• እዝሎች
      • እዝሎች

         
        የባህር ከፍታ መጨመርና አለማቀፍ ተጽእኖው

        ትንንሾቹ የደስት መንግስታት ብቻ አይደሉም ስለባህር ከፍታ መጨመር መቸነቅ ያለባቸው፡፡ ከ70 በመቶ በላይ የአለም ህዝብ የሞኖረው በባህር ዳርቻዎች አካባቢ ስለሆነ ከ15 11ዱ የአለም ትላልቅ ከተሞች ባህር-ገብ ናቸው፡፡ በ20ክ/ዘ ውስጥ የባህር ከፍታ በ10ና በ20 ሴ.ሜ (4-8 ኢንች) ጨምሯል፡፡

        21ኛው ክ/ዘ የባህር ከፍታ ከ9 እስከ 88 ሴ.ሜ እንደሚጨምር አይፒሲሲ ገምቶ ነበር፡፡ ይህ መለስተኛ የባህር ከፍታ መጨመር እንኳን መናጋት ያስከትላል፡፡ የባህር ዳርቻዎች በጎርፍና ማዕበል መጎዳት፣ የባህር ዳሪርዎች መሸርሸር፣ የውሃ በጨው መበከል፣ የባህር ዳርቻዎች ለም መሬቶችና ደሴቶች በጎርፍ መመታት፣ እና የባህረ-ገቦች በጨው መጠቃት በትንሽ የባህር ከፍታ መጨመር የሚከሰቱ እውነታዎች ናቸው፡፡

        አንድ አስፈሪ እውነታ የግሪንላንድ የበረዶ ንጣፍ የመቅለጥ አጋጣሚ ነው፡፡ እነንደ አይፒሲሲ፣ "የአየር ንብረት ሞዴሎች እንደሚያመለክቱት የግሪንላንድ አካባቢ ሙቀት መጨመር የአለም አቀፉን አማካይ ሶስት እጥፍ ሊደርስ ይችላል፡፡ የበረዶንጣፍ ሞዴሎች የሚተነብዩት የአካባቢው ሙቀት መጨመር በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለ ከሴ.ግ [5.4°] በላይ ሊደርስ ይችላል፤ ይህ የግሪንላንድን የበረዶው ንጣፍ በሙሉ እንዲቀልጥና የባህር ከፍታው እስከ 7 ሜትር ሊልል ይችላል፡፡" (የአይፒሲሲ 3 የዳሰሳ ጥንቅር ሪፖርት፣ ለፖሊሲ አውጪዎች የቀረበ)፡፡

        በሚገባ ሙቀት-አማቂ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ካልቻልን ግሪንላንድና ምዕራባዊ አንታርክቲክ የበረዶ ንጣፎች የተነሳ አለም የ13ሜተር (43ጫማ) ያህል የባህር ከፍታ መጨመር ሊጋረጥባት ይችላል፡፡ በጣም ዝቀተኛ የባህር ከፍታ መጨመር ብቻ ትልቅ የኢኮኖሞና ሰብኣዊ አደጋ ያሰከትላል፡፡ የሚከተሉት ዝርዝሮች በሚከሰተው የባህር ከፍታ መጨመር ሊደርስ የሚችሉ ናቸው፡

        ቢሊዮን ዶላሮች በማጣጣም ተግባር ላይ ማጥፋት - እርሱም ከተቻለ ነው፡፡ አንደ በቅርቡ የተደረገ ጥናት በአሜሪካ የአንድ ሜትር የባህር ከፍታ መ\ጨመር ለማጣጣም $156 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ (3% አመታዊ ምርት) እንደሚጠይቅ ግምቱን አስቀምጧል፡፡

         የአንድ ሜትር የባህር ከፍታ መ\ጨመር ጥቂት የማይባሉ እንደ ማልዲቭስ የመሳሰሉትን የደሴት አገሮችን ያሰምጣል፡፡ የፓስፊክ ደሴቷን አገር፣ ኪሪባቲን ከፈጠሯት ደሴቶች ሁለቱ በማእበል ተመተዋል፡፡ ሙቀት መጨመሩ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠለ እንደ ለንደን፣ ባንኮክና ኒውዮርክ ያሉ ከተሞች ባህር ውስጥ በመግባት ሚሊዮኖችን በማፈናቀል፣ እና ግዙፍ የኢኮኖሚ ውድመትንም ይከተላል፡፡

        የውቅያኖሶች ከፍታ መጨመር የገጸ-ምድርም ሆነ የከርሰ-ምድር ውሃን ለብክለት በመዳረግ፣ አሁን ያለውን የአለምን የውሃ አቅርቦት እጥረት ያባብሳል፡፡

        በባህር ዳርቻዎች አካባቢ ሚገኙ የገጠሩ ህዝብና እርሻዎቻቸው (በተለይ የሩዝ) በመጥለቅለቅ ይወድማሉ፡፡
        (ምንጭ: http://www.greenpeace.org/international/campaigns/climate-change/impacts/sea_level_rise/)


        ተጨማሪ የአለማቀፋዊ የበረዶ ግግሮች ሽሽት
        የአለም የፍራፍሬና አትክልት ቅርጫት ለሆነው ለካሊፎርኒያ ማእከላዊ ሸለቆ የመስኖ ውሃ የሚሰጠው በሴራ ኔቫዳ ተራራ ፣ አሜሪከ ላይ የተከማቸው በረዶ፣ ባፈው ቢራ መቅለጥ መጀመሩና በክፍለ-ዘመኑ ማክተሚየ ከ30-70 በመቶ እንደሚቀንስ ይገመታል፡፡
        (ምንጭhttp://www.sierranevadaalliance.org/programs/db/pics/1133215435_14399.f_pdf.pdf  Sierra Climate Change Toolkit 2nd edition, Sierra Nevada Alliance)

         

        ከአፍሪካ በከፍታው የመጀመሪያ በሆነው የኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የሚገኘው በረዶማ ሜዳዎች ባለፈው ምእተ-ዓመት ከ80% በላይ ተመናምኗል፣ ከ1989 እስከ 2000 ብቻ በ33% ቀንሰል፡፡ (ምንጭ: "ቶምፕሰን ለ. ጂ. ሞስሊ - ቶምፕሰን  ኢ. ዴቪስ ኤም.ኢ. ሀንደርሰን ኬኤ፣ ብሬቸር ኤች ኤች፣ ዛጎሮድኖቭ ቪኤስ፣ ማሽዮታ ቲኤ፣ ሊን ፒኤን፣ ሚካሌንኮ ቪኤን፣ ሀርዲ ዶ/ር፣ ቢር ጄ. 2002. የኪሊማንጃሮ በረዶ መሰረት መዝገቦች፡ የሆሎሴን የሀሩራዊ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መረጃ፤  ሳይንስ 298: 589–593.http://bprc.osu.edu/Icecore/589.pdf"

         
        የአለማቀፈዊው ሙቀት መጨመር የቻይናን የበረዶ ግግርሮች በአመት በ7% እንዲመናመን ያደርጋል፤ ይህም በ300 ሚሊዮን በሚሆነው ውሃውን በሚጠቀመው ህዝበ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡(ምንጭ: "በበረዶ የተሸፈነው የአለም ማማ ወደ በረሃነት መለወጥ፣ በጆፍሬይ ሊን ግነቦት 08 2006,ኢንዴፔንደንት, http://www.countercurrents.org/cc-lean080506.htm)

        ከ1930ዎቹ ጀምሮ በረዶማ የተራራዎች በመካከለኛው እስያ በ35-50% ሲቀንሱ እንዲሁም  ሌሎች በመቶ የሚቆተሩ አነስተኛ የበረዶ ግግሮች ጠፍተዋል፡(ምንጭ: http://www.unep.org/pdf/ ABCSummaryFinal.pdf  የተመድ የአካባቢ ጥበቃ የከባቢ አየር ቡናማ ዳመናዎች፣ በእሲያ ላይ ያተኮረ ክልላዊ የዳሰሳ ሪፖረት 2008)

        አፈንጋጭ የአለም አየር ጠባይ ሁኔታ

        2010 በጣም ሞቃታማ አመት ተብሎ የተመዘገበ ነው፡

        በተመድ የብሄራዊ የስነ-ውቅያኖስና ከባቢ አየር አስተዳደር (NOAA) የአየር ንብረት ሳይንቲስቶች ግንዛቤ ከሆነ ይህ አመት በታሪክ ውስጥ በሞቃታማቱ የተመዘገበው ነው ለመባል በመንገድ ላይ ነው፡፡

        በታሪክ ውስጥ የሃምሌው የሙቀት መጠን ሁለተኛው የተመዘገበ ትልቁ ሲሆን፣ የመጋቢት፣ የሚያዚያ፣ የግንቦትና የሰኔ የተመዘገቡ ከፍተኞቹ  የሙቀት መጠኖች ነበሩ፡፡

        በሰኔ 2010 የኖኣው (NOAA) የብሄራዊ አየር ንብረት መረጃ ማዕከል፣ አቶ ዴቪድ ኤስተርሊንግም በበኩሉ በመላው አለም የሚገኙ የመሬት አካላት ባልተጠበቀ ሁኔታ ሞቃታማ እንደነበሩ አስተውል፡፡

        ከሁሉም በላይ 17 አገሮች፣ ከ19% የአለም የመሬት ስፋት የሚሆነውን የያዙና፣ በሰሜን የሚገኙት ማለትም እንደ ፍንላንድና ሩሲያ የመሳሰሉት አገሮች አዳዲስ፣ በአብዛኛውም አስጨናቂ የሆነ መቀት አስመዝግበዋል፡፡

        በዚህ እጅግ በጣም ግዙፉ የገጸ-ምድር መጠን ላይ ነው ፕላኔያልተጠበቀ ከፍተኛ ሙቀት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለማስተናገድ የተገደደችው፡፡ እነዚህን አስደንጋጭ አሃዞችን በሚመለከት፣ አሜሪካዊው የብሄራዊ በረዶና መረጃ መዕከል ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ማርክ ሴሬዝ እንዲህ ይላሉ፡ ቁም ነገሩ የአለም ሙቀት መጨመር አለመገታቱ ነው፡፡

        ቶ ኬቪን ትሬንበርዝ፣ አሜሪካዊው የብሄራዊ የከባቢ አየር ምርምር ማዕከሉ የትንተና ክፍል ሃላፊ በበኩሉ ለተጨማሪ የሀሩር ውሽንፈርና ማዕበል መዘጋጀት እንዳለብን አስጠንቅቋል፣ እንዲህ በማለት፣

        ባለፈው ጊዜ ሙቀቱ እነዲሁ፣ ቀደም ሲል ያልተመዘገበ ነበር እነ ካቲሪናና ሪታን ያስከተለው ማዕበል/ሁሪኬን፣ እናም የምንለው ነገር ጠፍቶን ነበር፡፡ በዚህ አመት በአትላንቲክ የሙቀቱ መጠን በ2005 ከነበረው የበለጠ ነው፡፡

        (ምንጭ: http://solveclimate.com/blog/20100816/most-ever-heat-record-temperatures-19-percent-earths-surface

        http://news.discovery.com/earth/heat-record-climate-change.html

        http://www.washingtonpost.com/wp-dyn/content/article/2010/08/13/AR2010081306090.html

        http://www.accuweather.com/blogs/news/story/35632/hottest-year-on-record-so-far.asp

        http://green.blogs.nytimes.com/2010/08/17/weather-extremes-and-climate-change

         

        በሩሲያ፡                              

        2010 በሩሲያ ከፍተኛ ሙቀት ተከስቶ በሞስኮ በሰኔ ወር ብቻ 14340 ሰዎች ለሞት ተዳረገዋል፡፡ በግማሽ ምዕተ-አመት ውስጥ በሩሲያ የአውሮፓዊ ክፍሙቀቱ አስከፊ ድርቅ ማባስከተል፣ የሩሲያ መንግስት ስንዴን ወደ ውጪ መላክ እንዲያቋርጥ አስገደደ፡፡ ሙቀቱ በተራው  ሩሲያ ከፍተኛ የእሳት አደጋ በሩሲያ የአውሮፓዊ ክፍ አስከተለ፡፡

        (ምንጭ: http://climateprogress.org/2010/08/07/russian-heat-wave-drought-soil-moisture-wheat)


        ዋና ዋና የዱር እሳት አደጋዎች

        በአውስትራሊያ

        ደቡብ አውስትራሊያ የተለየ ሙቀትና ከባድ ዝናብ ስለወረደበት ሰሜኑን ለጎርፍ አጋለጠው፣ ምስራቁ ደግሞ እሳቶችንና ጎርፎችን ማስተናገድ ተገደደ፡፡ አንዴ በመቶ አመት ነበረ የሙቀት ወላፋን በሳመንቱ መገባደጃ ላይ የሙቀት መጠኑን አግዝፎና በድረቅ ንፋስ ታጅቦ ከተፍ በማለት በሃያ አምስት አመታት ውስጥ ያልታየ የዱር እሳት ወለደ፡፡

        (ምንጭ: http://www.google.com/hostednews/afp/article/ALeqM5gyUztdckUqzd_SFg9jClfRmHlWEg)

        በሩሲያ

        በነሃሴ ወር 2010 ሩሲያ የደንና ፒት እሳት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ አብዛኛውን የአውሮፓ ክፍሏን ማጥቃት ቀጠለ፣ ይህም ሰባት ክፍለ-ግዛቶችን የአስቸይ የጊዜ አዋጅ እንዲያወጡ አስገደደ፡፡ በጠቅላላው 520 እሳቶች በ188,525 ሄክታር (465,000 ኤከር) የሚሸፍነ የሩሲያን ምድር ለበለበ፡፡ ወደ 650,000ሄክታር ሚጠጋ መሬት ተቃጠለ፡፡

        ዋና ዋና የአለም የጎርፍ አደጋዎቸ

        በቻይና

        2010 ሰፋፊ የቻይና ክፍሎች በበጋው ዝናብ በመመታት አአስርተ-አመታት ያልታያ አስከፊ ጎርፍ በማስከተል አስፈሪ ናደዎችን በመውለድ በርካታ ወንዞች በአፍ-ገደባቸው ድረስ ሞሉ፡፡ በጎርፉ 1.4-ሚሊዮን ቤቶች ሲያወድም፣275-ቢሊዮን ዩኣን (41-ዶላር) የሚገመት የኢኮኖሚ ጥፋት አስከትሏል፡፡

        ሰሜናዊ ምስራበአስከፊ ሁኔታ የተመታና ከተሞችን ያጥለቀለቀ ሲሆን፣ በሰሜን ኮሪያን የሚያዋስኑ ወንዞች ከፍታቸው በመጨመር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ ሁለቱንም አገሮች ለሚያሰጋ አደጋ ጋርል፡፡

        (ምንጭ: http://www.google.com/hostednews/afp/article/ALeqM5juX85JVgP2tsnqUSZxNgLuXejxDw)

        በፓኪስታን

        በፓኪስታን የ2010 ጎርፍ በሞንሱኑ የሃምሌ ወር ዝናብ ተከትሎ የተከሰተ ነበር፡፡ ከ2,000 በላይ ሰዎች ገድሎ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቤቶችን አጠፋ፡፡ በተጨማሪም 20 ሚሊዮን ሰዎች ተጎድተዋል ወይም ቤት አልባ ሆነዋል፡፡
        (ምነጭ፡ http://en.wikipedia.org/wiki/2010_Pakistan_floods)

         

        ዋና ዋና የአለም የርዕደ-መሬት አደጋዎቸ

        በቻይና
        ግንቦተ 2008 መጠኑ 8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በሲሹኣን ክፍለ-ግዛት ደርሶ በደቡብምስራቅ ቻይና ሰፊ የሆነ መሬት ሲመታ፣ ከ87,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል ወይም የደረሱበት አልታወቀም፡፡

        ነሃሴ 2009 መጠኑ 6.2 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ጎልሙድን በመምታት የመሬት መናድንና የ30 bytocene መደርመስ አስከተለ፡፡

        ሚያዚያ 2010 መጠኑ 6.9 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በምዕራብ ቻይና ደርሶ ቢያንስ 589 ሲገደሉ ከ10,000 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል፡፡
        (ምንጭ:  http://www.telegraph.co.uk/news/worldnews/asia/china/7588401/China-earthquake-kills-hundreds.html)


        በሌሎች የአለም ክፍሎች

        በጥር ወር 2010 ሶስት ጠንካራ ርዕደ-መረት የሰለሞን ደሴቶችን በመምታት የመታ ሲሆን፣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ደግሞ መጠኑ 7.0 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ሀይቲን በመዘርጋት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ቤት አልባ በማድረግ ከ230, 000 ሰዎችን በመግደል ሌሎች 300,000 ለጉዳት ዳረገ፡፡ ኮሪን ጃፓንም ተመተው ነበር፡፡ ከዚያም ቺሊ መጠኑ 8.8 በሆነ ጉልበት (በጠንካራነቱ የተመዘገበ መጠን) ተመታች፡፡ ተጨማሪ ርዕደ-መሬቶች በጃፓን፣ በሜክሲኮ፣ በሱመትራና በቅርቡም በምዕራብ ቻይና ተከተለ፡፡ እስከ ሚያዚያ (2010) ከዚህ ተፈጥዊ ክስተት የሞት መጠኑ 250,000 ይደርሳል፡፡

        (ምንጭ: http://www.businessweek.com/news/2010-04-15/killer-quakes-on-rise-with-cities-on-fault-lines-roger-bilham.html)


        የአለም ምግብ እጥረት

        ሊተነበይ የማይችል የአየር ሁኔታ የምግብ አቅርቦትን መሰረት ያናጋል

        ማክሰኞ፣ መስከረም 7 ቀን 2010 የሲሪላንካው አለማቀፋዊ የውሃ አመራር ተቋም (IWMI) በአለም የውሃ ሳምንት በስቶክሆልም፣ ስዊድን ለአማቀፍ የሳይንቲቶች ጉባኤ ላይ ሪፖርት አቅርቦ ነበር፡፡ በዚህ ሪፖረቱ የአየር ንብረት ለውጡ የተዛባ ዝናብ በማምጣት ላይ መሆኑን ሲያስጠነቅቀ፣ ወቅቱን ያልጠበቀና መጠኑም ተለዋዋጭ የመሆኑ ጉዳይ እየጨመረ የምግብ ዋስትናና ለኢኮኖሚ እድገትም እንቅፋት እየሆነ ይገኛል ብሏል፡፡

        ይህም የሆነው በከፊል በእስያ በግምት 66% የሚሆነው ሰብል የሚመረተው በመስኖ ሳይሆን በዝናብ በመሆኑ ነው፣ በአፍሪካ ደግም 94%ው በዝናብ ነው፡፡ የሰሞኑን ለየት ያለ ደረቅ ሁኔታን በተመለከተ አውዳሚው የሩሲያው ሰደድ አሳትና በተቀራኒው የፓኪስታኑ አጥፊ ጎርፍ፣ የህንዱ የሳይንስና አካባቢ ሃላፊ የሆኑት፣ ሱሪታ ናሬን እንዲህ ይላሉ፣ ወብዙ ውሃ ወደ ማግኘቱ እየገባን ነው፣ ተጨማሪ የዝናብ ቀናትም ሊኖረን ነው፣ ይህ ግን አስተማመኝ አይደለም፣ ተለዋዋጭ ነው፣ በመጨረሻም ወደ ድርቅና ወደ ጎርፍ ሊመራን ይችላል፡፡”  (ምንጭ፡ http://www.france24.com/en/20100907-erratic-global-weather-threatens-food-security)

         

         አለማቀፋዊ የሙቀት መጨመር፡ ዲግሪ-በዲግሪ በመከተል

        አሁን ባለው ቀመር የአለም ሙቀት መጨመር ከቀጠለ ከምድረ-ገጽ የመጥፋት አደጋ የጋረጥብናል፡፡ ስለዚህ መሬት በመሞቀ ከቀጠለች ምን ይፈጠራል? የዲግሪ-በዲግሪ መመሪያው እነሆ፣ ከስድስት ዲግሪ፡ በማርክ ሊናስ ተጽፎ በናሽናል ጂኦግራፊ፣ ጥር 22, 2008 በወጣው፣ በሞቃቷ ፕላኔት ላይ የወደፊቱ ሯችን፣ ከሚለው ጽሁፍ የተወሰደ (ሊናስ መ. 2007)

        10 ሴ መጨመር

        ከበረዶ-የጸዳ ባህር መቀት በመሳብ የአለም ሙቀት መቸመርን ያፋጥናል፡ ውሃ ከሲሶው የአለማችን ክፍል ይጠፋል፣ አዚቅተኛ ስፍረዎች ያሉ የባህር ዳርቻዎች ይጥቅለቀለቃሉ፤

                  10 ሴ የአለም ሙቀት መጨመር መግታት እድሉ ዜሮ ነው፤

         

        20 ሴ መጨመር

        የአውሮፓዊያን በገዳይ ሙቀት መመታት፣ ደኖች በእሳት ይጋያሉ፣ የተጎዱ/የተጨናነቁ እጽዋቶች ካርቦን ከመውሰድ ይልቅ ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ ይጀምራሉ፣ የፍጥረታት ሲሶው የመክሰም አደጋን ጋፈጣሉ፣

                  20 ሴ የአለም ሙቀት መጨመር መግታት እድሉ 93% ነው፤ ይህ ሊሆን የሚችለው የሙቀት-አማቂ ጋዞችን ልቀት በ60% በሚቀጥሉት አስር አመታት ውስጥ መቀነስ ከተቻለ ብቻ ነው፤

        30 ሴ መጨመር

        ከእጹዋትና ከአፈር የካርቦን ልቀቱ የአለምን ሙቀት መጨመር ያፋጥነዋል፣ የአማዞን የዝናብ ደን መውደም፣ በባህር ዳርቻዎች የሚገኙ ከተሞች በከፍተኛ የማዕበል/ሁሪኬን መመታት፣ የአፍሪካ መራብ፣

        30 ሴ የአለም ሙቀት መጨመር መግታት እድሉ የመነመነ ነው፤ በተለይ የሙቀት ጭማሬው 20 ሴ ከደረሰና የካርቦን አዙርቱ በእጽዋትና አፈር መደገር ከጀመረ

        40 ሴ መጨመር

        ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የግግር መሬት/ፓርማፍሮስት መቅለጥ የአለም ሙቀት መጨመርን ማቆም አስቸጋሪ ያደርገዋል፣ ታላ ብሪታኒያ በጎርፍ ምክኒያት የሰው መኖሪያነያበቃል፣ የሜዲተራኒያ አካባቢዎች ይወድማሉ፣

        40 ሴ የአለም ሙቀት መጨመር መግታት እድሉ የመነመነ ነው፤ በተለይ የሙቀት ጭማሬው 30 ሴ ከደረሰና የካርቦን አዙርቱ በእጽዋትና አፈር መደገር ከጀመረና የግግር መሬት/ፓርማፍሮስት ቀልጦ ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ

         

        50 ሴ መጨመር

        ከውቅያኖሰ ወለል የሚመነቸው ሚቴን የአለም ሙቀት መጨመርን ያፋጥናል፣ የበረዶ ሽፋኖች ከሁለቱም ዋልታዎች ይጠፋሉ፣ የሰው ልጅ በምግብ ፍለጋ ይሰደዳል፣ እንደ እንስሳትም ለመኖር ይጥራል፣

        50 ሴ የአለም ሙቀት መጨመር መግታት እድሉ እጅግ የመነመነ ነው፤ በተለይ የሙቀት ጭማሬው 40 ሴ ደርሶ በውቅያኖሶች ወለል ስር ተከማችቶ የሚገኘው ሚቴን ካመለጠ፤

         

        60 ሴ መጨመር

        የምድር ላይ ኑሮ እንደ ጥፋት ውሃው በማዕበል ያከትማል፣በጎርፍ  መትለቅለቅና መዋጥ፣ የሃይድሮጂን ጋዚና የሚቴን የእሳት ሶች ከአቶሚክ ቦምቦች ጋር በአለም ዙሪያ መወዳደር፣ ፈንገስ ብቻ የሚተርፍ ይሆናል፣

        60 ሴ የአለም ሙቀት መጨመር መግታት እድሉ እጅግ ዜሮ ነው፤ በተለይ የሙቀት ጭማሬው 50 ሴ ካለፈ፣ በዚያ ጊዜ መጋቢዎቹ ሁሉ ከቁትትር ውጪ ይሆናሉ፡፡

         

          

        በእንስሳት ቆሻሻ መበከል

        በአሜሪካ

        በማዕካላዊ ምዕራብ ወደ 13% የሚሆነው የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶች ከተፈቀደው መጠን በላይ ናይትሬት ከማዳበሪያና ከእንስሳት ቆሻሻ ወደ ውሃው ይፈሳል ወይም በማምለጥ ወደ ጉድጓዶቹ ይገባል፡፡

        በ2001 የአሜሪካው የአካባቢ ጥበቃ ድርጂት (አጥድ/ EPA) ለነዋሪዎቹ ውሃ እንዲያቀርቡ የታሸገ ውሃ አምስት ውሃውን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን ያስገደደው እርሶቹ የመተጥ ውሃውን በመበከላቸው ነበር፡፡

        አንድ በ1997 የተደረገ ጥናት 82% የሞሆኑቱ የእንስሳት የእርሻ ስራዎች መሬቱ መሸከም ከሚችለው በላይ ናትሮጂን ሲያመርቱ፣ ከመሬቱ መያዝ አቅም 64% በላይ ፎስፈረስ የሚለቀው ደግሞ የዶሮ እርባታው ነበር፡፡

        በቅርቡ የተለቀቀው የቼሳፒክ ቤይ ድርጂት ሪፖርት የዶሮ የሚወጣው ቆሻሻ ዋነኛው የሰላጤው በካይ ነው ሲል ደምድመዋል፡፡

        (ምንጭ፡ http://www.hsus.org/farm/resources/pubs/gve/for_the_environment.html)

         

        የእንስሳትና የሰዎች የፍቅር ባህርያት (ፍ.ባ)
        በሁኔታ ላይ ያልተንተራሰ፣የፍቅር ባህርይ፡ ከባልና ሚስት፣ ከእናትና ልጅ፣ ለሁሉም ፈጥረታት ያለን ፍቅር  ነው፡፡ ረጂያችንንም ሆነ እንግዳ ወይም ጠላት እኛ መስዋእት ለመክፈልና ለመርዳት ዝግጁ ነን፡፡” —ሱፕሪየም ማስተር ቺንግ ሃይ   

        ከዚህ በታች የቀረበው የጥቂት ወካይ እንስሳትና ሰዎች የፍቅር ባህርያት (ፍ.ባ) መቶኛ ለሱፕሪየም ማስተር ቺንግ ሃይ ከላይ በተሰጣት መሰረት ያካፈለችን ግንዛቤዋ ነው፡

                                      የቤት እንሰሰሳት:  80% እስከ 300% ነው፤

        ውሻ                           110%                  አሳማ              120%

        ዶሮ                              90%                  ጎሽ                 110%

        ፈረስ                           180%

                                    
                                      የዱር አራዊት፡ ከ30% እስከ 300% ነው፤

        የዱር ጦጣ                   100%                  ድብ               110%

        ዝሆን                          100%                  ዌል                300%

        ላም                            300%                  ዶልፊን            110%

        ነብር                             20%                  አንበሳ               21%

                                      የሰው ልጅ: በአማካይ 20% ነው

                                በፕላኔ ላይ ከፍተኛው:  90%                    ዝቅተኛው:  5%

        ቅዱሳን/መምህራን: በመቶ ሺ (1000) % እና እነዚህ ሰዎች አይደሉም!

         
        የተቀደሰ ባህርይና የፍቅር ባህርይ ሁሉም አስፈላጊ ናቸው፣ የችሎታ ባህርይ አስፈላጊ ወይም አስፈላጊ ላይሆን ይችላል! ይህን የፍቅር ባህርይ ልናዳብረው ይገባል፡፡ የሰው ልጅ በፕላኔ ላይ ውድ ጊዜውን (አጭር ጊዜ) እንዴት እንደሚያሳልፍ/እንደሚጠቀምበት ሊያጤን ይገባል፡፡

         

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *