II. የሃይማኖት መሪዎች ሌሎችን በትክክለኛው የህይወት መንገድ ይመራሉ
የሃይማኖት ሰዎችና መሪዎች ስለዚህ ነገር መናገር አለባቸው፣ ግንባር ቀደም ሆነው ህዝቡ የተደቀነብንን ችግርና የአለም ሙቀት መጨመር መፍትሄን እንዲረዳ መርዳት አለባቸው።
የሃይማኖት መሪዎች ለተከዮቻቸው አርአያ መሆን አለባቸው። በመጀመሪያ ቬጀታሪያን እንዲመገቡ ማበረታታት አለባቸው፣ ክፉውን አስወግደው መልካሙን እንዲሰሩ፣ አካባቢውን እንዲንከባከቡ ማበረታታት አለባቸው። የሃይማኖት መሪዎች ለተከዮቻቸው እነዚህን እንዲያከናውኑ ቢነግሯቸው ምድራችን ለመታደግ የድህንነት ዋስትና አገኘች ማለት ነው፣ ምክኒያቱም ሰላም የሚጀምረው ከምግብ ማእዳችን ስለሆነ ነው። ሰላም ከምግብ ጠረጴዛችን ይጀምራል።
የሃይማኖት መሪዎች ድምጻቸውን መስጠትና የርህራሄ፣ የቬጀታሪያን ህይወት በመሩት እንደነ ኢየሱስ፣ ሙሃመድ፡ ቡድሃ፣ ጉሩ ናናክ ወዘተ፣ወዘተ፣በተከበሩ ጥንታዊ መስራቾች አስተምሮት መሰረት በአርአያነት በመኖር መንገዱን ሊመሩ ይችላሉ። የነዚህ ማስተሮች አስተምሮት የያዙ መጽሃፍት ሁሉም የሚያስተላልፉት መልእክት እርስ በርስ እንድንን ከባከ፣ እንድን ተሳሰብ የምድራችን መልካም ጠባቂ እንድንሆን ነው።
በክርስቲያን መጽሃፍ ቅድስ እንዲ ይላል፡ “ስጋ ለሆድ፣ ሆድም ለስጋ፣ ነገር ግን እግዚኣብሄር ሁሉቱንም ያጠፋቸዋል።” የቡድሂስቱ ማሃፓሪኒቫና ሱትራ ደግሞ እንዲህ ይላል፡ “ስጋ መብላት የርህራሄን ዘር ይገድላል/ያጠፋል እናም ማንኛውም የስጋ ተመጋቢዎች ተግባር፣ ከሰውነታቸው በሚወጣው የስጋ ሽታ አማካይነት ሁሉንም ፍጥረታት ያስበረግጋል።”
ክርስቲያን፣ ቡድሂዝም፣ ህንዱይዝም፣ እሰላም ማንኛውም ሃይማኖት የምነግረን፡ እንስሳትን አትብሉ ምክኒያቱም የእግዚኣብሄር ፍጥረት ናቸውና።
የቬጀታሪያን (ቪጋን) መንፈሳዊ ጎኑ/ገጽታው በጣም ግልጽነው - ያለ-አመጽ - "አትግደል።" እግዚኣብሄር ይህንን ሲነግረን፣ "አትግደል፣" ሰው አትግደል ሳይሆን፣ ሁሉንም ፍጥረታት አትግደል ነው።
በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ቬጀከተታሪያን (ቪጋን) መሆን እንዳለብን በግልጽ ተነግሯል። በሳይንሳዊ ምክኒያትም ቬጀታሪያን (ቪጋን) መሆን እንዳለብን የተረጋገጠ ነው። አሁንም ከጤና አኳያም ቬጀታሪያን (ቪጋን) መሆን እንዳለብን ነው። በኢኮኖሚያችንም ምክኒያትም ቬጀታሪያን (ቪጋን) መሆን ነው ያለብን። ከርህሩህነት አንጻርም ቬጀታሪያን (ቪጋን) መሆን አለብን። አለምን ለመታደግም ቬጀታሪያን (ቪጋን) መሆን እንዳለብን ግልጽ ነው።
አንዳንድ የምርምር ውጤቶች እንደሚያመለክቱት የምእራቡ ህዝብ በሳምንት አንድ ጊዜ ቬጀታሪያን (ቪጋን) ቢመገብ፣ በያመቱ 60-ሚሊዮን ሰዎችን ማዳን እንችል ነበር። ስለዚህ ጀግና ሁን፣ በሁሉም ምክኒያቶች ቬጀታሪያን (ቪጋን) ሁን። ነገር ግን ለምን ቬጀታሪያን (ቪጋን)? ብላችሁ ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ። ቬጀታሪያን (ቪጋን) ትክክል ነው ምክኒያቱም ውስጣችን ያለው ፈጣሪ/እግዚኣብሄር ይፈልገዋልና።
ስለዚህ የአካባቢ ችግሮችን ለመፍታት የሃይማኖት ደጋፊዎችን ልናስታውሳቸው የሚገባን እነዚህን ትምህርቶች በተግባር ላይ ማዋልን ነው። ዋነኛው ፍቱን ተግገባር፣ ዜጎች ወዲያወኑ ሊተገብሩት የሚችሉት - ቬጅ መሆን/ሁን። እንሚታወቀው ሌላው “አረንጓዴ ሁን” ማለት አካባቢውን ተንከባከብ፣ በቁጠባ ተጠቀም/ አታባክን።
ቬጅ መሆን በእውነተኛ የሃይማኖት እምነታችን መኖር ነው። ስጋን መተውና እጽዋትን-መሰረት ያደረግ የህይወት ዘዴ መከተል ማለት የሩህርህነት መርህን ተግባር ላይ ማዋል ነው።
ያለ-አመጽ/ በሰላም እናነባለን፣ እንኖረዋለን፣ በፍጹምነት ይህን መተግበር ይገባናል። አንገድልም፣ አነሰርቅም ነገር ግን ህይወትን እንታደጋለ፣ የበጎ አድራጎት ስራም እንሰራለን። እርሰበረሳችን እንፋቃቀራለን፣ እንረዳዳለን የሞራል ደረጃችንን ከፍ እናደርጋለን። የኛ ያልሆነውን አንወስድም። በአንጻሩ ለተቸገሩት የራሳችንን እንሰጣለን እንጂ። ሁሉም ሃይማኖቶች የሚያስተምን ይህንኑ ነው፣ ይህንን መተግበር ነው የሚጠበቅብን።
ወደኋላ ተመልሰን የጥንት የማስተሮች የነገሩንን፣ ነቢያት ያስተማሩንን ማየት አለብን። ይህን ነው ማድረግ ያለብን። እንዲያውም ምንም መስራት አይጠበቅብንም። በሰላም ለመኖር መጽሃፍቱ በቂያችን ናቸው፣ ነገር ግን ከተገበርነው ነው።