያችን ቀውስ ትልቁን አስተዋጽኦ እያደረገ ያለውን ኣስቁሙ



        ለዛሬው የአካባቢያችን አስጊ ችግሮች ከዋና ዋናዎቹ መንስኤዎች አንዱ እንሰሳትን ማርባት ነው። አስቸኳይ ተግባራዊ መድህን ያስፈልጋል። 59
        / ሄኒንግ  ስቴንፊልድ፣ የእንሰሳት መረጃና ፖሊሲ ጉዳይ ቅርንጫፍ ሃላፊ፣ የተመድ የምግብና እርሻ ድርጂት (ፋኦ)

         

        ለደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ሃይል እንሰሳት ናቸው። ትልቁና ዋነኛው ውሃ በካይ እንሰሳት ናቸው። እንሰሳት ከጠቅላላው የትራንስፖርት ዘርፍ የበለጠ የአየር ሙቀት አምጪ ጋዞችን ያመነጫሉ።

        የከብት እርባታ ረጅም ጥላ (ላይቭሰቶክስ ሎንግ ሻዶ)

         

        ለሁሉም የፕላኔታችን ሙቀት መጨመር ችግር ካርቦን ዳዮክሳይድን መውቀስን ማቆም አለብን። ራሳችንን ነው መውቀስ ያለብን። የስጋ እንዱስትሪ ነው መወቀስ ያለበት። የስጋ እንዱስትሪን ትኩረት ሰጥተን ማቆም፣ ማስወገድ ያለብን። መናገር አለብን - የስጋ እንዱስትሪ መቆም/መወገድ አለበት።

        የአለም ሙቀት መጨመር እንዳይባባስ ቀልጣፋው ዘዴ ቪጋን መሆን ነው። ቀላል ይመስላል ነገር ግን ከሁሉም የተሻለና እውን ሊሆን የሚችል ውጤቱም ወዲያው የሚታይ ነው። ከዚህ ዋናና በጊዜ ሊተገበር ከሚችል አማራጭ ውጪ ሌላ ማንኛውንም ነገር ብንሞክር በቂ ሆኖ ያከማቸነውን መጥፎ አጸፋዊ ውጤት ሊመልስ አይችልም።

        በተጨማሪም አሁን ያጋጠሙንን ችግሮች - እንደ ከባቢ አየር ሙቀት መጨመር፣ የውሃ እጥረት፣ የምግብ እጥረት እና የበረሃማነት መስፋፋት - ስጋን በማቆም ልናስወግዳቸው እንችላለን። አሁኑኑ እናቁም፣ በቃ አይቀጥልም!


        ስጋ አትብላ/አትብዪ። ቀደም ሲል አይፒሲሲ ይህን መናገር ፈርቶ ነበር፣ አሁን ግን መናገር ተችሏል፦ እባክዎን ስጋ መመገብን ይቀንሱ - ስጋ ካርቦን ተመጋቢ ምርት ነው።
        60

        / ራጄንድራ . ፓቾሪ

         


        የችግሩ መሰረት መለኮታዊ/መንፈሳዊ ነው


                                
        ለሰው ልጅ ጤናማነትና በአለም ላይ የመኖር እድሉንም የሚያሰፋ
        ከቬጄታሪያን አመጋገብ የበለጠ ምንም ነገር የለም።

        አልበርት አንስታየን


        ቀደም ብዬ እንደነገርኳችሁ ችግሩን ከመሰረቱ መዋጋት አለብን። የችግሩ መሰረት የአለም ሙቀት መጨመር መንስኤ ነው፣ እናም ይህ መንስኤ በሌሎች ፍጥረታት ላይ (እንስሳትን ጨምሮ) ያደረስነው ክፋት ነው።

        ማንኛውም ድርጊት የመልስ ምት ይጋብዛል፣ ይህም በሳይንስ የተረጋገጠ ነው።

        አየህ፣ የአፕል ዘር ብንዘራ የአፕል ተክል እናገኛለን፣ ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ ከተክሉም የአፕል ፍሬዎችን እናገኛለን። ይህ የህይወት ኡደት ነው። በመግደል ህይወትን መጠበቅ የለብንም። ማንኛውም ድርጊት ተመሳሳይ የአጸፋ ምልሽ ማፍራቱ አይቀሬ ነው። ይህ ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሳይንሳዊ አነጋገር ነው።

        ስለዚህ አሁን የችግራችን መሰረት አብረን በአለም ላይ አብረን ከምንኖር ሌሎች ፍጥረታት ማለትም ህይወት ያላቸው፣ ስሜታቸውን በሚገልጹ፣ በሚንቀሳቀሱ፣ አፍቃሪ በሆኑ እንደ እንስሳትን በመሳሰሉት የተለያየ መጠንና ቅርጽ ባላቸው ፍጡራን ላይ የምናደርሰው በደል ነው። እንዲሁም በአካባቢያችን ላይም ክፋት አድርሰናል። በመሆኑም ከኛ ጋር የሚኖሩ እንሰሳትን ገድለናል/ጨፍጭፈናል፣ አካባቢያችንን አጥፍተናል - ደኖቻችንን ጨፍጭፈናል፣ ውሃዎቻችንና አየራችንን አጥፍተናል/በክለናል። ከዚህ ሁሉ፣ የተሻለ ነገር መጠበቅ አንችልም።

        እነዚህ አሳዛኝ ለቅሶዎች ምስቅቅልና በጉስቁልና በቆሸሹ በተጣበቡና በጨለማ ጎረኖዎች ታጉረው የጸሃይ ብርሃን የማያገኙና የሚሰቃዩ እንሰሳት ከመገደላቸውም ሆነ ከተገደሉ በኋላ የሚደርስባቸው የተባበሰ ስቃይ ሰማይና ምድርን ያንቀጠቀጠ ነው።

        ስለዚህም የተፈጥሮ አደጋዎች፡ ድርቅና የመሳሰሉት የሰው ልጅ የሚያደርሰውንና የሚፈጽመውን ሰይጣናዊ/መጥፎ ድርጊትማስጠንቀቂያዎች ናቸው፣ እንዲሁም ወደ ተሻለና ብሩህ፣ ደስታና ስቃይ-አልባ ህይወት (ለእንሰሳትም ጭምር) ለውጥ ለማድረግ የሚበጁ ምክሮች ናቸው።

        የዘራኸውን ታጭዳለህ፣የትኛውም ቅዱስ የተባለ መጽሃፍ የሚያስተምረው ይህንኑ እንድንተገብር ነው። ስለዚህም የሰው ልጅ መንቃት አለበት፣ አለበለዚያ አጸፋውን ለማስተናገድ መዘጋጀት አለብን።

        ስለዚህ አሁን የገጠመንን ችግር ለመቅረፍ ድርጊታችንን መቀልበስ አለብን። አብረውን በአለም ላይ ለሚኖሩት ፍጥረታት ሁሉ ደግ መሆን አለብን። እነሱን ከመግደል፣ ከመጨፍጨፍ፣ ከመሰዋት፣ ልንከባከባቸው ልንጠብቃቸው ይገባል። ደንን ከመጨፍጨፍ ዛፎችን መልሰን መትከል ይገባናል። አካባቢያችንን ልንጠብቅ ይገባል። ፕላኔታችንን፣ አየሩን ከመበከል ወደ ዘላቂና ምቹ ሃይል አጠቃቀም መዞር አለብን። ድርጊቶቻችንን መቀልበስ ብቻ ነው ሚጠበቅብን።

        ከተፈጠሮ/ዩኒቨርሳል ሃይል ከተፈጥሯዊ የፍቅር ህግ ጋር መተባበር/መዋሃድ አለብን። የሰው ልጅ የሌሎችን ህይወት ካላከበረ የራሱም ህይወት ችግር ላይ ይወድቃል፣ ምክኒያቱም ሁላችንም የተሳሰርን ስለሆን።

        ያንዱ ህይወት በሌላው ላይ የተመሰረተ ነው፣ ይህ አፈሩን ወደ ለምነት እስከሚቀይሩልን፣ ጥቃቅኖቹ ትላትሎች ይደርሳል። ነገር ግን ሰዎች ከመግደል ፊታቸውን ቢያዞሩ፣ ከእንሰሳት ነጻ የሆነ የህይወት መንገድን ቢመርጡ፣ የደግነትና የሰላም ፍሬን ያፍሳሉ።

        በርካቶች ይህንን እንዲተገብሩ ጸሎታችን ው፣ ጊዜ ስለሌለን ግን በፈጠነ እርምጃ።

        ወደ ኣፍቃሪነታችን ተመልሰን ፕላኔቷን እንታደግ


        የተፈጠሮ አደጋዎች በከባቢያችን አየር ውስጥ ያለው የአፍራሽ/አሉታዊ ሃይል ውጤት መሆኑን መረዳት አለብን። እናም ይህፍራሽሃይልም በሰዎችና በንጹሃን እንሰሳት ላይ በምናደርሰው የጥላቻ፣ የአመጽና የግድያ ሀሳብ፣ ስሜትና ድርጊት የተፈጠረ ነው። የአደጋ ምንጩንና ትንኮሳውን ካላደረቅንና ካላቆምን አደጋው መጨረሻ የለውም። 

        አስተሳሰባችንንና የህይወት መንገዳችንን ወደ ከፍተኛና የበለጠ ርህራሄ እንዲሁም መልካምነት መለወጥ አለብን። ብርቅዬና ቆንጆ የሆነችውን ፕላኔታችንን ለመታደግ አሁኑኑ የቪጋን አመጋገብን በመጀመር ወደ እውነተኛውና ፍቅር የተሞላበት የሁሉንም ህይወት ወደ ማነቅመንከባከብ መመለስ ይጠበቅብናል። ቪጋን/ቬጄቴሪያን ፈጣኑና ከሁሉም የተሻለ መፍትሄ ነው።

        ቪጋን መሆን ለማንኛውም መንፈሳዊ እድገት ጠቃሚ ነው። በርግጥ ሁሉም በሳልና ጥንታዊ መምህራን የሚያስተምሩት የመልካሙን እጽዋት-አቀፍ አመጋገብ ጠቃሚነት በማያሻማ መልኩ አስቀምጠዋል። ይህ መሰረታዊ የመንፈሳዊ ህይወት መመዘኛ ነው።

        ከእንሰሳት ተዋጽኦ ነጻነት በስተጀርባ ያለው ጽንሰ-ሀሳብ ሰላማዊነት - አመጽ-አልባነት ነው። በቪጋን አመጋገብ መጥፎውን የመግደል ካርማ እናስወግዳለን ይህም በመንፈሳዊ ጉዟችን ላይ ሸክሙን ያቀልልናል፣ እንቅፋቱን ያስወግድልናል።

        ቪጋን መሆን ማለት እንሰሳትን መንከባከብ መጠበቅ ማለት ነው። የሰው ልጅ በስልጣኔ ለመቀጠል የሌሎቸን ህይወት ማጥፋት ማቆም አለበት። የዚህ ጠቀሜታው ዘርፈ-ብዙ ነው። ጤናችንን ከመጠበቅና ከመመለስ በተጨማሪ ብዝሃ-ህይወትን እንዲቀጥል፣ የፕላኔቷ ሚዛናዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ፣ እንዲሁም የህሊና ነጻነትና ንቃት እንዲዳብርና ከፍ እንዲል ይረዳናል።

        ይህ ሁሉ የርህራሄያችን ፍሬ ነው። ይህ በፍቅር የተሞላ አካሄድ የአካባበያችን ሰላም ፈጥሮ ለሁሉም ፍጡራን ምቾትን ያስገኛል። ከራሳችን ጋር ሰላም በመፍጠር፣ በወንድሞቻችንና በአብሮ-ኗሪ እንሰሳት ላይ እንግልትና ስቃይ ባለማድረስ የምናገኘው ውስጣዊ ሰላም በልበ-ሙሉነት መንፈሳዊ እድገታችንን እንድናጎለብት ያግዘናል።

         ሰፋ ባለ መልኩም ከፍ ባለ ደረጃ ፕላኔታችንም ትፈወሳለች፣ ልክ እያንዳንዱ የሩህሩህነት አመጋገብን በመከተል እንደሚፈወስ ሁሉ - ተመሳሳዮች ይሳሳባሉ። መልካሙ፣ ፍቅርና ርህራሄ የተሞላበት ሃይል ካንዣበበብን አደጋ ያድነናል፣ ጨለማውንም ይገፋል።

        ባጭሩ በምድር ላይ ገነት ፈጠርን ማለት ነው።

        የፕላኔቷን ሚዛን ያዛባሉ፣

        በትጋት

        እባክህ ንቃ/እባክሽ ንቂ!          በታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ

         

        ምድር ሆይ ንቂ ተጠንቀቂ

        የተመሰቃቀሉ ወንዞችና ተራሮች

        የተቃጠሉ ደኖች የተሸረሸሩ ኮረብታዎች የደረቁ ጅረቶች

        ምስኪኖቹ ነፍሶች በመጨረሻ የት ነው ሚገቡት?

         

        ታላቋ ምድር ሆይ ስቃይሽ ይቅለልልሽ

        እንባሽ ይድረቅ በሌሊቱ ጽናት

        ባህሮችና ሃይቆች ሆይ ዝማሬዎቻችሁን አታቋርጡ

        የነገውን ሰው ተስፋ በማለምለም...

         

        ፍጡራን ሆይ ለወዲያኛው አለም ዝግጅት ይኑራችሁ

        ምንም ቃላት ሳትተነፍሱ ያለፋችሁ ቢሆንም።

        የልቤ ድለቃ ረጋ እንዲል

        የምድር ኗሪዎች በጊዜ ንስሃ መግባትን በጉጉት እየተጠባበቅሁ።

         

        ጥልቅ ደኖች ሆይ እውነተኛው ማንነታችሁን ጠብቁ

        በስህተታቸው ወቅት የሰው ልጆችን ታደጉ።

        እባካችሁ ልባዊ ሺህ የእንባ ጠብታዎቼን ተቀበሉኝ

        ግርማ ሞገስ የተላበሱ  ዛፎች፣ ቅጠሎች እና ስሮቻችሁን ለመንከባከብ።

         

         

        ልብ ሆይ መንሰቅሰቁን አቁሚ

        በረጅሙ ሌሊት ነፍሴ እረፍት እንድታገኝ።

        እንባዬም ደረቀ ቃላትም አጠሩኝ

        በሀዘን ተጨብጬ ስቃዩ ለበዛባቸው ሳለቅስ!

         

        ምሽት ሆይ እባክሽ የብርሃን ምንጭሽን ፈንጥቂ

        በጨለማ ውስጥ ላሉት ሰብኣዊ ነፍሶች የብርሃን መንገዱን አሳያቸው

        አእምሮዬ እንዲረጋጋ ጸጥታና ሰላም ሁን

        እናም ወደ ምንምነት ግባ በተኣምረኛው ሰማያዊ ዝማሬ።

         

        ቀን ሆይ ድንገተኛ መቁነጥነጥን አትቀስቅሺ

        ሰላም በሁሉም ልቦች ውስጥ እንዲነግስ/እንዲያርፍ

        የሰው ልጆች ትግል እንዲከስም

        እውነተኛው ማንነት በታላቅ ሞገስ ይንጸባረቅ ዘንድ!

         

        ልቤ ሆይ ከንግዲህ አትተክዢ

         በክረምት ቁር እንደሚጥመልመሉ ነፍሳት።

        እንከን የለሹ ነገን በእርጋታ ጠብቂ

        እንዲሁም አለም ወደ ገነትነት የምትለወጥበትን ቀን።

         

        አለቅሳለሁ፣ እማጸናለሁ፣ እጸልያለሁ፣ እለምናለሁ!

        እስከ የማትባሉት ቡድሃዎች ሆይ፣

        ቦዲሳትቫዎች፣ መላእክት

        መጨረሻ በሌለው አዙሪት ውስጥ ግራ ተጋብተው የሚሰቃዩ ስደተኞችን

        ትክክለኛውን መንገድ ስተው የሚባዝኑትን ነፍሶች ኣድኗቸው።

         

        ወንድም ሆይ ንቃ!

        በታላለቆቹ ወንዞችና ባህሮች ላይ በኩራት ተራመድ

        የምትንቦገቦገውን ጸሃይ በቀጥታ ተመልከት

        እናም ሁሉንም ፍጥረታት ለመታደግ ቃል ግባ።

         

        እህት ሆይ ንቂ በዚህቺ ቅጽበት!

        ከጥፋት ስፍራዎች ተነሺ

        በአንድነት ፕላኔታችንን እናድሳት

        ሁሉም ኣስደሳች የአንድነት ዝማሬዎችን እንዲዘምር

        ሁሉም ኣስደሳች የአንድነት ዝማሬዎችን እንዲዘምር።

         

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *