• ምእራፍ አራት. የቪጋን ፖሊሲና ህግ ማውጣት > I.የአለም መሪዎች አርኣያ መሆን አለባቸው
      • I. የአለም መሪዎች አርኣያ መሆን አለባቸው


        ቪጋን ሁን



        ያላቸውን ሃይል/ስልጣን ተጠቅመው የፕላኔቷን አመጋገብ እንዲለውጡ እጠይቃቸዋለሁ። እናም በአፋጣኝ አዲስ ቴክኖሎጂ፣ ቀጣይነትና ተተኪነት ያለውን ሃይል መጠቀም።  እራሳችው ቬጄቴሪያን ወይም ቪጋን በመሆን ኣርአያነትታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። አመጋገባቸውን መለወጥ። ሃይላቸውን/ስልጣናቸውን መጠቀም። ኣርአያነትታቸውን መጠቀም፣ ለፕላኔቷ አዲስ የአመጋገብ ስርኣት፡ የቬጄተሪያን (ቪጋን) አመጋገብ መዘርጋት።105

        መጀመሪያ ራሳቸው ቬጄተሪያን (ቪጋን) መሆን፣ ከዚያም ስልጣናቸውን/ሃይላቸውን በሀቀኛነት ይጠቀማሉ። ልክ ሲጋራ ማጨስን እንዳገዱ ማለት ነው። ስጋን በማገድ፣ ለሰውም ሆን ለፕላኔቷ የስጋን ጉዳት በመዘርዝርና በመግለጽ ይህን ማስፈጸም ይችላሉ። ልክ ሲጋራ ማጨስ እንዳስወገዱት ይህንንም ማስቀረት ይችላሉ።


        ተግባርህ በፍቅር መርህ ላይ የተመሰረተ ይሁን



        መሪዎቹ ራሳቸውን መለወጥ አለባቸው፣ ከዚያም ስረኣተ-ማህበሩን በመለወጥ የበለጠ ነጻ፣ መንፈሳዊና ሞራሉ ከፍ እንዲል ማድረግ። ምክኒያቱም ይህን ሃላፊነት የነርሱ ነው - ይህ ያለ እግዚኣብር ፈቃድና ቸርነት እና ከለእርሰ ፈር-ቀዳጅ እቅድ ከባድ ነው፣ የተፈጥሮ ህግ ተከትሎ መንቀሳቀስ ይገባል ማለት ነው።

        የመጀመሪያው መርህ፣ እጅግ ተፈላጊው፣ የፍቅር መርህ ነው። በዚህ መርህ መሰረት የሚያከናውኑት ማንኛውም ነገር፣ ይህ መልካም ነው። ማለቴ ለሌሎች ሰዎች ጥሩ ነው። ለሰዎች እድገትና ለሁሉም ጥበቃና ክብር መስጠት ነው- ያ የፍቅር መርህ ነው። ይህንን የሚጻረር ማንኛውም ሌላ ነገር በራሱና በአገሩ ላይ አደጋን ይጋብዛል፣ ወይም በፕላኔቷ ላይ።

        እነዚህ መሪዎቹ መክረው እውነተኛ ማንነታቸውን ለማግኘት ወደ መንፈሳዊ ጎኑ ቢገቡ፣ ታላቅነታቸውን፣ መልካምነታቸውን፣ አፍቃሪነታቸውንና ደግነታቸውን ጥበበኛነታቸውንና የእግዜር ተምሳሌነታቸውን ይገነዘባሉ ። ስጦታቸውንም/ምንዳቸውን ያያሉ። ይህ ግን የሚረጋገጠው ለሰው ልጅ ወይም ለእንስሳት ወይም ለአካባቢው ከልባቸው በሚያበረክቱት መልካም ነገር ነው። የሚችሉትን ያህል አለምን ለመርዳት ከጣሩ፣ የተረዱ ሰዎች ቁጥርና ከልብ ከሆነ  ይህ ትልቅ ነገር ነው፣ እንዲሁ ታላቅ ነገር ይጠብቃቸዋል። እግዜር የልባችንና የስራችንን ያውቃልና።

         

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *