IV. የመልካም አስተዳደር አረኣያዎች/ምሳሌዎች
የአውርጳ ፓርላማ
ስጋ መብላት የአለም ሙቀት መጨመር መንስኤ እንደሆነ የአውሮፓ ፓርላማ ይቀበላል፣ እናም የስጋ እንዱስትሪ የሚደረገውን ድጎማ ለመቀነስና ድጎማውን ለኦርጋኒክ ገበሬዎች ሊሰጥ ሊነጋገር ነው።125
እንደምጠብቀው ፈጣን ባይሆንም፣ ወሳኙ አካል አንድ ነገር ለማድረግ እንቅስቃሴውን ጀምሯል። አንዳንድ ደፋርና ጎበዝ፣ ጀግና መሪዎች ለውጡን እውን ለማድረግ እየረዱ ስለሆነ ይህ ልብ የሚነካና የሚያነቃቃ ነው።
የአውሮፓ ፓረላማ አባል የሆነው፣ ጆን ሆልም የአውሮፓ ህብረት ስጋን በመቀነስ ሙቀት-አማቂ ጋዞችን ዝቅ ለማድረግ የሚያስችል እርምጃዎች እንዲወስድ ጠንክሮ እየሰራ ነው።126
ጀርመን
የጀመኑ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ብራዚልን በመጎብኘት ወደ አውሮፓ በሚላከው ስጋ ምክኒያት የሚጨፈጨፈውን ደን ለመግታት ጠንካራ ደንብ እንዲወጣ ለመርዳት ጥረት አድርገዋል።
ኤርላንድ
አሁን ወደ ኦርጋኒክ ገበሬነት ራሳቸውን የለወጡ ብዙ ሰዎች አሉ። በአየርላንድ፣ የግብርና ሚኒስትሩ ገበሬዎች ወደ ኦርጋኒክ እርሻ፣ ወደ አትክልት ማልማተ እንዲሸጋገሩ ደብዳቤ ጽፎላቸዋል፣ ድጎማም እንደሚገረግላቸው ቃል ገብቶላቸዋል። በመሆኑም በርካታ ገበሬዎች ወደ ኦርጋኒክ እርሻ እየገቡ ናቸው።
ቤልጂየም
በቤልጂየም ታላላቅ ከተማዎች አንዷ የሆነችው ጌነት ሀሙስን የቬጂ ቀን እንድትሆን በይፋ አውጃለች፣ ከዘንድሮው የትምህርት አመት ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ተ/ቤቶች ሁሉ ሀሙስ ሀሙስ የቬጀታሪያን ምግብ ብቻ እንዲቀርብ ተወስኗል።127
ዩናይት ኪንግደም
ልኡል ቻርለስ ያለ ምንም ፍርሃትና በጉብዝና ወጥተው ስለአካባቢ ስለተናገሩ አመሰግናቸዋለሁ። በእውነት አከብራቸዋለሁ፣ ሰላምታዬንም አቀርብላቸዋለሁ። የተግባር ሰው ናቸው፣ ከጊዜ ቀድመው የተገኙም ናቸው። ለምሳሌ አንድ የኦረጋኒክ ምርት ገበያን መርቀው ከፍተዋል፣ በአለም ላይ የዝናብ ደን ጭፍጨፋን ለመግታት ጠንክረው እየሰሩ ናቸው።
ልኡል ቻርለስ የራሳቸውንም የካረቦን አሻራ ለመቀነስ ለምሳሌ በመጓዣ ዘርፍ እየሞከሩ ናቸው። ከራሳቸው የግል ገንዘብ $2.8ቢሊዮን - ሶስት ቢሊዮን ዶላር ማለት ይቻላል ለድን እንክብካቤና መጠመቂያ ሰጥተዋል/መድበዋል።128
ለተደረገው አመራሩ የዩኬን መንግስት በትህትና አድናቆቴን እየገልጽሁ ሁሉንም ዝቅተኛ የካርቦን አሻራ ለሚኖረቸው የወደፊቱ የአገሪቱ ፕሮጀክቶች ድጋችንን እንገልጻለን።
ጠቃሚ የአገሪቱ ዘላቂ የምግብ ፖሊሲን በተመለከተ መንግስቱ የሚያከናውነውን ትንሽ ማለት እፈልጋለሁ። ቀደም ሲል በሀምሌ 2008 በጠ/ሚር ጎርደን ብራውን ያቀረቡት የዩኬን የምግብ ፖሊሲ በሚገመግም ሪፖርታቸው «ጤነኛ፣ አነስተኛ ተጽእኖ የሚኖረው ምጝብ ወተሮ ከምንመገበው ያነሰ ስጋና የወተት ተዋጽኦ ያለው ነው።129
ከዚም ወዲህ እስከ አሁንም ተመሳሳይ ሀሳብ በዩኬ መንግስት ውስጥ እየተበረታታ ይገኛል፡ በብሄራዊ የጤና አገልግሎቱ ፕሮ.ቲም ላንገና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚቴ በመሳሰሉት።130 እንዲያውም «መልካም የግብርና ተግባራት ደንብ» በመሳሰሉ መመሪያዎችን በማውጣት መንግስት ገበሬዎቹን እየረዳ ይገኛል።131
ዩኬ እጽዋትን ያማከለ አመጋገብ የሚከተሉ ወይም የሚሟገቱ እንደ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴትር፣ የምግብና ገጠር ጉዳዮቿ ሂላሪ ቤን፣ የፓረላማ አባሉ ዴቭድ ዲሬውና የአውሮፓ ፓርላማ ም/ሊቀመንበር ኤድዋርድ ማክሚላን የመሳሰሉ መሪዎች አሏት። እነዚህ የትክክለኛው አቅጣጫ አመልካች መልካም ምልክቶች ናቸው፣ እናም ሁሉም አገሮች የዩኬን አርኣያ በመመልከት ለጠቀሙ ይችላሉ።
አሜሪካ
ዩናይት ስቴትስ የሃዋይ ም/ቤትና ሰኔት በመላው የሃዋይ ት/ቤቶች የቪጋንና ቬጀታሪያን ምግቦች አማራጭ ለተመሪዎች እንዲቀርብ በሙሉ ድምጽ ውስኗል።132
እንደ አዲሱ የአየር ንብረት መርሃ-ግብር እቅዷ አካል፣የአለም ሙቀት መጨመርን ለመቀነስ፣ የስጋ ምግብን መቀነስ ለማበረታታት ሲንቺናት፣ ኦሃዮ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ከተማ ሆናለች።133
የመንግስት መሪዎች ስለቬጀታሪያን ፋይዳዎች በይፋ/እቅጩን መናገር ጀምረዋል። ለምሳሌ በዚህ በጋ ወር የዩኤስ ቪጋን የሆኑት፣ የም/ቤት አባል ዴኒስ ኩሲኒች በካሊፎርኒያ የመጀመሪያውን የቪጋን የምድር ቀን ለቬጀታሪያን ለሆኑትም ሆነ ለሌሎቹ ሁሉ መርቀዋል ከፍተዋል።134
ቀደም ሲል በሚያዝያ [2009] ለረጂም ጊዜ ስጋ በይ የሜሪላንዱ፣ ዩኤስኤ ሴናተር፣ ጃኔ ራስኪን አካባቢውን ለመርዳት ሲሉ ራሳቸው የቬጀቲያን ሳምንት አወጁ። ከዚያ ወዲህ በቬጀታሪያን ህይወታቸውን ቀጠሉ፣ መስከረም በሚካሄደው ብሄራዊ የቬጅፌስት ላይም ይናገራሉ ተብሎ ይጠበቃሉ። ይህ መልካም ዜና ነው።135
[በ2009 የባልቲሞር የህዝብ ት/ቤቶች ስርኣት ስጋ-አልባ ሰኞን አወጁ።136
[በሚያዚያ 2010, ሳን ፍራንሲስኮ የቬጅ ቀን በማወጅ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ከተማ ሆነች። የሳን ፍራንሲስኮ የተቆጣጣሪ ቦርድ ምግብ ቤቶችን፣ ግሮሰሪዎችንና ት/ቤቶችን በየሳምንቱ ሰኞ የስጋ-አልባ አገልግሎታቸውን እንዲጨምሩ የሚያበረታታውን ውሳኔ በአንድ ድምጽ አጽድቀዋል።137
[የዩኤስኤ የትምህትምክር ቤትና የሰራተኞች ኮመቴ የት/ቤት ምሳና የኦርጋኒክ ቪጋን የሙከራ መርሃ-ግብር ህግ አወጣ።]
ፎርሞሳ (ታይዋን)
በፎርሞሳ ፕሬዝዳንቱ፣ ማ ዪንግ-ጁ አትክልት መብላትና ስጋን መቀነስ የሙቀት-አማቂ ልቀት መቀነሻ ዋነኛው የህይወት ዘዴ እንደሆነ ገለጸዋል።
ለእንድ የፖለቲካ መሪ ይህን መናገሩ በእውነት ጉብዘናና ትልቅ እርምጃ ነው። ባለቤቱም፣ የፎርምሳ ቀዳማዊት እመቤት አርኣያነቷን የገለጸችው እንዴት የአለም ሙቀት ማሰወገድ እንደሚቻል፣ ስጋ መብላትን መቀነስ፣ የበለጠ አትክልትና ፍራፍሬ መብላት የጋዝ ልቀቱን ለመቀነስ እንደሚረዳ የሚገልጸውን አንድ ጽሁፍ ጮክ ብላ ለልጆች በማንበብ ነበር።
ፕሬዝዳንት ማ ዪንግ-ጁና መላው የፕሬዝደንቱ ጽ/ቤት ካርቦንዳዮክሳድን ለመቀነስ የሚረዱ እንደ በአካባቢው የተመረቱትን ምርቶች መመገብን፣ የበለጠ አትክልቶችን መመገብና ስጋን መቀነስ የመሳሰሉ እርምጃዎች ያካተተውን አዋጅ በፊረማቸው አጽድቀዋል።138
በመጨረሽም ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ የፎርሞሳ (ታይዋን) ህዝብ ስጋን ለመቀነስ በፊርማቸው ቃል ገብተዋል።