
የመረጃ ምንጭ፡ ፉወች፣ ኦርጋኒክ፡ የአየር ንብረት መድህን? የፉድወች ሪፖረት የሙቀት-አማቂ ጋዞች ጫና/ተጽእኖ በተለምዶ እራሻና በኦርጋኒክ እርሻ ላይ በጀርምን፣ ግንቦት 2009፥ ገጽ 10
ስጋ በሊታ ከተለምዶ እርሻ ጋር ሲነጻጸር
• ኦርጋኒክ [ስጋ ላይ የተመሰረተ] አመጋገብ 8% የሙቀት-አማቂ ጋዞችን ልቅት ይቀንሳል፣
• ከእንስሳት-ነጻ የሆነ፣ የቪጋን አመጋገብ የሚያመነጨው የሙቀት-አማቂ ጋዞች ከ1/7 ያነሰ ነው ከስጋ አመጋገበፀ
ጋር ሲነጻጸር፣ ይህ 86% ልቀት መቀነስ ማለት ነው፣
• የኦርጋኒክ ቪጋን አመጋገብ የሚያመነጨው 94% ያነሰ ልቀት ነው ከስጋ ተመጋቢ ጋር ሲነጻጸር፣
— የፉድወች ሪፖረት የሙቀት-አማቂ ጋዞች ጫና/ተጽእኖ በተለምዶ እራሻና በኦርጋኒክ እርሻ ላይ በጀርምን
[ስለዚህ] የቪጋን አመጋገብ የአረንጒዴዎች ሁሉ አረንጒዴ ፖሊሲ፣የአረንጒዴዎች ሁሉ አረንጒዴ ተግባር፣ እጅግ ርህራሄ የተሞላበት፣ እጅግ ጀግንነት የተላበሰ፣ህይወት አድን ተግባር ነው።
ምክኒያቱም ሚቴንን ከከባቢ አየር በማስወገድ ፕላኔቷን የማቀዝቀዝ ጉልህ ውጤት፣ ይህ የሚሆነው ወደ ኦርጋኒክ ቪጋን አመጋገብ ስንዛወረ ነው። ጎጂውን የሚቴን ልቀት ከከባቢ አየር ከማስወገድ በተጨማሪ ኦርጋኒክ የአስተራረስ ዘዴ 40% የሚሆነውን ካርቦን በመምጠጥ ወደ አፈሩ ይመልሰዋል። ስለዚህ ቬጅ መሆን ልቀትን በጉልህ ማስወገድ ብቻ ሳይሆን የበለጠ ካርቦንን ከከባቢ አየር ያስወግዳል።
በዚህ አካሄድ ምድርቷን ለመታደግ እተንቀሳቀሳለን። ምክኒያቱም ወደ ከእንስሳት-ነጻ የአመጋገብ መሸጋገር፣ በእንስሳት ላይ የምንፈጽመውነ ጭካኔ እንኳን ብንተወው፣ ሚቴንና ሌሎችን በካይ ጋዞችን ያስወግዳል፣ የፕላኔተዊ አደጋዎችን- ሱናሚ፣ ጎርፍ፣ ማእበል፡ ታይፉንና የመሬት መንሸራተትና መናድን፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ይቀለብሳል።
እንደ ውነቱ ከሆነ UNFCCC ሃለፊ፣አቶ ዪቮ ደ ቦር ሰኔ 2008 እንደገለጹት “ከሁሉም የተሻለው መፈፍትሄ ሀላችንም ቬጄታሪያን መሆን ነው።” ቪጋን ማለቱ ነው።
ቪጋን ሁን፡ እጅግ አረንጒዴማ የህይወት መንገድ
(ስጋ ማምረትን ማቆም) ከ$40 ትሪሊዮን የአለም ሙቀት መቀንሰ ወጪን በ80%ው ያድናል። ለምግብ ሰብል ማምረቻ የሚፈለገው መሬት 4.5 እጥፍ ያነስ ነው፣ 70% ንጹህ ውሃ ይቆጥባል፣ 80% የአማዞን የዝናብ ደን ከእንስሳት ግጦሽ ያደናል። የአለም ረሃብ ፍቱን መድህን ነው፣3.4 ቢሊዮን ሄክታር መሬት ነጻ ያደርጋል፣ በያመቱ 760-ሚሊዮን ቶን እህል ።(ግማሽ የአለም የእህል አቅርቦት ያህል) ነጻ ያደርጋል። ለስጋ ማምረት የሚውለውን አንድ-ሶስተኛ ያህለ የነዳጅ ዘይት ይቆጥባል፣ ከእንስሳት የሚመነጨውን ያልተጣራ የቆሻሻ ብከላ ይቀንሳል፣ ንጹህ አየር ያስገኛል፣ በያመቱ ከያንዳንዱ የአሜሪካ ቤት የሚወጣውን 4.5 ቶን የአየር ሙቀት-አማቂ ጋዝ ልቀት ያስቀራል፣ 80% የአለም የአየር ሙቀት መጨመርን ይቀንሳል። ዝርዝሩ ይቀጥላል።
በአሜሪካ የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ኦርጋኒክ እርሻ የላይኛውን የአፈረ ክፍል ይጠብቃል፣ የውሃ አካላትን ያጠራል፣ በመላው አለም ስራ ላይ ቢውል በያመቱ እስከ 40% የሚደርስ የካርቦንዳዮክሳይድ ልቀትን መውሰድ ይችላል። ይህ ለምድራችን ቀጥተኛ ጥቅም ነው።
ሌላው የቪጋን፣ የኦርጋኒክ እርሻ አገልግሎት እንደ የሰብል እህሎችን መቀያየርና የተፈጥሮ ማዳበሪዎችን ያሉትን ያጠቃልላል። ሰብልን መቀያየር ማለት የእራሻ መሬቱ በየወቅቱ በተለያየ እህል የሸፈናል ማለት ነው። ይህ አካሄድ ሰብሉን ጤናማ፣ የአፈሩንም ለምነት ይጠብቃል። ሌሎች ዘዴዎች እንደና አዳዲስ ዘዴዎች እንደ ሳያረሱ-የኦረጋኒክ እርሻ እርጥበቱን በመጠበቅና የመሬቱንም መከላት ለመቀነስ ይረዳል።
በአጠቃላይ ቪጋን፣ ኦረጋኒክ እርሻ ከተፈጥሮ ጋር ተዋዶና ተዋህዶ በመኖር ፕላኔቷንና ሁሉንም ፍጥረታት የሚንከባከብ ነው። ዘዴዎቹ በእርሻና በአካባቢ ጥበቃ መካከል ያለውን የተፈጥሮ ሚዛን እንዲጠበቅ ያደርጋሉ። የነዚህ ተግባራት በቴክኖሎጂ እየታገዙ ድምር ውጤታቸው የተዛባውን ሚዛን ለመመለስ ይረዳሉ።
የአካባቢ ምርትን መመገብና ኦረጋኒክ ስጋን መመገብ
የሚያስደንቀው ነገር፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የአካባቢ ምርትን መመገብ ቪጋንን መመገብ ያህል ጥሩ አይደሉም። ለምሳሌ የካርኔጂ ሜሎን ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች እንደገመቱት የቪጋን አመጋገብ ከአካባቢው 100% የስጋ ምርት ጋር ሲነጻጸር ከሰባት እጥፍ በላይ የጋዝ ልቀቱን ይቀንሳሉ። ስለዚህ ቪጋንን መመገብ ከአካባቢ ምርት የተሻለ ነው ማለት ነው።
በሌላ ጥናት በጀረመን የፉድወች የደረሰበት ግኝት ከስጋ ወደ ኦርጋኒክ ስጋ አመመጋገብ መቀየር 8% ብቻ የጋዝ ልቅት ሲያድን፣ ኦርጋኒክ-ወዳልሆነ አመጋገብ፣ ወደ ኦቪጋን አመጋገብ፣ ኦርጋኒክ ባይሆንም አመጋገብ መቀየር 86% ልቀቱን ይቀንሳል።102 ስለዚህ ፕላኔቷን ለመታደግ ቪጋን መሆን ነው።ኦርጋኒክ ባይሆን እንኳን! ኦርጋኒክ ጥሩ ነው፣ የአካባቢ ምርት ቆንጆ ነው፣ ነገር ግን የመጀመሪያው እርምጃችን ቢያንስ ቪጋን፣ ኦረጋኒክ ውይም ያልሆነ መከተል ነው።
ኦርጋኒክ ስጋ እንኳን የምህዳራችን ወዳጅ ፈጽሞ ሊሆን አይችልለም፣ ኦርጋኒቸ ካልሆነ ስጋ ምርት ጋር ሲነጻጸር የበለጠ መሬት ይፈልጋል፣ የበለጠ ሃይል ይጠይቃል። ይህንን ማመን ትችላላችሁን? ስለዚህ ኦርጋኒክ እንስሳትን ማርባት አይረዳም ማለት ነው። ቀጣይነት ያለው፣ ነጻ-ምርጫ፣ ኦረጋኒክ የዶሮ እርባታ፣ ለምሳሌ 20% የበለጠ ሃይልና 20% የበለጠና ከፍተኛ የሆን,ነ የአለም ሙቀት መጨመር ጫና ያስከትላል ከኦርጋኒክ-ካልሆነው ጋር ሲነጻጸር። ይህ በደንብ አስቡት። ስለዚሀ ተሳስተናል ማለትነው።