III. መልካም/የተከበረ ትምህርት የሚያስተምረው ጤናማ የአረንጓዴ የህይወት
መንገድን ነው
ቤታችን በመቃጠል ላይ ነው። ፕላኔታችን በመጥፋት ላይ ናት። እናንተ መምህራን/አስተማሪዎች መረጃ ልትሰጧቸው ይገባል። አስችኳይ እርምጃ መውሰድ አለባችሁ። ማድረግ የሚገባቸውን ንገሯቸው። ወደ ተሻለ ህይወት ምሯቸው። ከናንተ ብዙ ይጠብቃሉ፣ ያመሰግኗችኋልም።
ለህጻነቱ መረጃ ስጥ
ልንነግራቸው ይገባል። የአለም ሙቀት መጨመርን በተመለከተ፣ ፕላኔታችን ላይ ምን እየደረሰ እንደሆነና የሚፈለገውን ዝግጅት እንዲያደርጉና የሙቀት መጨመርን መቀነስ፣ ብሎም ለማቆም በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩለቸውን ሚና እንዲጫወቱ በቀጥታና በታማኝነት ልንነግራቸው ይገባል።
ህጻናት ልባቸው ንጹህና በጣም የዋህ ነው፣ የአረጋዊያንን መመሪያ በቀላሉ ሊቀበሉ ይችላሉ። ስለዚህ ለፕላኔታችን የሚበጀውን መልካሙ ነገር ምን እንደሆነ በጥኖቃቄ ልንነግራቸው ይገባል።
ከገለጻው በኋላ ወዲያው ይረዱና የሚፈለግባቸውን ወዲያው ሊያከናውኑ ይነሳሉ። ምክኒያቱም ህጻናት ለታላላቆቻቸው ትልቅ ክብር ስላላቸው ነው። ነገር ግን መጀመሪያ የሚከተሉት አይነት የተግባር አርኣያ ሆነን መገኘት አለብን።

Vegan children enjoy a happy meal of fruits,
vegetables and vegan apple pie.
እኛ አረጋዊያነን ነን፣ በመጀመሪያ ራሳችን አርኣያ መሆን አለብን፣ ከዚያም ማስተማር እንችላለን ምክኒያቱም ህጻናቱ ከምሳሌዎቹ ስለሚማሩ ነው፣ ከንግግር ይልቅ ከአንጸባራቂ ምሳሌዎች ነው የበለጠ የሚማሩት። ስለሆነም እንደ አዋቂዎች አንጸባራቂ ምሳሌ መሆን አለብን፣ የሚቻለንን ማድረግ አለብን።
ህጻናቱ ለመውረስ እንዲችሉ የምንሰራው ነገር ለፕላኔቷ መልካም የሆነውን ነው። ትልቅ መስዋእት ቢጠይቀንም አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ማድረግ አለብን፣ በእውነቱ ግነ ምንም መስዋእት የምናደርገው ነገር የለም። ማድረግ ያለብን ያን የስጋ ቁራጭ መጣልና በቶፉ መተካት ነው።
ወጣቱን ትውልድ ማንቀሳቀስ
አሁን ከሚስተዋለው አስቸኳይ ጉዳይ ይልቅ የወጣቶች ስሜትና ፍላጎት በፋሽንና በሌሎች ነገርች ላይ የተንጠለጠለ ይመስላል። ነገር ግነ አንዳንድ ገጊዜ አእምሯቸው ክፍት የሆነ ሰዎችም አሉ። እንተሌጀንት የሆኑ፣ ቀለል የሚሉ፣ ተቀባይና ታማኝ የሆኑ ሰዎች። አንዴ የአለም ሙቀት መጨመር ጋር ከተዋወቁ አንድ ነገር ለማድረግ ይወስናሉ። ይገርምሃል፣ በተለይ የሚሰሩት ነገር በእውነቱ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ከተረዱ እርምጃ ለመውሰድ የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ። አንተን የመሰለ መልካም መሪ ይፈልጋሉ።.
በቅርቡ የተደረጉ ሁለት ጥናቶች ያሳዩት ወጣት ሰዎች ፍቃደኞችና ራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ መሆናቸውን ነው።139 ይህ ማለት የዚህ እድሜ ባለቤተ የሆኑ ወታት ሰዎች ትልቅ ጉልበት/ሃይል ያላቸውና ጥቂቶቹም ለሌላው አሳቢ የሆኑ ናቸው።
ስለዚህ አሳቢና ፍቅራቸውን የሚያሳዩበትን የተግባር መንገድ እንዲያገኙ በመርዳት ልታበረታታ ትችላለህ። የአለም ሙቀት መጨመር ምን ያህል እውነትም አጣዳፊ ጉዳይ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ልትረዳቸው ትችላለህ። የአለም ሙቀት መጨመር ሰብኣዊ ገጽታውን አሳያቸው፣ በዚህ ምክኒያት የሚደርሰውን እውነተኛ የሰዎችና የእንስሳት ስቃይ፣ ለምሳሌ የሚፈናቀሉትን ወይም ለመፈናቀል ያቀዱትን የደሴት አገር ቤተሰቦች/ዜጎችን፣ ቤቶቻቸውን ሊያሰምጥ የሚንቀሳቀሰውን ውሃ በመፍራት - ወይም በጥቂቶቹ አጋጣሚዎች በባህር ከፍታ መጨመር የተከሰተውን።
ወይም በማረጃዎች የእንስሳትኢሰብኣዊ አያያዝ ወይም ቁንጅና ቤተ-ሙከራዎች - ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ፊልሞች አሉ። ማክሰኞ ማክሰኞ በሱፕሮም ማስተር ቴሌቭዥን “በእንስሳት ላይ የሚደረግ ጭካኔን አቁም” በሚባል ርእስ ተከታታይ ፕሮግራም አቅርበናል። ይህ የማይታሰብ ጭካኔ ነው። ይህ ከሰው የሞራል ደረጃ ውጪ ነው። ከደረጃችን፣ ከክብራችን በታች በመውረድ እንደዚህ አይነቱን ድርጊት በእንስሳት ላይ ፈጽመናል። እነዚህን ጥቂት ሀቆች፣ ለሰው ላንቃ ሲባል፣ በእንስሳት ላይ ስለሚደርሰው ሰቆቃ ብታሳያቸው አንድ ነገር እንዲያደርጉ የተማሪዎችን ርህራሄ ታነቃለህ።
ወይም ደግሞ የሚሰደዱ ወፎች የማረፊያ ጎጆኣቸውን ለመስራት ብዙ ለመብረር የሚገደዱበት፣ የዋልታ ድቦችም የማረፊያ በረዶ ለማግኘት ብዙ መዋኘት የሚኖርባቸው፣ እንዳንዴም ሰምጦው ሊቀሩ ይችላል፣ ወይም የጎረቤት አገር እየጨመረ የመጣ ጎርፍ ለማስተናገድ የሚገደዱበት ሁኔታ፣ በርካታ አደጋዎች፣ ወዘተ፣ ወዘተ ልታሳያቸው ትችላለህ።
የአየር ንብረት ለውጥ እንዴት ህይወትን እንደሚነካ፣ እንስሳቱን፣ ሰዎችንና የራሳቸውን ህይወት ጭምር እንዴት እንደሚነካ ንገራቸው። ከዚያም ወጣቱ የአየር ንብረት ለውጡን ማስቆም ከሁሉም የሚቀድም፣ እስካሁን ሲያስቀድም ከነበሩትን ነገሮች ሁሉ፣ ከስራቸውም በፊት፣ ከገንዘብ በፊት፣ ከመዝናናትም በፊት፣ የሚታይ መሆኑን ይገነዘባል፣ ምክኒያቱም ያልተረጋጋ‹ችና፣ አስተማማኝ የአየር ንብረትና ህይወት የሌላት ፕላኔት፣ ማንም በምንም ሊገለገልባት፣ ሊጠቀምባት፣ ሊደሰትባትና የሚፈልገውን ነገር ሊያደርግ የማይችልባት ናትና።
ነገር ግን ወጣቱን ሰው አሁንም ተስፋችን ተሟጦ አለመሄዱን ደግሞ ማሳየት ይገባል፣ አሁንም ፕላኔቷን መታደግ እንችላለን። ይህ ልትነግራቸው ትችላለህ። ይህ ጀግንነታቸውን ሊያሳዩ የሚችሉበት መልካም አጋጠሚ ነው፣ ቪጋን በመሆንና የዚህን መፍትሄ መልእክት በማሰራጨት። ህይወትን ሊያድኑ ይችላሉ፣ የራሳቸውንም ጨምሮ፣ በመላው አለም ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ህይወትና በአለም ዙሪያ የሚገኙ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን እንስሳትንም።
ቪጋን የመሆንን በርካታ ጥቅሞች/ፋይዳዎች - ለግልህ፣ ለእንስሳቱ፣ ለተራቡ ህዝቦች፣ ለተራቡ ህጻናት - ብታስረዳቸው፣ ይወዳሉ፣ ይደነቃሉም ምክኒያቱም ለውጥ ሊያመጡ እንሚችሉ ይረዳሉና።
ነገሩ ከገባቸው፣ ህይወታቸውን ለመለወጥ ወጣቶችብዙ ጊዜ ዝግጁ ናቸው። በእድሜ ክልሉም፣ ብዙ ጊዜ፣ ቬጀታሪያንነት ጥሩ፣ ትክክል መሆኑን በቅድሚያ የሚያዩ ናቸው። ስለዚህ ለአለም ሙቀት መጨመር መፍትሄ ማበጀት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ በምክኒያት ካስረዳናቸው ይነሳሳሉ። ይደግፉሃል። ከጎንህ ይሆናሉ። ይተገብሩታልም።

በት/ቤት ቪጋን ምሳን ለማስጀመር እርዳ
---------------------------------------------------------------------------------------------------
የጤናማ የት/ቤት ምሳና መክሰስ ፕሮግራምን አስመልክቶ አሁን በርካታ ጥናቶች ይገኛሉ። ህጻነት የበለጠ ሃሳባቸውን መሰብሰብ የሚችሉት ትኩስ ፍራፍሬና አትክልት ሲመገቡ መሆኑ ታውቋል።
የአሜሪካዋ ቀዳማዊ እመቤት አሁን ዘወትር ትኩስ ፍራፍሬና አትክልትን ለአሜሪካ ህጻናት እያስተዋወቀች ትገኛለች። እናም ት/ቤቶች እነዚህን ፋይዳዎች እንዲረዱ ከረዳን በሰፊው ሊጠቀሙበት ይችላሉ። በአሁኑ ጊዜ በርካታ ት/ቤቶችና ወላጆች በት/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ አትክልት ወይም በየመኖሪያቸው ከልጆቹ ጋር የጓሮ አትክልት መትከል/መዝራት ጀምረዋል፣ ህጻነቱም ይህንን ስራ ወደውታል፣ ራሳቸው ካመረቱት የበለጠ አትክልት እየበሉ ናቸውና።
ቪጋን በመሆን ፕላኔታችን እየፈወስንና እየታደግናት መሆኑን፣ ወላጆችን መርዳት መሆኑን፣ ራሳቸውንና፣ ሁሉንም ሌሎች ህይወቶችን መርዳት መሆኑን ለልጆቻችን መንገር አለብን። ልጆች በእውነት ከልባቸው አፍቃሪዎች ናቸው። ስለዚህ ቪጋን በመሆን ብዙ ህይወቶችን እንደሚያድኑ ከተረዱ ለመተግበር በጣም፣ በጣም ፈቃደኛ ይሆናሉ፣ ይመቻቸዋል። ለልጆቻችን ትተን ማለፍ ያለብን አለም አረንጓዴና ለም እንድትሆን እንፈልጋለን። ሰዎችና እንስሳት በሰላም አብረው የሚኖሩባት አለም ትተን ማለፍ መቻል አለብን። እነርሱም ይህን እውን ለማድረግ ለመርዳት ይወዳሉ።