• ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ በግንባር ለአለም መሪዎች ያቀረችው ተማጽኖ

      • ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ በግንባር ለአለም መሪዎች ያቀረችው ተማጽኖ




        ከመደበኛ ሀላፊነታቸውና ተጠያቂነታቸው ወጣ ብለው ለያንዳንዱ በመቆርቆር ለሚናገሩት ጎበዝና ድፍረትን የተላበሱ የአለም መሪዎችን እጅግ አመሰግናቸዋለሁ
        ። ለመልካም ምኞታቸው ህዝቡ አድናቆትን ባይቸራቸውም፣ ገነት ትመዘግብላቸዋለች። በወዲያኛው አለም ታላቅ በረከትን ይጎናጸፋሉ። ርግጥ በመሪነች ቦታ መሆን በጣም አስቸጋሪ ነው።

        መሪ መሆን ማለት ጉብዝናን፣ ርህራሄንና መልካምነትን መጎናጸፍ ነው። ለዚህ ነው መሪ የሆንከው። በመሪነት ቦታ መሆን በርግጥ ቀላል አይደለም፣ ለዚህ ነው የመረዎች ጥቂት የሚሆኑት። በአንድ አገር አንድ ንጉስ ብቻ ነው የሚኖረው፣ አንድ ንግስት፣ ጥቂት ልኡላንና ልኡላት፣ አንድ ፕሬዝዳንት፣ አንድ ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ከብዙሃኑ ህዝብ ጋር ሲታይ በጣም ጥቂት መሪዎች ናቸው ያሉት። ጎበዝና ደፋር ሀቀኛና ጥበበኛ መሪዎች በጣት የሚቆጠሩቱ ናቸው።

        ለነዚህ ጥበበኛና ጎበዝ መሪዎች ሙሉ ድጋፍና አክብሮት እንሰጣለን። ለመልካም ተግባራቸው ፈጣሪ ጥበቡንና ብርታቱን እንዲሰጣቸው እንጸልይላቸዋለን። ምክንያቱም መሪዎች ጥቂት ናቸው። እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው ጥበብና ድፍረት የተጎናጸፉት። መሪ በመሆን ለይተን ማወቅ ያለብን ነገር ለምናገለግለው ህዝብ መልካሙንና መልካም ያልሆነውን ነገር ነው። መልካሙን እንዲተገብሩ እናበረታታለን፣ እናመቻቻለን። መጥፎውንና ክፉውን ተግባር እንዲያቆሙ እንዲተው እንጠብቃቸዋለን። ይህ ነው የመሪነት ትርጉም።

        ለመላው ህዝብ ጠቃሚ የሆነውን ከእንሰሳት ተዋጽኦ ነጻ የሆነ የህይወት ዘይቤን አበረታታ

        መልካም መንግስት ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር ለተራውና ለመላው ህዝብ ጠቃሚ የሆነውን ፖሊሲ ማበረታታት ነው። ይህን እውን ለማድረግ መንግስታት አሁን መረዳት ያለባቸው ሁኔታው ልዩ መሆኑንና ይህም ልዩ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚፈልግ ነው።

        እኔ የምሰጠው ሀሳብ ሁላችሁንም የአለም መሪዎችና መንግስታት የምማጸናችሁ ከእንሰሳት ነጻ የሆነ ህይወትን እንድታበረታቱ ነው ፈጠን ብላችሁ፣ ፕላኔታችንን ለመታደግ እንችል ዘንድ

        ቅድሚያ የመኖራችን ጉዳይ

        ጊዜ የለንም ብዙ ጊዜም አልቀረንም። ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም። ይህ የመኖርና ያለመኖርና ስለልጆቻችን ነው። መንግስታት ሁሉ ህዝቦቻቸውን ጤነኛ፣ ከእንሰሳት ነጻ የሆነ አመጋገብ እንዲከተሉ ቢያበረታቱ ፕላኔታችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ መታደግ እንችላለን።

        ለምድራችን መልካም የሆኑ ተግባራት ስራና መኖሪያንም ይፈጥራሉ። የምግብ እጥረት አለብን፣ ስለዚህ መንግስታት የኦርጋኒክ ቪጋን ገበሬዎችን በቀላሉ ሊያበረታቱና ሊረዱ እንዲሁም የሌሎች አረንጓያዴማ ልምዶችን ሊያራምዱ ይችላሉ። ይህ በጣም ይረዳል። መንግስት ቅድሚያ መስጠት አለበት፣ ፕላኔቷን ለመታደግ፣ ኦርጋኒክ እርሻን መደጎም።

        ለሁሉም የአለም መሪዎች ደግሜ ጥሪዬን አቀርባለሁ፣ ፍቅራችሁ በቅድሚያ ለአገራችሁ ዜጎች፣ ለሴቶችና፣ ለሁም ህጻናት ይሁን፣ በድፍረት መከወን አለበት፣ ህዝቦቻችሁ የሰጡኣችሁንና የያዛችውትን ስልጣንና ሀይል አለምን ለማዳን አውሉት።

        አለማቀፋዊው የእንሰሳት እንዱስትሪ አሁን የሃይል ዘርፉን ያህል እንዲያውም የበለጠ ዋንኛው የአለም ሙቀት መጨመር ምክኒያት ሆኗል። ይህ እንዱስትሪ ቢያንስ ከ80% በላይ አስተዋጽኦ እንዳለው አውቃለሁ። የስጋ እንዱስትሪ የህዝቦቻችሁን ውሃ እያሟጠጠ፣ ጤናቸውን እየጎዳ፣ ወደ ጦርነት እየገፋቸውና አዳዲስ በሽታዎችን በየቀኑ እየፈለፈለ ይገኛል።

        ህዝቦቻችሁን እየገደለ ነው፣ ማቆም የምትችሉትም እናንተው ብቻ ናችሁ።

        የሚያስፈልጋቸው አንጸባራቂነታችሁን፣ ጀግንነታችሁን፣ የቪጋን አርኣያነታችሁን ነው ምክነያቱም በእውነት መንግስታቶቻቸውንና መሪዎቻቸውን በእውነት ይመለከታሉ።

        የኦርጋኒክ ቪጋን እርሻ መመሪየዎቻችሁና በጣም ተፈላጊውን የቪጋን የህይወት ዘይቤ ለውጥ የሚያመጡ ዘመቻዎቻችሁ ወይም ህጎቻችሁ በትልቁ ሁኔታዎችን ለህዝቡ ያመቻችላቸዋል።

        ህይወታቸውንና የሚወዷቸውን ህይወት በመታደጋችሁለመጪው ትውልዶችና ለልጆቻቸው አለምን በማዳናችሁ ዜጎቻችሁ በእናንተ ስር የሚተዳደሩት ሰዎች ያደንቋች ያሞግሷች ይወዳች ይደግፏችሃል ያስታውሷችልም። ፈጣሪም በጣሙን ይባርካችኋል። የቪጋን ለውጥን ምሩ። ይቅርታንና ሰላምን አራምዱ እናም ችግሮች እንደ ድህነት ግጭት የገንዘብ ቀውስ እና ወረርሽኝ ያሉት ሁሉ ይጠፋሉ

        የአገር መሪዎችእስካሁን በዚህ በኩል ላደረጋችሁት ጥረት አመሰግናችኋለሁ።

        ሁላችንም የመፍትሄው አካል ነን

        ነገር ግን ከፈቀዳችሁልኝ፣ በሀቀኝነት የምለው እስካሁን በማድረግ ላይ ያለነውና ያቀድነው በቂ አይደለም፣ ፍጥነት የለውም፣ እናም በማፍጠን የበለጠ እንደምትሰሩ በድፍረታችሁና በእምነታችሁ እተማመናለሁ።

        ለአለም ድርጅቶች ሁሉ፣ የማህበራዊ እንቅስቃሴን ጥንካሬ በደንብ የሚረዱ የመገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ ለህዝብ የመረጃ ምንጭ በመሆናችሁና አስገራሚና ስብእና የተላበሰ፣ ጠቃሚ፣ ተክክለኛ፣ ከእንሰሳት ነጻ የሆነ - የቪጋን ህይወት መንገድ ህዝቡን ስላሳያችሁ አመሰግናችኋለሁ።

        ግለሰቦች፣ እናንተም ፕላኔታችንን ለመታደግ ላደረጋችሁት ሁሉ አመሰግናችኋለሁ፣ ግን እባካችሁን በወቅቱ አድርጉት፣ ብዙ ይቀረናል፣ ነገር ግን ያለን ጊዜ በጣም ትንሽ ነው።

        መሪዎቻችንና ሰብኣዊ ፍጡራንን ሁሉ ጎረቤቶቻችንን ሁሉ ለለውጥ መገፋፋትና ማንቀሳቀስ፣ ቪጋን እንዲሆኑና ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን፣ ልጆቻቸውንና እንሰሳትን እንዲታደጉ፣ እናም የምትኖሩት ህይወት ትርጉም ይኖረዋል ማለት ነው።

        ከአደጋው መውጣት እንችላለን፣ በትክክለኛ አቅጣጫ። ቤታችን በእሳት ተያይዟል ይሁንና የውሃ ጎማ(ሆዝ) እዚያው ፊት ለፊታችን ይገኛል።

        ኣንሱትና ተጠቀሙበት ይህን ያህል ቀላል ነው ነገሩ። በቃ ቪጋን ሁኑ። እናም እባካችሁ ፍጠኑ። ያለን ጊዜ የተቆጠረ ነው።

        የሰው ልጆች ሁሉ፣ ፈጣሪ/እግዚኣብሄር ይህን ያህል ይወዳችኋል። ስለዚህም ፕላኔታችንን ለመታደግ ከምንጊዜውም የበለጠ ተስፋ አለን። ለአዲስ፣ በርህራሄና በፍቅር ሃይል፣ በደግነት ለተሞላችና በረከቱ ከፈጣሪ ለማይቋረጥባት ለቪጋን ፕላኔት እንንቃ።

        ለዚህ ሰላማዊና ልንደርስበት ለምንችለው አለም መልካም ስራችሁን እንድትቀጥሉበት ጸሎቴ ነው። በጣም አመሰግናችኋል ሁላችሁንም። አመሰግናለሁ።

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *