• ሰዎች አሁን በመተባበር ይህንን አጣዳፊ ቀውስ ለመፍታት እየጣሩ ናቸው፡፡ መሻሻልና ተቀባይነትን በየቦታው እያየሁ ነው፡፡ > ለማየት የምትፈልገውን ለውጥ ሆነህ ተገኝ
      • V.     ለማየት የምትፈልገውን ለውጥ ሆነህ ተገኝ



        ራሳችንን በመለወጥ አለምን እንለውጥ



        የተሻለ ፕላኔቷን መታደግ የሚችለው ግለሰቡ ነው። (ፕላኔቷን መታደግ የምንችለው እያንዳንዳችን ነን።)

        ነገሩ ከራሳችን ይጀምራል። ጊዜ መቆጠር ከመጀመሩ በፊት አንስቶ እድገት ምን ጊዜም ከግለሰብ ይጀምራል።  አለምን መለወጥ ከፈለግን መጀመሪያ ራሳችንን መለወጥ አለብን። መንግስት አሁን ሲጋራ ማጨስ መጠጥ መጠጣት ወይም እጽ መጠቀምን ቢከለክል እንኳን ነገር ግን ሰዎች በግል መጠቀም ከቀጠሉ ምንም ለውጥ አላመጣንም ማለት ነው። ስለዚህ አሁን መለወጥ ነው ያለብን።

        ብዙ ሰዎች ስጋን እንዲሁም ሌሎች የእንስሳት ተዋጽዖዎጭኝ እየተው በሄዱ ቁጥር አለምን ለማዳን ያለን እድል ይሰፋል፤ ይህ ብቻም አይደለም፣ ወደ ተፈጥሯዊ ግርማ ሞገሷና ቁንጅናዋ በመመለሷ እስካሁን አይተን የማናቀውን የበለጠ በረከት፡ ሰላምና ደስታን እንጎናጸፋለን።

        ምድራችን ወደ ቀድሞ ገጽታዋ ከተመለሰች ከሁሉም ፍጥረታት ጋር በርህሬሄ፣ በይቅርታና በሰላም ለመኖር የሚያስችልንና የበለጠ አስተማማኝ የሰ.ራ ፈጠራ ውጤቶችን የምናፈራበት ሁኔታን እንፈጥራለን።


         

        አዎንታዊ ሃይል አለምን ይታደጋል

        ሁላችሁም እባካችሁ ቀጥሉ። ስራችሁን ቀጥሉ ምክኒያቱም የሁላችሁም ጥረት አስተዋጽኦ አለውና። ስለስጋ ጎጂነትና ስለቬጀታሪያን አመጋገብ ፋይዳ አንድ በራሪ ወረቀት መረጃ እንኳን ፕላኔቷን የሚረዳ ስለሆነ አስተዋጽኦው ከቁጥር የሚገባ ነው። የእያንዳንዱ ቃልም የግምት ውስጥ የሚገባ ነው። አንድም መረጃ አይናቅም። እያንዳንዱ ሰው ትንሽ ይረዳል፣ እናም ወደ ገንቢ አቅጣጫ በሚመራ የወል ንቃት ምክኒያት ፕላኔቷ ትለወጣለች።

        ሁሉም የሚፋልገው አንድ ነገር ነው፣ ሁሉም የሚፋልገው ፕላኔቷን መታደግ ነው፤ የሚፈልገው አለምን ለማስቀጠል ነው፣ ይህንን ህይወት ለመጠበቅ ወይም የተሻለ ሁኔታ ለመፍተር ነው። እናም ንቃተ-ህሊናው ገፀዙፍ ነው። ሃይሉ መልካም ነው። ሁሉም ያንን ቁራጭ ስጋ ቢያስቀምጥ/ቢተው፣ የህይወት ዘቤውን ቢለውጥ - በጣም ቀላል ነው።


        መጀመሪያ  ፕላኔቷን አድን ሌሎቹ ነገሮች በኋላ ይለወጣሉና። አንተ/ቺ ብቻ አይደለህም ፕላኔቷን የምትታደጋት። ንቃተ-ሂሊናቸውን የለወጡ እንጂ። ወደ አረንጓዴነት የገቡ፣ መልካም ተግባር የፈጸሙ፣ ያ ማለት እራሳቸውን ለተሻለ ነገር ለውጠዋል ማለት ነው። ንቃተ-ሂሊናቸው አድጓል፣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ለምድራችንም በረከት ይሰጣታል። እነርሱም ኑሯቸውን ይቀጥላሉ፣ ልጆቻቸውም፣ የልጅ ልጆቻቸውም ልጅ ልጅ ልጆቻቸውም፣ ወዘተ።


        በዚያን ጊዜ የሰዎች ነቃተ-ሂሊና ከፍ ይልና ነገሮች ለነርሱም፣ ለሁሉም ግልጽ ይሆናል። በፍቅርና ሰላም መኖር እንኖራለን። ማየት የምትገልገው አይነት የአዎንታዊ አለም እይታ፣ በምድር ላይ ገነት ሊኖርህ ይገባል። መልካም አለም ማለሞ፣ አዎንታዊ አለም፣ ቆንጆ አለም፣ ገነት የሆነች አለም ማለም ይኖርብሃል። አለምን መታደግ የረሁርህነት ተግባር ነው። አለም መትረፍ እንኳን ባትችል ራስን ታድናለህ። በደግነት ፍቅርህ ትድናለህ። ጸጋህ ፈርጀ-ብዙ ነው ምክኒያቱም ሌሎችን ማዳን ትፈልጋለህና።

        አለምን መታደግ ከፈለግህ፣ ለዚህ ግብ እውን መሆን ለመስራት ከፈለግህ፣ መልካምነትህን/ክብርህን አያሳደግህ፣ የመንግስተ-ሰማያት አሴትህን እያሳደግህ ነው። ስለዚህ ፕላኔቷን ለመታደግ የሚያስትል ማበረታታቻ ካሰራጨህ/ ካስተላለፍክ፣ ቬጅ ከሆንክ፣ አረንጓዴ ከሆንክ፣ መልካም ከሰራህ፣ ሌሎችን ረዳህ ማለት ነው፣ ምክኒካቱም የሌሎችን ፍጥረታት ህይወት ለመታደግ በመፈለግህ ቅዱስ እሴትን አሳየህ ማለት ነው። ቅዱስነትህን ዳግም ኣነቃህ ማለት ነው። ጉዳዩ ቁሳዊ/አካላዊ ፕላኔትን ወይም ህይወትን መታደግ አይደለም። ምን ያህል ለመስራት ፍላጎት እንዳለህና በዚህ ህይወት-አድን ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ እንደቆረጥክ ነው::


        ሃይሉ ያለው በተጠቃሚ እጆች ውስጥ ነው

        ራሳችንና ፕላኔቷን በተመለከተ ትክክልኛ ነገር ማድረግ የሚከለክለን ማንም ሊኖር አይችልም። የእንስሳት ተዋጽኦን አለመጠቀም፣ አለመብላት፣ አለመግዛት ነው፤ ከዚያም እነዚህ ድርጅቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይከስማሉ። ስለዚህ ሃይሉ ያለው በእጅህ ውስጥ ነው።

        እኛ፣ ተራ ተጠቃሚዎቹ ታላቁን የመምረጥ ሃይላችንን ማለትም ስጋንና የእንስሳትን ውጤቶች የማቋረጠ ሃይላችንን በመጠቀምና ቬጋኖች በመሆን ነው። ቪጋን ከሆን ህይወት ገፊውን የሆነውን እንስሳት ማረባትን ለመቀጠል አንገደድም።

        በአሜሪካ የአሳማ እንዱስትሪ ከ2007 ጀምሮ $5.4 ቢሊዮን ዶላር ከስሯል።142 በአሁን ጊዜ ዋና ዋና ኩባንያዎች አንዱ ከሌላምው ቀጥሎ በመክር ላይ ይገኛሉ፣ ከመንግስት እርዳታ በመተየቅ ላይም ናቸው፣ ይህም ኩባኒያዎቹ የማይፈለገውን አሳማ ከገበሬዎች በ2009 $105ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ተገደዋል።143 ሃይለኛው የአሳማ እንዱስትሪ ለመቀጠል የሚታገለው፣ አንደኛ ለእንስሳቱ የእህል ምግብ መናር፣ ሁለተኛ ተጠቃሚዎች ከአሳማ ጉንፋን ወረርሽኝ በኋላ ምርቱን እንደሚፈለገው አለመግዛት ናቸው። እስቲ አስብ ማንም ስጋ ባይመገብ፣ ለመኖር ማንም እነዚህን እንስሳት አይገድልም ነበር። ይህ ከኩባኒያዎቹ የማግባባት ዘመቻ የበለጠ ሃይል አለው።

        ሃይል አለን። የእንስሳቱ ኩባኒያዎች ሃይል እኛ የሰጠናቸው ነው! ሃይላችንን እኛ አካፍለናቸው ነው። ነገር ግን መግዛቱን ካቆምን አይኖሩም/የሉም።


        “እንዴት ቬጅ እንደሚኮን ለጀማሪዎች” ሱፐፕሪየም ማስቴር ቺንግ ሃይ


        1.    ቬጅ ከመሸመትህ በፊት - ማለት ከመሸመትህ በፊት ቬጋን ምግብ መመገብ፣ ሱፐርማረኬት በሚትደርስበት ወቅት
            እንዳርብህ።

        2.   በቀጥታ ወደ ሱፐርማርኬቱ የቬጅ ክፍል ሂድ/ጂ፣

        3.   ከኢተርኔት ወይም ከጓደኛ ወይም ከቪጋን ድርጅት የቬጅ ምግብ ዝርዝሮችን አግኝ፣

        4.   ደጋፊ፣ አዲሰ የቬጅ ጓደኛ አብጂ፣

        5.   ስለቬጅ ፋይዳዎች/ጥቅሞች መረጃ አግኝ፣

        6.   የቬጅ መንገድን ለአሰራጭ፣

        7.   ቅዱስነት ይሰማህ።



        አረንጓዴ ሁን



        አረንጓዴ ሁን፡፡ እነዚህ አካባቢውን ለመጠበቅ የሚወሰዱ እርምጃዎች ናቸው፣ ማለትም እንደ ዛፍ ተከላ፣ ዘላቂነት ያላቸው የኢነርጂ ምንጮችን ስራ ላይ ማዋልና መጠቀም፣ የሃይብሪድ መኪናዎችን መጠቀም፣ ወዘተ፡፡ ይህ የአረንጓዴ አመጋገብንም፣ የቪጋን አመጋገብንም ይጨምራል፡፡144

        የኦረጋኒክ ቪጋን እርሻን ደግፍ

        ኦጋኒክ ለመሆን ሞክር፡፡ የኦርጋኒክ ገበሬዎችን ለማበረታታት/ለመደገፍ ኦርጋኒክ ምግብ ግዛ/ግዢ፡፡ የኦርጋኒክ፣ ቬጅታሪያን አራሽን ለመደገፍ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፡፡

        እንስሳትን ማርባት ትተው ቪጋን ወይም የኦርጋኒክ ቪጋን ስራን የመረጡ፣ ከአሜሪካ እስከ ኢራን እስከ ኣውላክ (ቬይትናም) እስከ ፎርሞሳ (ታይዋን)፣ የተቀየሩት አዲስ መረጃ ስላገኙ ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ከሌሎች ሰዎች፣ ከመሬቱ ጋር ተሳስቦ/ተስማምቶ፣ ህይወት ደጋፊ ምርቶችን የሚያመርት፣ ሀቀኛ ገበሬ የተሸለ መንገድ እንዳለ በመረዳቱ ነው፡፡  የእንስሳት አርቢዎችን፣ አንድ ባንድ ስጋ ስለሚያስከትለው ጉዳትና ኦርጋኒክ ቪጋንን ፋይዳዎች በማነጋገር እኛም መረጃ መስጠት እንነችላለን፡፡

        መስራት የሚፈለግናየሚችል ሁሉ ይስራ፡፡ ወደ ገበሬዎቹ ሂድና አነጋግራቸው፡፡ በምትችልበት አጋጣሚ ሁሉ ይህን ለማድረግ ጊዜ መድበህ ወደነስሱ ሂድ፡፡ ምንም እንኳን እንደ መንግስት ሃይል/ስልጣን ባኖረንም መሞከር እንችላለን፣ አንድ ባንድ ፡፡ እውነታውን ማስጨበጥ ይገባል፡፡ ሁኔታውን ንገራቸው፡፡ እስኪገባቸው ደግመህ ደጋግመህ ንገራቸው፡፡ ጻፍላቸው፡፡ አናጋግራቸው፡፡ የምንችለውን ብቻ ነው ማድረግ ያለብን፡፡

        አትከልትና ዛፎችን ትክል

        የኦርጋኒክ ተክሎችንና ዛፎችን መትከል እንችላለን፡፡ የተሻለው የፍራፍሬና የነት ዛፎችና እንደ ባቄላ ያሉና ብዙ ውሃ የማይፈልጉ ተክሎችን መዝራት ነው፡፡

        አንድ ዛፍ አንዴ፣ ከዚያም ወዲህ ኢክሲጂን እጥረት ፈጽሞ ሊያጋጥመን አይችልም፡፡

        አትክልችን ወይም ዛፎችን በመሬትህ ላይ ወይም በጓሮህ መትከል ትችላለህ፡፡ ፍራፍሬዎች ሊያሟሉልን ይችላሉ፡፡ ጣፋጭ ፍራፍሬዎች ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ የተለያዩ ብዙ አይነት ፍራፍሬዎች አሉ፣ ዱባ፣ ሀባብ፣ ቅልና፣ ፓፓያ፡፡ የምትችለውን ትከል፡፡ በቀላሉ የሚበቅሉ፣ ልታሳድግ ምትችለውን ትከል፣ የሚያሟሉልንና በምግብ ይዘት የበለጸጉ፣ በፍጥነት የሚያድጉና ብዙ ውሃ የማይፈልጉ፣ በማንኛውም ነገር ላይ መኖር ስለምንችል ማለት ነው፡፡

        ሮ ቦታ ያላቸው ሰዎች፣ ሳር ወይም ሌላ ነገር ከመትከል ወይም ባዶ ከመተው አትክልት ቢያበቅሉ ይመረጣል፡፡ ለራሳችሁ የሚበቃ ወይም የሚደግፍ ተጨማሪ ማምረት ትችላላችሁ፡፡ በዚህም  ገንዘብ፣ ጊዜና የመገገዛ ኢነርጂ በመቆጠብ ጥሩ ቬጅታሪያን ምግብ ሊኖራችሁ ይችላል፡፡

        እቤት ውስጥም ማብቀልና ማምረትም ትችላላችሁ፡፡ በረንዳ ካላን በውሃ ውስጥ እንኳን መትከል እንችላላን፡፡ የራሳችን አትክልት እንዲኖረን አሁኑኑ መጀመር አለብን፡፡

        የውሃ እጥረት ካለብን፣ ባቄላና ፍራፍሬ ማብቀል እንችላለን፡፡ የባቄላ ዝርያዎች በቀላሉ ይበቅላሉ፡፡ በፍጥነት ይበቅላሉ፡፡ ያለ ውሃ ያድጋሉ፡፡ እንዴት ማብቀል እንደምትችል ከሱፕሪየም ማስተር  ቴሌቪዝን መማር ተወቸወላለህ፡፡145

        አታባክን/ቆጣቢ ሁን

        ቀላል ኑሮ ኑር፣ የቀለለ፣ የበለጠ ቀላል ኑሮ የተሸለ ነው፡፡

        በቁጠባ ተጠቀም፣ ከሚያስፈልህ በላይ አትተቀም፣ ያለህን አድንቅ/ባለህ ተደሰት፡፡ ተፈትሮ የሰጠችን ሃብት ውድና ውሱን ናቸው፡፡ ማባከን አንችልም፣ ምክኒያቱም በአግባቡ ስንጠቀምበት ነው ለረዚም ጊዜ ሊቆዩልን የሚችሉት፡፡

        ሁል ጊዜ አዲስና የፋሽን ልብስ መግዛት የለብንም፡፡ ወደ አዲስ ምግብ ቤትም መሄድ የለብንም፡፡ ብዙ ገንዘብ ሳናወጣ በህይወት ውስጥ የሚያስደስቱንና የሚያረኩን ነገሮች አሉ፡፡ ያለ የቤት እቃ መኖር እንችላለን፤ ይህም መልካም ነው፡፡

        መቆጠብ ትችላለህ፣ አነስተኛ ሙቅ ውሃ መጠቀም፣ አልፎ አልፎ ሻወር መውሰድ፣ ሻወር ስትወስድ ውሃ ከፍተህ አትተው፣ ጥርስህን ስትቦርሽ ውሃ ዝም ብለህ አትልቀቅ፣ በማትጠቀምበት ጊዜ ኮምፒተርህን አጥፋ፣ በማትፈልግበት ወቅት መብራት አጥፋ፣ የማትጠቀምበቸውን ማናቸውንም ነገር አጥፋ፣ ምናልባትም ወጪህን እስከ 10% መቆጠብ ትችል ይሆናል - የውሃና ኤሌክትሪክ በድምር፡፡

        ሌላው ቀለል ያለ የኑሮ ማበልጸጊያ ዘዴ ጊዜህን ጸጥ ባለ የተፈትሮ ቦታ ማሳለፍ ወይም በቤትህ ውስጥ ጸጥ ያለና ሰላማዊ አካባቢ መፍተር ነው፡፡ አንባቢ አዕምሮ - መንፈስን ከፍ የሚያደርጉ እንደ መንፈሳዊ መጽሃፍትን ማንበብ፣ እንዲሁም ሜዲቴሽን በሰላምና በደስታ ለመኖር የሚያስችሉን እናም ለመደሰት ብዙ መኩተን እንደማያስፈልግ ራሳችንን ማስገንዘብ የሚያስችሉን ጥሩ መንገዶች ናቸው፡፡



        መልካም ተግባራትን ፈጽም
        ---------------------------------------------------------------------------------------------------


        ለፕላኔታችንነ የፍቅር አየር መፍጠር አለብን፡፡ ይህም እንድንጠበቅ ይረዳናል፡


        የፕላንታችንን አስተማማኝ ቀጣይነት የምናፋጥንበት ሌላው ጥሩ መንገድ የበለጠ ገንቢ/አዎንታዊ ሃይል.ኢነርጂ መፍጠር ነው፡ መልካም ተግባር፣ ፍቅርና ደግነት ማራመድ፡፡ የፍቅር አሴትህን ማስፋፋት ነው፡፡ ይህ የማበገር ጋሻን ይፈጥርና ከክፉ ይጠብቀናል፣ ፕላኔቱንም ይጠብቃል፡፡

        መልካም ተግባራት በመፈጸም የፕላንታችንን የፍቅርና ገንቢ/አዎንታዊ ከባቢን ማጠናከር  እንችላለን፡፡ ለፕላንታችን አስደሳችና ፍቅር የተሞላበት ከባቢያችንን በመፍጠር በዚያ ተጠብቀን በደስታ መኖር እንችላለን፡፡ ይህ በጣም ሳይንሳዊ ነው፡፡ ይህንን ለመረዳት በምንም ሃይማኖት ማመን አይጠበቅብንም፡ ከባቢያችንን እንፈትራለን፡፡ ሁሉም ተስማሚውን ከባቢ ከፈጠረ፣ ፕላኔታችን ሰላም ታገኛለች፣ እኛም በገነት ውስጥ እንዳለን ይቆጠራል፡፡

        ትርፍ ገንዘብ ካለህ ወይም ቡድሃዎች ወይም ቦዲሳቲቫዎች ከምትፈልገው በላይ ብዙ ገንዘብ ሰጥተውህ ከሆነ ሂድና  ለድሆችና ገንዘቡ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ስጥ፡፡ የምትሰጠው የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ለጽድቅ መስጠት የለብህም፡፡



        ጸልይ ንስሃም ግባ
        -----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

        ጸልይ፣ በቆራጥነት ጸልይ፡፡ ወደ መንግስተ-ሰማያት ጸልይ፣ ወደ ሁሉም ቡድሃዎች፣ ወደ አማልክት፣ ወደ ሁሉም መላዕክት ጸልይ፣ እንድንነቃ ለሚረዱን፡፡ ወደ ለሁሉም እንስሳት ጸልይ፣ በቀትታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስጋን በመመገብ የጎዳናቸውና ያሰቃየናቸው እንስሳት ሁሉ ይቅርታ እንዲያደርጉልን እንጸልይ፡፡ እንዲሁም ለመንግስተ-ሰማያት ጥበቃና ምህረት እንጸልይ፡፡  መላው አማልክት በጊዜ ቤታችንን እንድና ተርፍ እንዲረዱን እንጸልይ፡፡ ከልብ በመጸለይና በፍትነት መንቀሳቀስ አለብን፡፡ በእውነቱ በራሳችን ብቻ ይህን ማድረግ አንችልም፡፡

        ምድርንና ነዋሪዎቹን በመጉዳታችን ተጸጽተን ንስሃ በመግባት ደግመን ደጋግመን ይቅርታቸውን መጠየቅ አለብን፡፡ ድርጊቶቻችንንም መቀልበስ አለብን፡፡ የተሻለው ንስሃ ለለውጥ ጥረት ማድረግ ነው፡፡ አዙረህ እይ፣ ሞልካም የሆነውን ተግባር ፈጸ.ም፡፡ መጥፎ ከሆነው ድርጊት ሁሉ ተቆጠብ፡፡

        መለኮታዊ ሃይል በምድር ላይ ተከስቶ መሪዎችን፣ የብዙሃን መገናኛን፣ ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎችና መላው የአለምን ዜጎች ትክክለኛ እርምጃዎች ወስደው በፍትነት-ሳይዘገይ በፍጥነት ፕላኔን መታደግ እንዲችሉ እንዲያነቃቸው መጸለይ እንችላለን፡፡ ምክኒያቱም በአሁኑ ወቅት/ቅጽበት፣ ከክፉ እንድት ጠብቀን መጸለይ ሳይሆን፣ ገነት ጣልቃ ገብታ ፕላኔታችንን እንድትታደግልን እንሻለን፣ እያንዳንዱ ሰው ለቪጋን መፍትሄ እንዲነቃ መጸለይ፣ ምክኒያቱም ያ ነው ፕላኔታችንን መታደግ የሚችለው፡፡



        የቪጋንን ጉዞ ጀምር
        ---------------------------------------------------------------------------------------------------

        ዜናውን አሰራጭ

        ተጨባጭ ሁኔታው በሚጠይቀው መሰረት የህይወት ዘይቤያቸውን ወደ መልካም እንዲቀይሩብዙ ሰዎችን ለማንቃት እንደረዱ፣ እነዚህ በመስካቸው እውነተኛ ፋና ወጊዎችና ትክክለኛ የጊዜያችን ኮከቦችና ጀግኖችናቸው፡፡

        መልዕክቱን ማሰራጨት አለብን፣ ማናችንነም ለፕላንታችን የምናስብ መልዕክቱን ማሰራጨት አለብን፡፡ ከዚያም ሰዎች ወደኛ ይቀላቀላሉ፡፡

        ለመንግስታትና ሚዲያ ጻፍ

        ለዘላቂ ውጤት፣ በመጻፍና ስለአለማችን ሁኔታ ያለውን መረጃ ከድረ-ገጽ [SupremeMasterTV.com] በመቅዳት በመላክ፣ በመስጠት የመንግስት ሃላፊዎችን ማግኘትና ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡145

        መንግስት ያውቃል፡፡ ነገር ግን የቅድሚያ ትኩረቱን ሌላ ቦታ አድርጎ ነው እንጂ፡፡ አንተና ሌሎች ዜጎች ትኩረታችሁ ከሆነ መንግሰታችሁን በማግኘትና በመጻፍ ጉዳዩ ምን ያህል አጣዳፊና ለኛም ሆነ ለልጆቻችን የወደፊት ህይወት የታጋረጠውን ችግር መንገር ወይም ማስታወስ ትችላላችሁ፡፡

        ስለቪጋን መፍትሄ ለመንግስት መሪዎቻችሁ ጻፉ፣ ከተቻለ አብራችሁ ሄዳችሁ መጎብኘት ትችላለችሁ፡፡ በሀገሮቻቸው ላይ ተጋረጠውን አስከፊ ችግር መሪዎች ይረዳሉ፡፡ አሁን ዜጎች ከረዱኣቸው፣ ከሳሰቡኣቸው የተሻለ ፍላጎታቸውን የሚጠብቅ መሆኑን ካስታወሱ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለመቅረፍ የበለጠ ይነሳሳሉ፡፡ እናም አለም ሙቀት መጨመር ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ያስታውሳሉ፣ ይህ ሙያዊ ግዴታቸው ብቻ ሳይሆን በግልም ማለትም የራሳቸውንና የልጆቻቸውን ህይወት የሚመለከት መሆኑን ይረዳሉና፡፡

        ለመላው የመንግስት አካላት መጻፍ፣ ለፕሬዝዳንቱ ብቻ ከሆነ ውሳኔ/ውጤት ላያስገኝ ይችላል፡፡ ለሚመለከታቸው የመንግስት መምሪያዎች ሁሉ ጻፍ፡፡ ሁሉም ይህንን በአንድነት ይፈጽም/ያድርግ፡፡ ብዙ ቅጂዎች በማዘጋጀት ለያንዳንዱ፡ ለፕሬስዳንቱና ለቁልፍ ወሳኝ መምሪያዎች አድርስ፡፡

        ብዙ ጻፍ፡፡ ኢሜል አድርግላቸው፣ ፋክስ አድርግላቸው፣ ጻፍላቸው፡፡ ለጋዜጦች ጻፍ፡፡ ለሬድዮ፣ ለቲቪ አውራ፡፡ ቃለ-ምልልስ ስጥ፡፡ የምታውቀውን ለሁሉም ንገር፡፡ የምትችል ከሆነም አግባባ፡፡ የምታውቃቸውን መሪዎች አነጋግር፡፡ ጉኣደኞቻቸውን አነጋግር፣ መሪውን የምታውቅ ካልሆነ ጉኣደኛውን ቅረብ፣ መሪውን የሚያውቁ ሰዎችን አነጋግር፡፡ አስተናጋጁን/ዋን፤ የቤት ጠባቂያቸውን፣ የጽዳት ሰራተኞቻቸውን፣ ሾፌሮቻቻን፣ የቤተሰቡን አባላት፣ ልጆቻቸውን አነጋግር፣ ወደ አንድ ት/ቤት የሚሄዱ ልጆችን፣ ሰራተኞቻቸውን፣ ጸሃፊዎቻቸውን፣ በተገቢው መንገድ ለፕሬዝዳነቱ ጆሮ የቀረቡ ናቸው ብለህ የምተገምተውን ማንኛውንም ሰው አነጋግር፡፡

        መሪዎቹ ተገቢና ገንቢ እርምጃ ከወሰዱ በመጻፍ ማመስገንና ማበረታታት አለብን፡፡ ገንቢ አበለታታች መሆን አለብን፡፡ ትክክለኛ ነገር ሲያደርጉ በለጠ እንዲገፉበት፣ እነዲያውም የተሻለ አንዲሰሩ ማበረታታት አለብን፡፡

        ወደ ፕሬዝዳንት ኦባማ አንድ ደብዳቤ ጽፌኣለሁ፣ ለአወሮጳ ህብረትፓርላማ ጽፋለሁ፣ ለአወሮጳ ኮሚሽነር ጽፋለሁ፣ እነርሱም መልስ ሰጥተውኛል፡፡ በመጪዎቹ ጊዜያት እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተውልኛል፣ ያልኩትን ቃል፣ ምክር ማስታወሻ እንደሚወስዱ፣በልባቸው፣ በአዕምሮኣቸው ቃል ገብተውልኛል፡፡ የሚሰሙ፣ እንደዚህ ያሉትን መሪዎች አደንቃቸዋለሁ፡፡

        መሰረታዊ እንቅስቃሴዎችንና የቪጋን ጉዞን ምራ

        መሰረታዊ ሴሚናሮችን አካሂድ፡፡ ለአለም አየር ሙቀት መጨመር መፍትሄ ለህዝብ መረጃና ማስረጅ ስጥ፡፡ ጥረትህን ከሌሎች ቭጀታሪያኖች ጋር አቀናጅ፡፡ አብረህ በመስራት የጥረት ፍሬዎች ይበረክታኩ/ይበዛሉ፣ እናም ፕላኔታችን ልትድን ትችላለች፡፡

        መንግስትን ወይም ቴክኖሎጂን እስክሰራ ቁጭ ብለን ከመጠበቅ እንደ ግለሰብና እንደ ህብረትሰብ፣ እርምጃ መውሰድ አለብን፡፡ ቀላል ነው፡፡ አንድ መፍትሄ ነው ያለው፡ ርህራህ ምግብ፣ ምክኒያቱም ርህራሄ ርህራሄን ይወልዳልና ነው፡፡ ያ በጣም ቀላል የዩኒቨርስ ህግ ነው፡፡ ማንኛውም ተግባር ተቃራኒ ምላሽ አለው፡፡ ስለዚህ ለመንግስት ፖሊሲ የማረጋገጫ ሂደትን መጠበቅ ወይም ገንዘብን መጠበቅ የለብንም፡፡

        በአካባብህ ደረጃ አንድ የምግብ ማዘጋጀት ክፍለ-ጊዜን መደገፍ ትችላለህ፡፡ ይህ ሰዎች ጣፋጭና የበለጸገ የቪጋን ምግብን ለራሳቸውንና ለቤሰቦቻቸው ማዘጋጀት ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እንዲረዱ ያደርጋል፡፡

        ፈጣን አገልግሎት ሚሰጡና በምግብ ይዘታቸው የበለጸጉ ላቭንግ ሃት/የፍቅር ጎጆዎች የሚባሉ የቪጋን ምግብ ቤቶች እነዲስፋፉ ሀሳብ ነበረኝ፣ እውንም/ፍሬያማም ሆነዋል፡፡ አሁን ብዙ ናቸው፡፡ ከ90 በላይ/አሁን ያለን መረጃ 138 መሆኑን ያሳያል፣ በተለያዩ አገሮች ውስጥ የፍቅር ጎጆዎች ተከፍተዋል፣ ከፎርሞሳ (ታይዋን) እስከ ፈረንሳይ እስከ አሜሪካና አውስትራሊያ ድረስ፡፡147 የተከፈቱት ስራ በሚጣደፍባቸው በገበያ ማዕከሎችና በዋና ዋና መገናኛዎች አካባቢ ነው፡፡

         

        መግለጫ፡ ከሱፕሪየም ማስተር ቺንግ ሃይ ጣፋጭ ቪጋን ምግቦች አንዱ የሆነው በልዩ የምግብ ዝግጅት “A Gift of Love” SupremeMasterTV.com/gol; SupremeMasterTV.com/veg ላይ ቀረበ

        ሌሎች ሰዎችም፣ ሁሉም የቪጋን ምግብ ቤቶች መክፈት ይችላሉ፡፡ አስበውት አይደለም የሚከፍቱት፣ ቪጋን ስለሆነ፣ እየተለመደ ስለመጣ፣ በጥሩ ምግብነት ወይም ተመጋቢዎች ወጣቶችና አረጋዊያን፣ እንዲየውም ከስጋ የተሻለ ነው!” ብለው ስለተቀበሉ ነው፡፡ ስለዚህ የቪጋን ምግብና ተዋጽኦውን ማዘጋጀትና ለሰዎች ማቅረብ፣ በእውነቱ የተሻለ አማራጭ ይሆናል፡፡



        መግለ:የኢንተርናሽናል የፍቅር ጎጆ የምግብ ቤት ሰንሰለት በሱፕሪየም ማስተር ቺንግ ሃይ LovingHut.com የተጸነሰና የተባረከ ነው፡፡



        ሰዎች አሁን በመተባበር ይህንን አጣዳፊ ቀውስ ለመፍታት እየጣሩ ናቸው፡፡ መሻሻልና ተቀባይነትን በየቦታው እያየሁ ነው፡፡

        ሰላማዊ ተረቶችን እያየሁ ነው፣ ደግ የእርዳታ እጆችን በየአገሮቹና በግለሰቦችና በቡድኖችና በድርጅቶች ይታያሉ፡፡ በተለያየ መንገድ ፍቅር እያደገ በመምጣት ላይ መሆኑን እያየሁ ነው፡፡

        እነዚህ ምልክቶች እስካሁን ጎልተው አልወጡም ይሆናል፣ ነገር ግን በፍትነት ወደ ወላፈን እሳት የሚለወጡ ጣጣቴዎች ናቸው፣ ይህ ያለፈውን የድንቁርናና የጥላቻ ቅሪት ወደላ በመተው፣ በምድር ላይ የአዲስ መልካምና ቅዱስ ዘር ጅምርን የሚያበስር ነው፡፡

        እባክህ አዎንታዊና ገንቢ አስተሳሰብ ይኑርህ አናም ማድረግ የምትችለውን ሁሉ በማድረግ ጎረቤቶችህን አንቃ/እናንቃ፡፡ በህወታችን እውን ስለሚሆነው ስለገነታዊ አለም አልም፣ እናም ለመጪው ቀጣዩ ትውልድም አዳርስ፡፡

        አብረን ነን። አንፈራም። ጠንካሮች ነን። አለምን ለመቀየር ቆርጠን ተነስተናል። ደፋሮች/አይበገሬዎች ነን። ሰላምን፡ ደህንነትን ፍቅርን ከሚመኙ ከሁሉም ሰብኣዊ ፍጡሮች ጋር ነን።

        ይገባናልም!  እባክህ ቀጥልበት።

         

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *