I. አለም የብዙሃን መገናኛን መልካም አገልግሎትና አመራር ይፈልጋል
አሁን በዚህ ቅጽበት በታሪካችን የብዙሃን መገናኛዎች አለማችንን ለመታደግ በጣም ትልቅ፣ ጀግንነት የተሞላበት፣ የተቀደሰ ሚና አላቸው። ህይወትን እያዳኑ በተጨማሪም የብዙሃን መገናኛዎች በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ፍቅርና የተቀደሰ አሴቱንም ማትረፍ ይችላሉ።
የታተሙ ቃላት በጣም ሃይለኛ ናቸው፣ ትልቅ ሃይል አላቸው። ሰውች በእለት ተግባራቸው በጣም ስራ ስለሚበዛባቸው ለመረጃና ለድርጊቶች ርፖርት፣ ጠቃሚ ለሆኑ ጉዳዮች፣ በህይወታቸው ውስጥ የሚፈልጉትን መረጃ ለመግኘት የብዙሃን መገናኛን ይፍልጋሉ። ስለዚህ በዚህ ወሳኝ ወቅት እርስበስርስ ለመነቃቃት፣ ፕላኔታችንና የፍጥረታቷ ህይወት አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ጊዜ፣ የብዙሃን መገናኛዎች ጠቃሚ መሳሪያቸው ነው።
በርካታ የቴሌቭዥንና ሬድዮ ጣቢያዎች ስለፕላኔታችን አስቸኳይ ሁኔታ እንዲያውም ስለ ቪጋ መፍትሄ፣ማድረግ ያለብንን ሽግግር፣ በጣም በትንሹ ለውጥ ለማምጣት፣ የስጋ ቁራጭ ውጣ የቬጀታሪያን ፕሮቲንን ግባ ተንተርሰው፣ ፕሮግራም አዘጋጅተው ስርጭት መጀመራቸው አስደስቶኛል። ይኸ ነው የሚፈለገው - ትንሽ ለውጥ፣ እያንድንዱ ሊፈጽመው የሚችለውን። ይህ ርካሽ፡ ጤናማም ነው።
የብዙሃን መገናኛው ለሰዎች የመፍቴውን አቅጣጫ በመጠቆም ብዙ ሊረዳ ይችላል። እንደእውነቱ ከሆነ በአሁኑ ወቅት የሚዲያ አስቸኳይና አጣዳፊ/ ሚና ራውሳቸው ቪጋን መሆን ነው - ርሁሩህ፣የተከበሩና መልካም ተግባራት ፈጻሚዎችና አጣዳፊውን የመፍትሄ የድርጊት መልእክት ለህዝቡ ማድረስ ነው። ሚዲያው አርኣያ መሆን አለበት።
እያንድንዱ ጋዜጣ፣ በየቀኑ በሚታተሙበት ጊዜ አንድ አረፍተ-ነገር አትመው ሊወጡ ይገባል። “ቬጅ ሁን፣ አረንጓዴ ሁን።” ይኸ ነው የሚፈለገው፣ በጣም ቀላል። ሁሉለም ጋዜጦች ይህንን ሊያደርጉ ይችላሉ። አንድ ርእስ በሆነ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ነው።“ፕላኔቷን ለመታደግ፣ ቬጅ ሁን፣ አረንጓዴ ሁን።”
ሁሉም ሚዲያ የ ቬጅ ማስታወቂያ በየቀኑ በቴሌቭዥን፣ በጋዜጣ፣ በሬድዮ፣ ወዘተ፣ በቢልቦረድ፣ በፊልም፣ ወይም በተንቀሳቃሽ ምስል፣ በኮምፒውተር ቦረድ ለእይታ እንዲያቀርብ እመኛለሁ። ይህ የትም ቀዳሚው የትኩረት ርእስ መሆን አለበት።
ሚዲያው ፕላኔቷን ለመታደግ መርዳት አለበት፣ ምክኒያቱም ፕላኔቷ ከሄደች ሁላችንም የለንምና። ሁሉም ይህን መገንዘብ አለበት። ገንዘብ -ጥቅም የለውም፡ ቤት-የለውም፣ ስልጣን-የለውም። ስለዚህ ህዝቡን ለማስገንዘብ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን። ብቸኛዋን ፕላኔታችንን፣ ቆንጆዋ ፕላኔተ በታደግ አለብታችንን መታደግ አለብን። እርሷን ብቻ ነው የምናውቀውና።
ለህብረተሰቡ እውነተኛ፣ታማኝ ጓደኛ ሁን፡ ስለአደጋኛ ሁኔታዎች ሁሉንም አስጠንቅቅ፣ አዳዲስ ግንኙነቶችን ፍጠርና መረጃዎችን ይፋ አድርግ፣ የስጋና የአለም ሙቀት መጨመር መካከል ያለውን ግንኙነት፣ ሰዎች የተሻለ የህይወት ጎዳና እንዲመርጡ እድል በመስጠት፣ ጠንካራ የጀግና ድምጽ በመሆን፣ ስቃያቸው የከፋ እንስሳትን ጨምሮ፣ በተለይ ድምጽ ለሌላቸው የጀግና ድምጽ ሁን፣ ምክኒያቱም ሁላችንም የተያያዝንና የተሳሰርን ስለሆን ተጽእኖው ሁላችንንም ይነካልና።
አለም የሚዲያን የተከበረ አገልግሎትና አመራር ይፈልጋል። ስለዚህ እባካችሁ፣ ደፋር ጋዜጠኞች የተቻላችሁትን ሁሉ አድርጉ። ፕላኔታችንን እንዴት መታደግ እንዳለብን እውነቱን ተናገሩ።