የታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ አጭር የህይወት ታሪክ
ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ዘርና ብሄራዊ ወሰን የማይገድበው የሰው ልጅ ፍቅርና እንክብካቤ ያላት እውቅ የአለማችን በጎ ኣድራጊ፣ የአካባቢ ተቆርቋሪ፣ ጸሃፊ፣ የስነጥበብ ሰው፣ ዲዛይነር፣ ሙዝቀኛ፣ የፊልም ዳይሬክተርና የመንፈሳዊ መምህርት ናት። ከ1980ዎቹ መጀመሪያ ጀምራ ከዋናዎቹ እጅግ ቆራጥ የምድራችን የስነምህዳር ፋናወጊዎች፣ አካባቢንና ብዝሃ- ህይወትን ተንከባካቢ፣ ደን አስፋፊና ዘላቂ ህይወት አራማጅና በተለይም ለአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ፈጣንና ውጤታማ መፍትሄ የሆነውን የኦርጋኒክ ቪጋን አመጋገብን ያስተዋወቀች ፍና ወጊ ናት።
በማያወላውልና በቆራጥ ውሳኔዋ የጸናችው ታላቋ መምህርት ምድርን ሊያጠፋ ባንዣበበውና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የአየር ንብረት ቀውስና በቪጋን መፍትሄ ላይ አለምን ለማንቃት ጊዜዋንና ሀብቷን በመሰዋት ላይ ትገኛለች፡፡ ከ2006 እስከ 2008 ድረስ አማራጭ ኑሮንና የአስቸኳይ ጊዜ የአለም ሙቀት መጨመር SOS global-warming-awareness ንቃት የዘመቻ ጥሪን በማወጅና በፍጥነት በአለም ላይ በመስፋፋት ላይ የሚገኘውን የፍቅር ጎጆ (Loving Hut) የተባለ በራሷ የተነሳሳ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ አለም አቀፋዊ ቪጋን ምግብ ቤቶችን በታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ አለም አቀፋዊ ማህበር አጋዥነት ለመክፈት ችላለች፡፡ የዜና መጽሄት ታሳትማለች፣ መጽሃፍት ትጽፋለች፣ በ2005 The Real Heroes ዘሪል ሄሮስ የተባለ ቬጂታሪያን ጥናታዊ ፊልም አዘጋጅታለች፣ ዘ ኪንግ & ኮ (The King & Co) የተባለ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ አዘጋጅታለች፣ በርካታ አለም አቀፋዊ የአየር ንብረት ኮንፈረንሶችን በማነሳሳት አለምን የሚሸፍን 24/7 የሚሰራ ሳተላይት፣ በሱፕሪም ማስተር ቴሌቪዥን (Supreme Master Television) እንዲሰራጭ አድርጋለች። ይህ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ አጠቃላይ የአየር ንብረት ዘገባዎችን፣ የቪጋን አመጋገብንና ሌሎች ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ርእሶችን ያሰራጫል፡፡ በዚህ ሳቢያ “ፕላኔቷን ለመታደግ ቬጅ ሁን፣ አረንጓዴነትን አራምድ” የተባለው መፈክሯ በአለም አካባቢ በመሰራጨት የሰው ልጅ በማነሳሳት ጤናማ፣ ዘላቂ የቪጋን ህይወት ዘይቤና ወደ ከፍተኛ የሰላምና ሚዛናዊ ደረጃ የሚያሸጋግረውን ኑሮ እንዲቀበል የበኩሉን አስተዋጽ በማበርከት ላይ ይገኛል።
ደግሞም ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ፣ የውስጥ መልካምነታችንና ለፍጥረታት ሁሉ ያለንን ፍቅር እንድናስታውስ በመልካም አርኣያነቷ ታሳስበናለች። በጥልቅ መንፈሳዊ ግንዛቤዋ የሰው ልጆችን የስቃይ መሰረታዊ ምንጭ፣ ማህበራዊ አለመግባባትና የአካባቢ ውድመት በሌሎች ፍጥረታት ላይ ንጹሃን እንሰሳትን ጨምሮ የምናደርሰው ትንኮሳና ግፍ መሆኑን ለይታ እንድታወጣ አስችሏታል። ከሩህሩህነቷ በመነሳት አቅምና ድምጽ አልባ ለሆኑት ፍጥረታት ዘ በርድስ ኢን ማይ ላይፍ፣ ዘ ዶግስ ኢን ማይ ላይፍና ዘ ኖብል ዋይልድስ (The Birds in My Life, The Dogs in My Life, and The Noble Wilds) የተሰኙ በሽያጭ በአለም ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ የያዙትን መጻህፍት አበርክታለች ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ። እነዚህ እንቁ የጽሁፍ ስራዎቿ ወደ በርካታ የአለም ቋንቋዎች ተተርጉመው የእንሰሳትንን መለኮታዊ ፍጥረትና ገደብ የለሽ ፍቅር የሚያጎሉ ጥልቅ ሀሳብና ስሜታቸውን አለም እንዲረዳ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ የተወለደችው በመካከለኛው ኣውላክ (ቬትናም) ውስጥ ሲሆን፣ ትምህርቷን በአውሮፓ ተከታትላ በቀይ መስቀል ድርጅት ውስጥ አገልግላለች። የሰው ልጅ ስቃይ በሁሉም የአለም ማእዘናት መኖሩን የተገነዘበችው በዚህ ጊዜ ነበር። ከዚያም በህይወቷ ስትመኘው የነበረውን የሰው ልጆች ስቃይ መድህን የመፈለግና ማሳካት ግቧን ሰነቀች። ከዚያም የመንፈሳዊ ንቃት ጉዞዋን ወደ ሂማለያ አቀናች። በመጨረሻም የመለኮታዊ ሃይል በውስጣዊ ብርሃንና ድምጽ ተላልፎላት ተቀበለች። በኋላም የኳን ኢን ዘዴ ብላ ሰየመችው። ከተወሰነ የልምምድ ጊዜ በኋላ፣ ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ታላቁን መገለጽ ተጎናጸፈች። ወዲያው ከሂማለያ መልስ በአካባቢዋ በሚገኙ ሰዎች ጥያቄ ታላቋ መምህርት የኳን ኢን ጥበብን ማካፈል ጀመረች፣ ወደ ውስጣቸው እነዲመለከቱና መንፈሳዊ ታላቅነታቸውን እንዲያገኙ ተማሪዎቿን ማበረታታት ቀጠለች። ሳይቆይም እንድታስተምራቸው ከብዙ አገሮች ከአሜሪካ ከአውሮፓ ከእሲያ ከአውስትራሊያና ከአፍሪካ የግብዣ ጥሪዎች ይጎርፉላት ጀመረ። በተጨማሪም የታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ሩህሩህ ልብ በሌሎች ያልታደሉ ፍጥረታት እንክብካቤም ይገለጻል። ከጥበብ ስራዎቿ ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ የተቸገሩ የእግዚአብሄር ልጆችን በአደጋ ወቅት ደርሶ የበጎ ስራና የማጽናናት ተልእኮዋን እንድታከናውን አስችሏታል።
ለሰብኣዊ በጎ ስራዋ ምንም እውቅና ባትፈልግም እንኳን፣ የታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ በአለም ዙሪያ ከሚገኙ መንግስታትና የግል ድርጅቶች በርካታ ሽልማቶችን የአለም የሰላም ሽልማት፣ የአለም መንፈሳዊ መሪነት ሽልማት፣ የሰብኣዊ መብቶች ሽልማት፣ የአለም ሰብኣዊ ዜግነት ሽልማት፣ ለሰው ልጆች የላቀ ህዝባዊ አገልግሎት ሽልማት፣ የ2006 ጉሲ የሰላም ሽልማት፣ የሎሳንጅለስ የሙዚቃ ሳምንት የአድናቆት ሰርቲፍኬት፣ ለ27ኛው አመታዊ የቴሊ የ2006 ቀዳሚ የብር ሽልማት፣ ፕሬዝደንታዊ የንቁ ህይወት ዘይቤ ሽልማት ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከጆርጅ ቡሽና የ2010 የፕሬዝዳንት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሽልማት ከባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አግኝታለች።
በተጨማሪም ጥቅምት 25 እና የካቲት 22 እ.ኤ.ኣ.(October 25 and February 22) “የታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ቀን” ተብለው በአሜሪካ ውስጥ እንዲከበሩላት በሃዋይና በኢሊኖይስ የመንግስት ባለስልጣናት ታውጀዋል። በኢሊኖይሱ አዋጅ ላይ በርካታ የደስታ መልእክቶች የቀድሞዎቹን የአሜሪካ መሪዎች እነ ክሊንተን ቡሽና ሬገን ጨምሮ ተልከውላታል። የሰዎችና እንሰሳት የግል መልካም ተግባራት ለማድነቅና ሌሎች በመልካም አርአያነታቸውን እንዲነሳሱ ለማበረታታት አንጸባራቂ የአለም ሽልማት (Shining World Awards series) በታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ተቋቁሟል። ይህ ሽልማት ለሰዎችና እንስሳት የሚገባቸውን የጀግንነት፣ የፍቅር፣ የመሪነት፣ የብርቱነት ወይም የአዋቂነት (intelligence) እውቅና ይሰጣል።
ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ለራሴ ሳትል ሌሎችን ለማገልገል ህይወቷን የሰጠች ለተወዳጇ ፕላኔታችንና ለውድ ነዋሪዎቿ መልካም ቀጣይ ኑሮ ናት። በታሪክ ታላላቅ ባለራእዮች ነበሩ እናም ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይም የራሷን እንደሚከተለው ትገልጻለች “ህልም አለኝ። መላው አለም ሰላም እንዲሆን ኣልማለሁ። እኔ የማልመው ማንኛውም ግድያ እንዲቆም ነው። የማልመው ህጻናት ሁሉ በሰላምና በሚዛናዊነት እንዲራመዱ ነው። የማልመው ሁሉም አገሮች እጅ ለእጅ እንዲጨባበጡ፣ እርሰ በርስ እንዲጠባበቁና እንዲረዳዱ ነው። እኔ የማልመው ቆንጆዋ ፕላኔታችን እንዳትወድም ነው። ብዙ ብዙ ቢሊዮን፣ ብዙ ትሪሊዮን አመታትን ይጠይቃል ይህችን ፕላኔት ለመፍጠር፣ እናም ቆንጆና አስገራሚ ናት። ህልሜም እርሷ እንድትቀጥል ነው፣ ግን በሰላም በቁንጅናና በፍቅር።”
የዚህን አለም መሪዎችና መሪ ያልሆኑትንም፣ በጠቅላላው ህዝቡን በውነት እንዴት አቅፌኣቸው “ንቁ፣ ተነሱ ” ብዬ እንደምነግራቸው አላውቅም። ተቀብዬኣቸውና አቅፌኣቸው “ንቁ፣ አሁኑኑ ንቁ። ንቃ/ንቂ ፍቅሬ፣ ንቃ/ንቂ ጓዴ፣ ራስህን/ሽን ኣድን/ኣድኝ” ብዬ ልነግራቸው እፈልጋለሁ።