ምእራፍ ሶስት
ኦርጋኒክ ቪጋንነት የፕላኔቷ መድህን
ቪጋንነት አለማችንን ይታደጋል። እጽዋትን መሰረት ያደረገ አመጋገብ መከተል እስከ 80%
የአለም ሙቀት መጨመርን ሊገታ፣ ረሃብን ከአለም ሊያጠፋ፣ ጦርነትን ሊያስወግድ፣ ሰላምን
ሊያበረታታ ይችላል፣ እናም ውሃና ሌሎች ብርቅዬ ሃብቶቿ እፎይታን ያገኛሉ ለፕለኔቷና
ለሰው ልጅ ህይወትን በመስጠት። በአጭሩ አሁን የተጋረጡበንን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች
በፍጥነት ይገታልናል/ይቀርፍልናል።
እነዚህ ሁሉ አውዳሚ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ የሚስተዋልባቸው ብዙዎቹ አካባቢዎች እንደ የአረክቲክ መቅለጥ፣ የመሬት መስመጥ፣ ከበረዶ ሽፋን መቅለጥ የተነሳ የሚከሰት የውሃ እጥረትና እንዲያውም ባህር ውሽንፍር መጨመር ከምድር ሙቀት መጨመር ጋር በቀጥታ የተቆራኙ ነቸው። ስለሆነም ከሁሉም አስቀድሞ ፕላኔቷን ማቀዝቀዝ አለብን። የአለም ሙቀት መጨመርን ለመግታት የተሻለው መንገድ መንስኤ የሆኑት ሙቀት አማቂ ጋዞችን ማግታት ነው።
ከእንዱስትሪና ከትራንስፖረት ዘርፍ ከመሳሰሉት የጋዝ ልቀቱን ለመቀነስ በመደረግ ላይ ያሉትን ጥረቶች እናውቃለን። በነዚህ ዘርፎች የሚስተዋሉት ለውጦች ብዙ ጊዜ የሚወስዱ ናቸው - በዚህ ቀመር፣ በዚህ ሰኣት ከሚፈለገው የበለጠ ጊዜን ይጠይቃሉ። አንዱና ዋናው ፈጣንና ውጤታማው የሆነው የከባቢ አየር ሙቀትን የመቀነስ መንገድ የሚቴን ምርትን መቀነስ ነው።
ሚቴን ከካርቦን 72 እጥፍ ሙቀት-አማቂ እቻ አይደለም፣ ከካርቦን በጣም በፈጠነ በአጭር ጊዜ ከከባቢ አየር ውስጥ ሊወገድ ይችለል። ስለዚህ ከካርቦን ይልቅ ሚቴንን ማምረት ብናቆም ከባቢ አየሩን የበለጠ በፍጥነት ማቀዝቀዝ እንችላለን።
ኦርጋኒክ ቪጋንነት በርካታ ፋይዳዎች አሉት፣ ለህይወታችን አስጊ የሆኑ ሚቴንንና ሌሎች ሙቀት-አማቂ ጋዞችን በመቀነስ ፕላኔቷን የማቀዝቀዝ ውጤት ይኖረወል።
ኦርጋኒክ - ምክኒየቱም የትም የሚረጩ፣ ፈሰው ወንዙን አፈሩንና ህይወት ያላቸውን ነገሮች የሚበክሉና የሚመርዙ ሰውንም ለተለያዩ ህመሞች የሚዳርጉ ጎጂ ኬሚካሎችን አንፈልግመም።
በተጨማሪም ኦርጋኒክ - ምክኒያቱም ይህ ተግባር በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኘውን ግዙፉን የካርቦንዳዮክሳይድ መጠን በመምጠጥ ፕላኔታችንን ያቀዘቅዝልናል።