• ምእራፍ ሶስት. ኦርጋኒክ ቪጋንነት የፕላኔቷ መድህን > I. ፕላኔቷን አቀዝቅዝና አካባቢውን እንደነበር መልስ
      • I. ፕላኔቷን አቀዝቅዝና አካባቢውን እንደነበር መልስ


        ሚቴንን ጥቁር ካርቦንና ሌሎች ሙቀት-አማቂ ጋዞችን ማስወገድ


        እንሰሳት - እጅግ ትልቁና ዋነኛ የሚቴን አምንጪ

        ትልቁ ስጋታችን ካርቦንዳዮክሳይድ አይደለም፣ ሚቴን እንጂ።
        ሚቴን የሚመጣው እንሰሳትን ከማርባት ነው።


        ትልቁን የአለም ሚቴን አምንጪ በመቀነስ መጀመር እንችላለን፣ የእንሰሳትን ማርባት ማለት ነው። ስለዚህ እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ፕላኔቷን ለማቀዝቀዝ የእንሰሳትን እርባታ እንዱስትሪን ለማስቆም ስጋ መመገብን ማቆም አለብን። በዚህ መሰረት ከእንሰሳት እንዱስትሪ የሚመነጩ ሙቀት-አማቂ ጋዞችን - ሚቴንና ሌሎች መርዛማ ጋዞችን መግታት እንችላለን።


        ሙቀት-አማቂ ጋዞችና የአለም ሙቀት መጨመር እምቅ ሃይል

         

        ሙቀት-አማቂ ጋዞች

        CO2

        (ካርቦንዳዮክሳይድ )

        CH4

        (ሚቴን)

        N2O

        (ናይትረስ ኦክሰይድ)

        የአለም ሙቀት መጨመር እምቅ ሃይል (ጂደብሊዩፒ GWP)*

        1

        25*

        298*

        የቅድመ-እንዱስትሪ በከባቢ አየር  ውስጥ የነበረው

        280 ፒፒኤም

        0.715 ፒፒኤም

        0.270 ፒፒኤም

        በከባቢ አየር  ውስጥ በ2005 የነበረው

        379 ፒፒኤም

        1.774 ፒፒኤም

        0.319 ፒፒኤም

        የእንሰሳት ድርሻ በመቶኛ**

        9%

        37%

        65%

        * በመቶ አመታት ጊዜ ውስጥ በአማካይ ሚቴን 25 ናይትረስ ኦክሳይድ 298 ጊዜ ከካርቦንዳዮክሳይድ የበለጠ የሙቀት መጨመር ሃይል አላቸው።.  በሃያ አመታት ጊዜ ውስጥ በአማካይ ሚቴን 72ጊዜ የበለጠ ሃይል አለው። ፒፒኤም ማለት አንድ በሚሊዮን (one part in 1,000,000 parts, ppm)   (አይሲሲ IPCC, 4ኛው አመታዊ የዳሰሳ ሪፖርት, 2007, ሰንጠረዥ 2.14)

        ** (ስቴንፊልድ እና ባልደረቦቹ, የእንሰሳት ረዥሙ ጥላ/Livestock’s Long Shadow, 2006)



        በአለም ውስጥ ያለው ሁሉም ሰው ይህንን ቀላል ግን ትልቅ እቅም ያለውን ከእንሰሳት-ውጤት-ነጻ የሆነውን አመጋገብ ቢከተል የአለም ሙቀት መጨመርን በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀልበስ እንችላለን። ከዚያም ሌሎቹን የረጂም ጊዜ እንደ የአረንጒዴ ቴክኖሎጂን ያሉትን የመፍትሄ እርምጃዎችን በመውሰድ ተጨማሪ ካርቦንዳዮክሳይድከከባቢ አየር ለማስወገድ በቂ ጊዜ ይኖረናል።

        እንደ እውነቱ ከሆነ የስጋ ምርትን ማቆም ብንዘነጋ እንድም እነዚህ የአረንጒዴ ቴክኖኖጂ እንደ የንፋስ፣ የጸሃይ ሃይል ያሉትን የመተግበር ጥረቶች በሂደት ሊፋቁ ወይም እነርሱን ለመትከል እድል ከማግኘታችን አስቀድሞ ፕላኔቷን ልናጣ እንችላለን።

        የናሳ ተመራማሪዎች እንደገለጹት ትልቁ ምንጭ ሰው-ሰራሹ የእንሰሳት እርባታ የሆነው ሚቴን በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ 100 ጊዜ ከካርቦንዳዮክሳይድ የበለጠ ሙቀትን የማመቅና ምድርን የማሞቅ ሃይል አለው።

                                

                                “በሃያ አመታት ጊዜ ውስጥ ሚቴን 72 ጊዜ ከካርቦንዳዮክሳይድ የበለጠ

                                ምድርን  የማሞቅ ሃይል አለው።” 62
                                                                                                                    —አይፒሲሲ

         

                                “በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ሚቴን 100 ጊዜ ከካርቦንዳዮክሳይድ

                                የበለጠ ምድርን  የማሞቅ ሃይል አለው።”

                                “ዛሬ አንድ ቶን ሚቴን ቢለቀቅ የአንድ ቶን ካርቦንዳዮክሳይድ ዛሬ ተለቆ

                                እስከ 2075 የሚያደርሰውን የሙቀት መጨመር ያህል አቅም በአንድ

                                አመት ውስጥ ይኖረዋል።” 63

                                                  —ዶ/ር ኪርክ ስሚዝ የአለም አቀፍ የአካባቢ ጤና ፕሮፌሰር ዩኒቨርሲቲ                      
                                                   ካሊፎርኒያ በርክሌይ


        ማስተዋል ያለብን ምንም እንኳን ከዚህ በፊት የሙቀት-አማቂ ጋዞች ምንጮችን አስመልክቶ የወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱት የእንሰሳት ድርሻ
        18% ቢሆንም፣ ይህም ከጠቅላላው የትራንስፖርት ዘርፍ የበለጠ ቢሆንም ግምቱ በጣም ያነሰ እንደነበርና አሁን በተደረገው ቀመር ከ50%  እንደ ሚበልጥ ተረጋግጧል። ገመዋለሁ፡ እንሰሳት የሚለቁት ሙቀት-አማቂ ጋዞች እንደገና በተሰራው ቀመር መሰረት ከጠቅላላው የአለም ድርሻቸው ከ50%  በልጦ ተገምቷል - 50% ው ከእንሰሳት እንዱስትሪ ነው። ስለዚህ ቁጥር አንዱ መፍትሄ ነው።64  

         
        የሚቴን ውሁድና የሃይድሮጂን ሰልፋይድ አደጋ

        በሚቀዘቅዝበት ጊዜ ሚቴን ሃይድሬት በውቅያኖስ ወለል ስር ታምቆ አደጋ ሳይፈጥረ ይቀመጣል። አሁን ግን የአየር ጸባዩ እየሞቀ ሲመጣ ጋዞቹ ለማምለጥ ይጣደፋሉ። ሳይንሳዊ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ወደ ከባቢ አየር መውጣት ጀምረዋል። ፓርማፍሮስቱ/ግግሩ መሬት ክፍል በየቀኑ በመቅለጥ ላይ ይገኛል።65

        የዚህ አደገኛ ጊዜ መዳረሻ ምልክቶች እየታዩ ናቸው፣ ቀደም ሲል በመሬት አካል ስር ተጋግሮ በሰላም ተከማችቶ የነበረው የሚቴን ጋዝ አሁን ከሀይቆችና ከሌሎች አካባቢዎች እየፈላ/ bubbling ነው።66
        ይህ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ግዙፍ ጋዝ መቼ እንደሚያመልጥና በድንገት ከፍ ያለ ሙቀት በማድረግ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የአለም ሙቀት መጨመርን እንደሚያስከትል ማንም መናገር አይችልም። ያ ደግሞ እጅግ አደገኛ ነው።



                “ግግሩ መሬት እንደተቀበረ ፈንጂ ነው - ሊፈነዳ ደቂቃ የሚቆጥር - መቅለጡ እየቀጠለ በሺዎች 
                ቴራግራም ቶን የሚገመት ሚቴን ወደ ከባቢ አየር ሊያመልጥ ይችላል የአለም ሙቀትን በማባበስ።
                ይህ አሁን ግንዛቤ ያገ!ነው የሚቴን ጋዝ ምንጭ ቀደም ሲል በተሰሩት የአየር ንብረት ሞዴሎች
                አልተካተተም።” 67

                (1 ቴራግራም = 1 ሚሊዮን ቶን)
                                                                —ዶ/ር ካቲ ዋለተርስ,  በአላስካ ዩኒቨርሲቲ, የውሃ ምህዳር ባለሙያ


        በመሆኑም የሚያሳስበን ሚቴን ብቻ አይደለም። ከውቅያኖስ በርካታ ጋዞች አሉ። [ለምሳሌ] በምድራችን ታሪክ ውስጥ የሃይድሮጂን ሰልፋይድ መሰረት 90% የሚበልጠጡ ፍጥረታት ሙልጭ ብለው በመጥፋታቸው ነው። 68

        የሃይድሮጂን ሰልፋይድ እንደአወሳሰዱ መጠን ብቻውን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን አይን አፍንጫ ጉሮሮ የመተንፈሻ ቱቦ ላይ የመከርከር ስሜት ያመጣል፣ ድንገተኛና ያልተጠበቀ ውርጃን፣ የአካላችን ተግባራት የማስተጒጎል፣ ራስ ምታት፣ መደበርና መቻጫን ስሜት፣ ማስመለስ፡ ማሳል፣ የመተንፈስ ችግር፣ አይን የመጉዳት፣ ------ በድንነት፣ ሞት ወዘተ።

        ስለ አለም መቀት መጨመር ባናነሳ እንኳን ጋዙ ራሱ እኮ ሊገለን ይችላል። በአሁኑ ወቅት ብዙ የሚቴን ጋዝ ወደ ከባቢ አየር አምልጦ በርካታ ሰዎች በራስ ምታት የአእምሮ ህመም ላይ ይጥላል ወይም አካላቸውን እያሰቃየ ይገኛል እንደ ሳይንቲስቶች ምርምር እንሚያሳየው።

        የሚቴን ጋዝ ራስ ምታት ያስከትላል፣ የመተንፈሻ አካላትንና የልብ ስራ መስተጒጎልን ያስከትላል፣ መጠኑ ከበዛም በማፈን ሊገድል ይችላል። ከካርቦን ሞኖክሳይድ መርዛማነትጋር ተመሳሳይ ነው። የካርቦን ዳዮክሳይድን 23 እጥፍ ያህል አደገኛ ገዳይ ነው።

        ሌሎች ከእንሰሳት የሚመነጩ ገዳይ ጋዞች

        የእንሰሳት እንዱስትሪ ሌሎች ገዳይ መርዘኛ ጋዞችንም ይለቃል። ትልቁ የናይትረስ ኦከሳይድ ምንጭ ማለትም 65%የሚሆነውና 300 ያህል ጊዜ የካርቦንዳዮክሳይድን የሙቀት-አማቂነት ሃይል አለው። እንዲሁም 64% የሚሆለውን አሞኒያ- አሲዳማ ዝናብ የሚያስከትለውን ጋዝና ሃይድሮጂን ሰልፋይድ - ገዳይ የሆነውን ጋዝ እንሰሳት ያመነቻሉ። ስለዚህ እንሰሳትን ማርባት መተው ማለት ሚቴንን ጨምር እነዚህን ገዳይ ጋዞች ሁሉ ማስወገድ ነው።69


        የጥቁር ካርቦን አውዳሚ ውጤት

        ጥቁር ካርቦን በአለም አካባቢ የሚገኙትን የበረዶ ንጣፎችና ሽፋኖችን በፍጥነት እንዲቀልጡ የሚያደርግ 680 ጊዜ ከካርቦንዳዮክሳይድ የበለጠ ሙቀት አማቂ ብናኝ/አካል ነው። እስከ 40% የሚሆነው የጥቁር ካርቦን ብናኝ ልቅት ለእንሰሳት ግጦሽ ደኖችን በማቃጠል  የሚመጣ ነው።

        ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ለእንሰሳት እርባታ ሲባል የደቡብ አሜሪካ ደኖች ተመንጥረው እየተቃጠሉ ወደ 60% የሚደርስ የጥቁር ካርቦን ብናኞች በንፋስ ሃይል ወደ አንታርክቲካ ተወስዶ ጉዳት እያደረሰ ነው።

        ፈጣን የማብረድ ውጤት ለማምጣት ስጋን ማምረት ማቆም

        በሚቀጥሉት አስርና ሁለት አስርተ-አመታት ፕላኔታችንን መብረድ/መቀዝቅዘ ማየት ከፈለግን መጀመሪያ ሚቴንን መቀለስ የበለጠ አመርቂ ውጤት ያስገኛል። እናም በፕላኔታችን ላይ ትልቁ የሚቴን ምንጭ እንሰሳት ስለሆኑ፣ ቪጋን መሆን ፈጣኑ የጋዙ መቀነሻ መንገድ ነው፣ በዚህም ፕላኔቷን በፍጥነትና በስኬት ማቀዝቀዝ ማለት ነው።

        የዩኤስኤ ተመራማሪና የአይፒሲሲ አባል የሆኑት ዶ/ር ኪርክ ስሚዝ እንዳሳዩት በጥቂት አመታት ጊዘ ውስጥ የሚቴን መክሰም ካርቦንዳዮክሳይድን ጥሎት ያልፋል፣ እናም በአስርተ አመታት ውስጥ ይህ ከመላ-ጎደል ሲጠፋ ካረቦንዳዮክሳድ ግን ፕላኔቷን በማሞቅ በከባቢ አየር ውስጥ ለሺህ አመታት ይቆያል። ስለዚህ ፕላኔቷን በፍጥነት ለማቀዝቀዝ ከፈለግን ቀደም ብለው ሊጠፉ የሚችሉትን ማስወገድ ነው። 71

        በሌላ አነጋገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሚቴን የበለጠ ጎጂ ነው፣ ካቆምነው ግን የአለም ሙቀት መጨመር አዝማሚያ በፍጥነት መቀልበስ እንችላለን።

        እጅግ የተሻለው ነገር ስጋ መብላትን መተው ነው፣ እስሳትን መግደል ማቆም ነው፣ የእስሳት እርባታን ማስቀረት ነው። ከዚየም ሚቴንና ናትረስ ኦክሳይድ ይጠፋሉ ማለት ነው። በዚህ መሰረት ትልቁን የአየር ብክለትም ቀነስን ማለት ነው። የአለም ሙቀት መጨመርንም ሂደት ጋታን ማለት ነው። እንደነገርኳችሁ 80%ው ወዲያው ይወገዳል፤ ውጤቱንም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ማየት እንችላለን።


        ውቅያኖሶችን መትረፍ


        የውቅያኖሶችን ሙት ቀጠናዎች መስፋፋት መግታት

        የእንስሳት እርባታን ማቆም ሌሎች በርካታ ፋይዳዎች አሉት። ለምሳሌ የውቅያኖስ ሙት ቀጠናዎች በመሰረቱ የሚፈጠሩት በአብላጫው ከእንስሳት የመኖ እርሻ ከሚፈስ ማዳበሪያ ነው። የውቅያኖስ ሙት ቀጠናዎች ሙት ቀጠናዎች ለውቅያኖስ ስነ-ምህዳር ደህንነት አደገኛ ናቸው፣ ነገር ግን ከእንስሳት ጋር የተያያዘውን ተግባራትን፣ ውቅያኖሶችን መበከል ካቆምን ይህን ሁኔታ ማስቀረት እንችላለን።

        ግዙፉ የሜከሲኮ ባህረ-ሰላጤ የሙት ቀጠና - ኒው ጀርሲን የሚያክለው የሚያክለው፣ ፍጥረተ-ውሃን ያፈነው በመሰረቱ ከመካከለኛው ምእራብ የሚፈሰው የናትሮጀን ውህድ ነው፣ የእንስሳት ቆሻሻና ከምግባቸው (ሰብል) ማምረቻ ማሳ የሚፈሰው ማዳበሪያ ውጤት ነው፤ ይህ ቆሻሻ መርዛማ ነው። አንቲባዮቲክ፣ ሆርሞኖችና ጸረ-ተባይ መርዞች፣ እናም ከ10 እስከ 100 ጊዜ ሃይለኛ ገዳይ በሽታ-አምጪ ተዋስያን - እንደ ኢ-ኮላይና ሳልሞኔላ ያህል ይዘት ያለውን የያዘ ነው፣ ከሰው ሰገራ ጋር ሲወዳደር።72

        አንድ ጊዜ በ1995 ስምንት ኤከር (16ሄክታር የህል) ትልቅ በአሳማ ፍግ የተሞላ የውሃ ገንዳ pig-manure lagoon በሰሜናዊ ካሮሊና ፈንድቶ ወደ 25ሚሊዮን ጋሎን (100ሚሊዮን ሊትር የህል) መርዛማ ቆሻሻ፣ በአውዳሚነቱ የታወቀውን የኤክሶን-ቫለዴዝ Exxon-Valdez  ነዳጅ ፍሳሽ እጥፍ የሚሆን ፈሶ/አምልጦ ነበር። በቆሻሻው ውስጥ የሚገኘው የናትሮጂን ውህድ በኒው ወንዝ ውስጥ የሚገኙትን በመቶ ሚሊዮን የሚቀጠሩ አሳዎችን ወዲያውኑ ለህልፈት ሲዳርግ ብከላው ወደ ውቅያኖሱም በመዛመቱ የበለጠ ጉዳት አድርሷል።73

                       “ኦክሲጂን-አጠር የሆኑ ሙት የውቅያኖስ ቀጠናዎች ቁጥር በ1960ዎቹ ከነበረው
                       ከ49 በ2008 ወደ 405 አድጒል”
        74

                                                    —ዶ/ር ካቲ ዋለተርስ,  በአላስካ ዩኒቨርሲቲ, የውሃ ምህዳር ባለሙያ


        አሳ ማጥመድን በማቆም የባህር ህይወትን ማትረፍ

        ለውቅያኖስ ሚዛን መጠበቅ የባህር አሳን በእጅጉ እንፈልጋለን፤ አለበለዚያ ህይወታችን በአደጋ ላይ ይወድቃል።

        አሳን ማጥመድ የአለምን የተወሳሰበውን የውቅያስ ስርኣተ-ምህዳሮችን ስለሚረሽ ለአለም ሙቀት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል። እንደሚታወቀው ፕላኔታችን ከ2/3ኛ የበለጠ በውቅያኖስ የተሸፈነች ስለሆነ ሚዛኑን የጠበቁ የባህር ምህዳሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው።

        በውቅያኖስ ውስጥ የሚኖር እያንዳንዱ ህይወት ያለው ነገር ሁሉ የተለየ ተግባር ያለው ስለሆነ የውቅያኖስ ምህዳር በጣም የተወሳሰበ ነው። ስለዚህ አንዱን አሳ እንኳን ለሰው ምግብነት ማውጣት የባህሩን ሚዛን ያናጋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ይህንን የሚዛን መዛባት ተጽእኖ/ውጤት በባህር ውስጥ በሚኖሩ አጥቢ እንስሳት ላይ ያየነው ጉዳይ ነው።

        አሳን ማጥመድ አቁም እናም የባህር ህይወት ሲለመልም ይታይሃልና። በአሟጣጭ የ ሰርዲን አሳ ማጥመድ ምክኒያት በናሚቢያ ጠረፎች የተከሰተው የጎጂ ጋዞች መፍላት የአካባቢው ስነ-ምህዳር በማጥፋት ሙት ቀጠናን ፈጥሯል።ይህም የሆነው ያን ንጹህና የስነ-ምህዳሩ ወዳጅና ጠቃሚ ሃይል ያለውን ፍጥረት የማጥፋት ውጤት ነው። 75

        አሳን አሟጦ ማስገሪ አሳዎች እየመነመኑ እያነሱ እንዲሄ ያደርጋል፣ ስለዚህ ትንንሾቹን አሳዎች ለማጥመድ የማጥመጃ መረቡ የቀዳዳ ስፋት ማነስ አስፈለገ፣ ይህ ሌሎችንም አሳዎች ያጠምዳል። ይሀ የበለጠ የባህር ስነ-ምህዳሩን ያጠፋል፣ ተጨማሪ አሳዎችን ህይወት ያጠፋል። ለእንስሳት ምግብነት፣ ለማዳበሪያ ወይም ከሞቱ በኋላ ወደ ባህር ነው እጣ-ፈንታቸው። ለምሳሌ ለያንዳንዱ ቶን የፕራውን አሳ ማጥመድ ሶስት ቶን ሌሎች አሳዎች ተገድለው ይጣላሉ።

        አንድ የዩኤስ አሜሪካ ጥናት እንዳጋለጠው አሳሞችና ዶሮዎች ጠቅላላው የጃፓን ህዝብ የሚመገበውን እጥፍ ያህል እንዲመገቡ ይገደዳሉ፣ ስድስት እጥፍ የመላው የአሜሪካ ህዝብ የሚመገበውን ያህል ማለት ነው። ዛሬ ከሚጠመደው አሳ ቢያንስ አንድ-ሶስተኛ ያህሉ ለሰው ሳይሆን ለእንስሳት ምግብነት ይውላል።

         

         የሚነገሩን ግምቶች ሁሉ ትክክል ከሆኑ በ40 አመታት ጊዜ ውስጥ አሳ-አልባ መሆናችን ነው። 76

                                                      ፓቫን ሹክዴቭ የተመድ የአካባቢ መርሃ-ግብር የአረንጒዴ ኢኮኖሚ ጥረት ሃላፊ


        የውሃ እጥረትን ማስቀረት



        እንስሳት፡ ትልቁ የውሃ ማጠራቀሚያ

        የእርሻ ተግባሮቻችንና የውሃ ሃብታችንን እንዴት በማስተዳደር ላይ እንደምንገኝ እንደገና መመርመር አለብን፣
        እርሻና የእንስሳት ማርባት ለ70% የውሃ ተጠቃሚነትና 80% የደን ጭጨፋ ጋር የተያያዙ በመሆናቸው። ”

                                                                                                                                                                               — ባን ኪ-ሙን 

        ውሃ ማለት ለህይወታችን ሁሉም ነገር ማለት ነው፣ ውሃ ህይወት ነው። ውሃን መጠበቅና መንከባከብ አለብን፣ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን። የመጀመሪያው እርምጃ ቪጋን መሆን ነው፣ ምክኒያቱም በፕላኔታችን 70% በላይ የሚሆነውን ንጹህ ውሃ የሚጠቀመው የእንስሳት እንዱስትሪ ስለሆነ ነው።

        በእንጻሩ 1.1 ቢሊዮን የሚገመት ህዝብ የንጹህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ አይደለም፣ በያመቱ 3.8 ትሪሊዮን ቶን የሚሆን ብርቁ/ውዱ ንጹህ ውሃ ለእንስሳት ማምረቻ/እርባታ ነው የሚውለው።

        የአለማችን የህዝብ ቁጥር ከ ስድስት ቢለዮን በላይ ሲሆን፣ ግማሹን የአለማችን ህዝብ የሚያገለግለው ምንጭ ለጉድጒድ ውሃ ምንጭ የሆነው የከርሰ-ምድር ውሃ እየደረቀ እየሞተ ነው። እናም የአለማችን የመጀመሪያዎቹ አስር ወንዞች በመድረቅ ላይ ናቸው፣ እየጠፉ ናቸው። እናም ሶስት ቢሊዮን ህዝብ የውሃ እጥረት አጋጥሞታል።

         

          የውሃ እጥረት አለብን?

          እንድ የስጋ ምግብ ከ1,200 ጋሎን በላይ ውሃ ይፈጃል፣

          እንድ ከዶሮ የተሰራ ምግብ ከ330 ጋሎን ውሃ በላይ ይጠቀማል፣

          እንድ የተሟላ የቪጋን ምግብ ከቶፉ ሩዝና አትክልት ጋር ከ98 ጋሎን ውሃ
          ብቻ ይወስዳል፣77



        ገላችን እንኳን ባንታጠብ፣ ጥርሶቻችን ባንቦርሽም፣ ይህ ምንም ማለት አይደለም ስጋ መብላትን እስካላቆምን ድረስ።

        አሜሪካኖች የውሃ እጥረት ስጋት ገብቷቸዋል። የበረዶ ሽፋኑ እየቀለጠባቸው ነው። ወንዞቻቸውም እየደረቁ ናቸው። በጥቂት አመታት ውስጥ ውሃው ለ23 ሚሊዮን ህዝባቸው እንኳን በቂ አይሆንም።78


        የኦርጋኒክ ቪጋን አመጋገብ፡
        90%ውን የአለም ውሃ ይቆጥባል


        የመረጃ ምንጩ፡ ማርሽያ ክሬት፣ በካሊፎርኒያ ምግብ ማምረቻ የውሃ ግብኣት፣ የውሃ ውሃ ትምህርት ተቋም መስከረም
        1991 (ሰንጠረዥ ኢ3 ገጽ28)

        ስጋን ማምረት ግዙፍ ውሃ ይጠይቃል። አንድ የስጋ ምሳ ለማዘጋጀት እስከ 1200 ጋሎን (4800 ሊትር) ንጹህና መልካም ውሃ ይጠይቃል። 79  በአንጻሩ አንድ የተሟላ የቪጋን ምግብ 98 ጋለን ብቻ ይፈልጋል። ይህ ከ90% በላይ ያነሰ ነው።

        የውሃ እጥረትን ማስቀረት እንችላለን። ድርቅ ህዝቦቻችንን እያሰቃየ ውሃን ማባከን አንችልም/አይገባም። ስለዚህ የውሃ እጥረትን ለመቅረፍና ብርቅዬውን ውሃ ለመንከባከብና ለመጠበቅ የእንስሳት ምርቶችን ማቆም አለብን።


        መሬትን መጠበቅ



        ግጦሽና በረሃማነትን ማስቆም

        የእንስሳት ዘርፍ አንዱና ትልቁ ሰው-ሰራሽ የመሬት ተጠቃሚና የመጀመሪያው የደን መጨፍጨፍ ተጠያቂ ሃይል ነው።

        መሬት ግጦሽን በማስቆም አፈሩንና ህይወታችንን መጠበቅ አለብን። የእንስሳት መሬትን መጋጥ ዋናው የበረሃነትና የሌሎች ጉዳቶች መንስኤ ነው፣ እንዲሁም 50% ለሚሆነው የመሬት መከላት ተጠያቂ ነው።

        በአለም ላይ ያለን የመሬት ሽፋን 30% ብቻ ነው። ከዚህ ውድ 30% አንድ-ሶስተኛው ነው በጥቅም ላይ የዋለው፣ ይህ ለሚገባን ህይወታችን ሳይሆን ለእንስሳት ከሎ ወይም የእህል ምግባቸውን ለማምረት ነው - ሁሉም ጥቂት የስጋ ቁርጥራጮችን ለማምረት።

        ለምሳሌ አንድ ቢሊዮን ኤከር (405,000ሄክታር) ወይም 80% ከጠቅላላው የአሜሪካ የእርሻ መሬት፣ ከጠቅላላው የአሜሪካ መሬት ግማሽ ያህሉ ለስጋ ምርት ይውላል።  በአንጻሩ ከሶስት ሚሊዮን ኤከር (1.2ሚለዮን ሄክታር) ብቻ ለአትክልት እርሻ የዋለ ነው።80

        አንድ በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በሜክሲኮ 47% ሚሆነው መሬት በእንስሳት እንዱስትሪ ምክኒያት ወደ በረሃማነት ተለውጧል።81 ሌላም ከ50 እስከ 70% የአገሪቱ ክፍል በድርቅ እየተሰቃየ ይገኛል።

        በመላው ሜክሲኮ ለእንስሳት እርባታ መሬቱ በመመንጠሩ ሚዛኑ ተዛብቶ አስጊ የአፈር መበላሸት አስከትሏል። በሰሜናዊው የአገሪቱ አካባቢ ሁለት-ሶስተኛ የሚሆነው መሬት በአጠቃላይ በፍጥነት እንደተከላ ይቆጠራል። 82 እንስሳቱ ያገኙትን እጽዋት በመብላትና መሬቱን በመደምደም የሚታየው ሲሚንት የመሰለ ምንም ሊያበቅል የማይችል መሬት ብቻ ነው። ይህ የአለሙን የሙቀት ጭማሬ ያባብሰዋል፣ ምክኒያቱም ከሚሞቱት እጽዋትና ከተራቆተው አፈር ተጨማሪ ካርቦን ስለሚለቀቅ ነው።


        የአለምን ረሃብ ማስወገድ



        እያንዳንዱ ሰው እጽዋትን-መሰረት ያደረገ አመጋገብ ቢከተል ለአስር ቢሊዮን ህዝብ የሚበቃ ምግብ ይኖራል።

        እንስሳትን በማርባት መሬትን ማባከን


        የምግብ እጥረት አለብን
        ?

        በአለማችን ምን ያህል ሰዎች ናቸው የተራቡት? 1.02-ቢሊዮን ሰዎች።

        በየአምስት ሰከንዱ አንድ ህጻን በረሃብ ይሞታል።

        በአሁኑ ሰኣት እንስሳት የሚመገቡት እህል ሁለት ቢለዮን ሰዎችን ሊመግብ
        ይችላል።
        83

                                                                                              —ጁሊ ጌለትሊና ቶኒ ሃርድል


        በአሜሪካ
        90% አኩሪ አተር፣ 80% በቆሎና 70% የሚሆነው እህል እንስሳትን ለማደለብ ይውላል ፣ ይህ ቢያንስ 800 ሚሊዮን ሰዎችን መመገብ የሚችል ነው። 84 መሬቱን፡ ውሃውንና ምግቡን ከሰዎች ይልቅ ለእንስሳት በማዋላችን ሰዎች እየተራቡ ናቸው፣ ህጻናት በሴኮንዶች ውስጥ እያለቁ ናቸው።

        ስጋ ባንመገብ የእርሻ ምርቶችን፣ እህልን ከምናራባቸው እንስሳት ይልቅ ሰዎችን መመገብ እንችላለን። በዚህም ረሃብን እናስወግዳለን፣ እናም በረሃብ ምክኒያት የሚካሄድ ጦርነት ይቀራል። ጥቅሙ ብዙ ነው።


        የመሬት አጠቃቀም ብቃት?



        የመረጃ ምንጨፀ: የዩኤስኤ የእርሻ መምሪያ፣ ኤፍኤኦ/ደብሊዩኤችኦ/ዩኒሴፍ የፕሮቲን አማካሪ ቡድን፣ 2004


        በተጨማሪም የተፈጥሮ/ኦርጋኒክ የአስተራረስ ዘዴን የከተከተልን የበለጠ ምግብ ማምረት እንችላለን፣ ጤናችንም ይጠበቃል፣ አፈሩም ጤናማ ይሆናል። ከዚያም አፈሩ ያገግማል፣ እናም የተትረፈረፈ ምግብ ይኖረናል ማለት ነው። 



        ደን ጭፍጨፋን አቁም



        ዛፎችን በመትከል የደን ጭፍጨፋን ማስቀረት አለብን።  የመሬት መከላት ባለበት እንዲሁም በባዶ ስፍራዎች ሁሉ ዛፍ መትከል ያስፈልጋል፡።

        ስጋን ማምረት የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ አራማጃ ሃይል ነው። እንደ የተመድ ግምት 20% የሚሆነው የሙቀት-አማቂ ጋዝ ልቀት ከስጋ ጋር በተያያዘ መልኩ የደን መጨፍጨፍ ውጤት ነው። 86 80% የሚሆነው የአማዞን ደን የሚመነጠረው እንስሳቱን ለእርድ ለማዘጋጀት ለከብቶች ግጦሾሽ ነው፣ ቀሪው ደግሞ እንስሳቱን ለመመገብ አኩሪ አተር ይዘራል።

        እንስሳትን ለማርባት በያመቱ እንግሊዝ የሚያክል የደን መሬት ይመነጠራል። ለዚህ ነው ፕላኔታችን በሙቀት እየጋለች ያለችው፣ እናም በርካታ ስፍራዎች በድርቅና ጎርፍ ይጠቃሉ።

        250 ሀምበርገሮችን ለማምረት
        አንድ የእግር ኳስ ሜዳ የሚያክል የደን መሬት በየሰኮንዱ
        ይመነጠራል
        87

        55 ካሬሜትር የዝናብ ደን ለያንዳንዱ ሀምበርገር እናጣለን ማለት ነው። 88

        ደን ካርቦንዳዮክሳይድን በመምጠጥ ትልቅ ድርሻ አለው። ለምሳሌ የአሜሪካው የሰሜናዊ ፓስፊክ አካባቢ ከጠቅላላውን የኦሪገን ከ/ሀገር ልቅት ግማሹኝ ያህል ሊመጥ ይችላል።

        እንደ ግሪን ፒስ፣ የአካባቢ ተቆረቃሪ ድርጅት 8% ከምድር ደን ጋር የተያያዘው ካርቦን የተከማቸው የሚገኘው በማእከላዊ አፍሪካ በጉዙፉ የኮንጎ ወንዝ ተፋሰስ ነው። ተከታታይ የኮንጎ ድን ጭፍጨፋ ከዩኬ የ60 አመታት የCO2 ልቀት ጋር ተመጣጣኝ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች። 89 ስለዚህ ደኑን መጠበቅና መንከባከብ የሚያስፈልገው፣ አሁን እድሉ እያለን።

        ዛፎች ዝናብ ይስባሉ፣ አፈር ይጠብቃሉ፣ የአፈር መከላት ይከላከላሉ። ኦክሲጅን ይሰጣሉ፣ ጥላ ይሆናሉ፣ የደን ወዳጅ ለሆኑት ለእንስሳት መጠለያ ናቸው፣ እነዚህም በተራቸው ፕላኔታችን በጥሩ የስነምህዳር አኳኳን እንድትቀጥል አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

        የደን ጭፍጨፋ ደኑ የሚቆጣጠረው ቋሚ/የተራዘመ የአለም የሙቀት፣ የዝናብና የአየር ጸባይ ሁኔታ ለውጥ ብቻ አይደለም። በደኖች ላይ ኑሮው የተመሰረተው በሚሊዮን ስለሚቆጠር ህዝብም ብቻ አይደለም። ነገሩ ከዚህ የበለጠ ነው።


        ሃይል መቆጠብ

        ስጋን ለማምረት የሚጠይቀው የሃይል ዋጋ

        ስጋ ማምረት ከፍተኛ ሃይል ፈላጊ ነው፣ ሃይል አባከኝም ነው። እንድ ኪሎግራም ስጋ 169 ሜጋ ጁልስ (169-ሚሊዮን ዋት) ይህል ሃይል ይጠይቃል፣ ይህ ንድ መካከለኛ የአውሮፓ መኪና 250 ኪሎ ሜትር ይህል ማስናዳት የሚችል ሃይል ነው!

        አንድ ባለ ስድስት-አውንስ (170ግራም) የስጋ ስቴክ 16 እጥፍ የበለጠ የነዳጅ ሃይል ይፈጃል፣ ሶስት አይነት አትክልትና ሩዝ ከያዘ የቪጋን ምግብ ጋር ሲነጻጸር።

                                           

        የመረጃ ምንጭ: ጊዶን ኢሼልና ፓሜላ አ ማረቲን፣ምግብ፣ ሃይልና የአለም ሙቀት መጨመር
        አርዝ እንተራክሽን, ቅጽ10 (2006), ገጽ
        9

        በተጨማሪም ስጋ ማቀዝቀዣ፣ መጓጓዣና መጋዘን እንደሚፈልግ፣ እያደገ የመጣ የእንስሳትን ለምግብ የማጓጓዝ፣ ማሸግ፣ በለጂም ጊዜ በከፍተኛ ሙቀት የማብሰል፣ እንስሳቱ የሚለቁት ቆሻሻ ማበምንና ማስወገድን የሚፈልግ መሆኑን  የተመድ ኢፒሲሲ ሊቀ መንበር፣ ዶ/ር ራጄንድራ ፓቻሪ በአክረው ይገልጻሉ። ስጋን ማምረት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀቀና አባካኝ ነው፣ ዘላቂና አዋጭ ያልሆነ መጥፎ የስራ ዘርፍ ነው። 91

        ትክክለኛ የስጋ ዋጋ


        አንድ ፓውንድ (ግማሽ ኪሎግራም) ስጋ ለማምረት 2,500 ጋሎን (10,000 ሊትር) ውሃ፣  12 ፓውንድ (6ኪሎግራም) ጥራጥሬ፣ 35 ፓውንድ (17 ኪሎግራም)  ለም አፈርና ከአንድ ጋሎን (4 ሊትር) ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የነዳጅ ሃይል ይፈልጋል። እነዚህ ሁሉ ወጪዎች በምርቱ ዋጋ ላይ ቢደመሩ/ቢንጸባረቁ፣ ካለ ድጎማ ዝቅተኛው/በትንሹ የሀምበርገር ዋጋ በዩኤስኤ $35  ያወጣ ነበር። 92

                                                                                                                                            —ዮሃንስ ሮቢንስ

        የብዝሃ ህይወት ተሃድሶ



        በዚህች ፕላኔት ላይ ሁሉም ነገር፣ እኛ ጨምሮ የተያያዘ/የተሳሰረ ነው፣ እናም ኑሮን አመቺ አድርጎ ለመኖር እርስ በርስ እንረዳዳለን። ግን ይህ ካላወቅን ራሳችንን ገደልን ማለት ነው።  አንድን ዛፍ  ወይም እንስሳ ስንገድል የራሳችንን ትንሹን ክፍል ገደልን ማለት ነው።

        በታክሶኖሚ ቡድኖች ጥናት የቀረበ የተለያዩ ዝሪያዎች አጠቃላይ አስጊ ሁኔታ



        ምስጋና: የባህዮሎጅካል ኮነቬንሽ ኦን ዳይቬርሲቲ ጽ/ቤት አለማቀፋዊ የብዝሃ-ህይወት እይታ 3, 2010, http://www.cbd.int/doc/publications/gbo/gbo3-final-en.pdf, 28


        በውቅያኖስ፣ በጅረቶችና በሌሎች የውሃ አካላትየገኙ የነበሩት ብዙ የአሳ ዝሪያዎች ጠፍተዋል፣ እንደ ኮራል ሪፍ የባህር አካባቢዎች ከገጸ-ምድር እንዲጠፉ ተደርገዋል በማስገሪያ ፈንጂዎችና ማጥመጃዎች የአሳ ማጥመጃ ተግባሮች። በመሬት ላይም ስጋን መመገብ ለሰፊ መሬቶች መመንጠርና ለግጦሽና ለእንስሳት መኖ አኩሪ አተርን የመሳሰሉ ሰብሎች መዝዪያ መዋል ተያቂ ናቸው።

        እነዚህ ድርጊቶች ሁሉ የብዝሃ-ህይወት ሃብታችንን እየዘረፉ ስለሆነ በአስደንጋጭ ሁኔታ የእንስሳትና የእጽዋት ዝሪያዎች እየጠፉ ናቸው።  93



        በታክሶኖሚ ቡድኖች ጥናት የቀረበ የተለያዩ ዝሪያዎች አጠቃላይ አስጊ ሁኔታ


        በውነት ንጹህና ጤናማ ውሃን ለራሳችንና ለልጆቻችን ለመጠበቅ/ለማቆየት ከፈለግን፣ እንስሳትን ማርባት አቁመን እጽዋትን-መሰረት ያደረገ አመጋገብ መከተል አለብን።

        የዩኤስ የአካባቢ ጥበቃ መ/ቤት እርሻ፣ በአብዛኛው ለስጋ ምርት የሚውል ነው፣ ለሶስት-አራተኛው የውሃ ብከላ ተጠያቂ ነው ይላል። 94 አንድ የአሳማ ማርቢያ/እርሻ፣ ወደ 500,000 አሳማዎች የሚይዝ፣ በያመቱ የሚለቀው ቆሻሻ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ በኒው ዮርክ ከተማ የማናሃታን ነዋሪዎች የሚለቁትን ያህል ይሆናል። በቨርጂኒያ አስተዳደር የዶሮ ማርቢያ/እርሻዎች እንኳን 1.5 እጥፍ የበለጠ የናይትሮጂን ቆሻሻ ይለቃሉ በተማሰሳይ አስተደደሩ ነዋሪዎች ጋር ሲወዳደር። ይህንን የሚቆጣጠር ምንም ደንብ የለም።

        በአየርላንድ 1.8 ሚሊዮን አሳማዎች 4.2 ከሚሆነው ጠቅላላ ህዝቧ የበለጠ ቆሻሻ ይለቃሉ!

        መሬቱ  ይህን ሁሉ መምጠጥ/መሳብ ስለማይችል አብዛኛው ቆሻሻ ወደ ወንዞችና ወደ አፈሩ ይገባል። እየተናገርን ያለነው ስለአስፈሪ መርዛማ ነገርና ዘግናኝ ችግር ፈጣሪ - እንደ ሃይሮጂን ሰልፋይድና አሞኒያ ያሉ  መርዛማ ጋዞችን ጨምሮ፣ የጸረ-ነፍሳት ተረፈ-ነገር፣ ሆርሞኖች፣ አንቲ-ባዮቲክና ባከቴሪያ ኢ-ኮላይ ያሉ ምግብን በመመረዝ ሞትን የሚያስከትሉትን ጠንቆች ነው።        

        እንደ ሳይንቲስቶች የተጠናቀረ መረጃ ከሆነ ከቆሻሸው ጋር ለእንስሳት ምግብ ከሚውል ሰብል ማብቀያ ማሳዎች የሚለቀቅና የሚፈስ ኬሚካል ማዳበሪያ ለሙት ቀጠናዎችና አልጌ፣ በውሃ አካላት ላይ የሚበቅል አረንጒዴ ነገር፣ ወረርሽኝ መንስኤ የሆነ ተጨማሪ ችግር አለ።

        በብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ አብዛኛኛው የአገሪቱ እንስሳትና ሲሶው የወተት ልማት ጣቢያዎች የሚገኙበት አካባቢ እንዲህ ያለ ነገር ተስተውሏል። በብሪታኒያ ጠረፍ ይህ ቆሻሻና የኬሚካለ ፍሳሽ ወደ ባህሩ እየገባ አደገኛና ገዳይ የሃይድሮጂን ሰልፋይድ ጋዝን የሚለቅ የመርዛማ አልጌ ወረርሽኝ መንስኤ ነው። አልጌው ውስጥ በመግባቱ አንድ ፈረስ በግማሽ ደቂቃ ውስጥ እንደ ሞተ በቅርቡ በዜና እንደተሰማ በአካባቢው የሚኖሩት 300 ሰዎች የጤና ጉዳይ እየተጠና ይገኛል።

        ይህንን ሁሉ የሚያባብሰው ከቁጥጥ ውጪ የሆነ የእንስሳት ቆሻሻ ነው፣ ማለትም ለተለያዩ ይንስሳትና ሰዎች በሽታዎችና ሞት መንስኤ የሆነውን ይህን ብከላ የሚገታ ምንም ነገር የለም።

        (ለተጨማሪ ከእንስሳት ቆሻሸ የሚመነጭ ብከላ ምሳሌዎች እባክዎ እዝል 9 ይመልከቱ፤)


        የገንዘብና የጤና ወጪን መቅረፍ


        የአለም ሙቀት መጨመርን የመስርየት ወጪን በትሪሊዮች ማዳን

        መሪዎች የአየር ለውጥን ለመስርየት ለሚደረገው ወጪ እየተጨነቁ ናቸው። ሆኖም አስደሳሹ ዜና አለም ከእንስሳት-ነጻ ወደ ሆነ የአመጋገብ ስርኣት ቢለወጥ ወጪውን ከግማሽ በላይ መቀነስ እንችላለን። ይህ ማለት በአስር ትሪሊዮኖች ዶላር መቀነስ ነው።

                •  የአየር ለውጥ ወጪ

        በአውሮጳ ኮሚሽን ጥናት ግምት የአየር ለወጥ እስከ $74 ትሪሊዮን ወጪ ሊጠይቀ/ ይችላል። የአንድ ሜትር የባህር ከፍታ የባህር ማእበል በመጨመር እስከ $1.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት የንብረት ጥፋት ያስከትላል። 95  

                —የአካባቢ ሳይቲስቶች  ፋ. ኤከርማንና ኢ.ስታንቶን

                 የጃፓን የቸልተኝነት ዋጋ እስከ $176 ቢሊዮን/አመት ይደርሳል በ2100። 96

                —ፕሮ.ኖቡኦ ሚሙራና ባልደረቦቹ

                •  በቪጋን አመጋገብ ገንዘብ መቆጠብ

        አለማቀፋዊ የቪጋን አመጋገብ መከተል በ2050 ከሚያስፍልገው ጠቅላላው ወጪ ማለትም $40-ትሪሊዮን የአየር ለውጥን ለመሰርየት የሚያስፈልገውን እስከ 80% ($32 ትሪሊዮን ዶላር) ወጪ ይቀንስልናል 97

                —ኤለክ ስቴፌስት በኔዘርላንድ የአካባቢ ዳሳሽ አጀንሲ



        የጤና ወጨዎችን መቀነስ

        ስጋ በመብላት የሚመጣ የጤና ጠንቅ እየጨመረ እንደመጣ ግልጽ ነው። እንስሳት ሆርሞንና አንቲባዮቲክ በብዛት እየተሰጣቸው፣ እንደ ስጋ ሲበሉ የሰውን ጤና አደጋ ላይ ይጥላሉ።

        ደግሞም በቄራያዎች አካባቢ እንደ አሞኒያና ሃይድሮጂን ሰልፋይድ ያሉ መርዛማ ተረፈ-ምርቶች ይኖራሉ። እነዚህ መርዛማ ነገሮች የብዙ ሰራተኞችን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ።

        ስጋ እንደ ምግብ የሰው ልጅ ወደ ሰውነቱ የሚወስድ የጤናማ ያልሆነ፣ መርዝ፣ ንጽህና የጎደለው ነገር ነው። ለጤናችን የምናስብና ህይወታችንነ የምንወድ ብንሆን ኖሮ ስጋ በጭራሽ አንበላም ነበር። ያለ ስጋ እድሜያችን ረዥም፣ ጤነኞች፣ ጥበበኞች ነን።

        ሳይንስ ስጋን የብዙ አይነት ካንሰሮች፣ የለብጋግጠ ህመም፣ የደም ግፊት፣ስትሮክ ከመጠን በላይ ውፍረት መንስኤ እንደሆነ አረጋግጧል። ዝርዝሩ ይቀጥላል፣ ይቀጥላል። እነዚህ ከስጋ መብላት ጋር የተቆራኙ በሽታዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሰዎች ይገድላሉ፤ ሌሎች ሚሊዮን ሚሊዮን ሰዎችን ለህመምና አካለ-ጎዶሎነት ይዳርጋሉ። ስጋ መብላት የሚያስከትለው ትራጄዲ/አሳዛኝ ፍጻሜ መጨረሻ የለውም። ባሉት ሳይንሳዊና ህክምና መረጃዎች እስካሁን ይህንን ማወቅ ነበረብን።

        አስቀያሚውን/ቆሻሻውን ሁኔታ ሳናወሳ፣ እንስሳቱ እስከሚታረዱ ድረስ የሚቆዩበት የተጨናነቀው አካባቢ፣ እንደ የኣሳማ ጉንፋን አምጪ-ቫይረስ ያሉትን የሚያሰራጭ ነው። እውነቱ በስጋ የሚተላለፉ በሽታዎች የሰውን የሚመስለው እንደ እብድ ላም ያሉ በሽታዎች እጅግ ጋዳይ ናቸው። የእብድላም በሽታ የያዘው ሰው ከአሳ!ኝ ሞት ሊተርፍ አይችልም። እንደ ኢ-ኮላይ፣ ሳልሞናላ፣ ወዘተ፣ ያሉ ሌሎች በካዮችም አደገኛ፣ ለዘለቄታው ጎጂ የሆኑና ወደ ሞት የሚያመሩ በሽታ ሊያመጡ ይችላሉ።

        በቪጋኑ አለም፣ በመሰረቱ ከእንስሳት ማረቢያ ከሚመነጩ፣ በኢ-ኮላይ፣በገዳይ ባክቴሪያ መንስኤነት የህጻነትን አእምሮ የሚጎዳ ወይም የሽባ በሽታ አሳዛኝ ዜና አይኖርም። በኣሳማ ጉንፋን ወረርሽኝ፣ ወይም በእብድ ላም በሽታ፣ በካንሰር፣ በስኳር፣ በስትሮክና በልብ፣ በሳልሞላ፣ ኢቦላ፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ምክኒያት የራስ ምታት እንኳን አይኖርም። በጣም የምንፈራው ኤድስ እንኳን፣ መነሻው ለምግብ እንስሳት ከማደን ነው። ከአስቀያሚውና ቆሻሻው የእንስሳት ማርቢያ አካባቢዎች 75% ለሚሆኑ ሰውን እያሚያጠቁ ላሉት በሽታዎች ተጠያቂ ነው።

        ለጤንነታችን መልካም ነው የተባለው ወተት እንኳን በተቃራኒው የበሽታ(ትልቅ ወጪን ጨምሮ) መንስኤ የሆነ መርዝ ነው። ጥቂቶቹ እነሆ፡ የባክቴሪያ ማይክሮቦች፣ ጸረ-ተባይ መርዝና በቺዝ ከእንስሳት የሆድ ውስጥ የሚገኙ ኤንዛይም፣ በወተት ውስጥ ከሚገኙ ሆርሞኖች የጡት ፕሮስቴት/ካንሰርና የቆለጥ ካንሰር፣ ሊስቴሪያና የክሮን በሽታ፣ ኦስትሮፖሮሲስ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ የስኳርና የልብ በሽታን የሚያመጡ ሆረሞኖችና ስቦች፣

                •  የስጋና ወተት የጤና ዋጋ
                
        2010 በአሜሪካ የልብ በሽታ ህክምና $503,000 ያስወጣል ነበር። 98  
              በአመት የካንሰር ህክምና$6.5 ቢሊዮን ይጠይቃል።
              
        የስኳር በሽታ በአመት $174 ቢሊዮን ነው።
              
        አንድ ሰው ከክብደት ጋር የተያያዘ የህክምና ወጪ በአመት $93 ቢሊዮን ይደርሳል። 99


        ለአረንጒዴ ቴክክኖሎጂ ጊዜ መግዛት


        ካርቦንዳዮክሳይድን (CO2) በፍትነት መቀነስ/ማስቆም አንችልም፣ ምክኒያቱም በአንድ ምሽት ይህንን የሚያከናውን ቴክኖሎጂ አሁን የለንም። በዩኤስኤ ጎዳናዎች ላይ ስንት በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ መኪናዎች እናያለን? ይህ ምን ያህል ካርቦንዳዮክሳይድ ይቀንሳል? ብዙ አይደለም። የሚቴን ብከላ ግን ከእንስሳት እርባታ፣ ያንን ካቆምን የሙቀት መጨመር ብሎ ነገር አይኖርም!

        ሳይንስ ትንሽ በመራመድ ካርቦንዳዮክሳይድን በመሰብስ ከባህር ውሃ ጋር ቀላቅሎ ሲሚንቶ መፍተር ችሏል። ያ ሲሚንቶን ለማመምረት ካርቦንዳዮክሳይድን ለሚጠቀሙ የአሰራር ስልቶችና አዲስ ካርቦንዳዮክሳይድን ከባቢ አየር እንዳይ በከል ለመቀነስ ይረዳል። ነገር ግን አዲስ ቴክኖሎጂ ሰርቶ ገበያ ለማውታት ረዥም ጊዜን ይጠይቃል።

        ካርቦንዳዮክሳይድን በመምጠጥ የተፈጥሮ ሳርና ደን ከካርቦን-ሰብሳቢ ቴከኖሎጂ የበለጠ ውጤታማ እንደሆኑ የተመድ የአካባቢ መርሃ-ግብር ገልጿል። በተጨማሪም እንደሚመስለኝ አስተማማኝም አይደሉም። በደንብ አልተሞከሩም። ካርቦኑ እንደገና በተጠናከረ መልክ ወደ አየር የሚሾልክ/የሚያመልጥ ቢሆንስ? ከአመት እስከ አመት፣ በአስርተ አመታት ሰብስበን፣ እናም አንድ ነገር ቢከሰት፣ ቢያመልጥ ምንልናደርግ ነው

        ስለዚህ በቪጋን አመጋገብ፣ ለጤናችን የሚስማማውን በመመገብ፣ ለእንስሳቱና ለአካባቢውም  መልካም የሆነውን መመገብ ነው፣ ሌላውን ተፈጥሮ ታስተካክለዋለች፥ ታድሰዋለች፡ ሚዛኑን በመጠበቅ አለምን ታድናለች። 100


         
         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *