V. ኦርጋኒክ ቪጋንነት መንፈሳዊ/መለኮታዊ እንቅስቃስ ነው
አነስተኛ ገበሬዎችም በቬጀታሪያንነት ዙሪያ መለኮታዊ ድርሻ አላቸው። የቪጋን አመጋገብ ራሱ የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ አካል ነው፣ ምክኒያቱም የተከበሩ ሰብኣዊ ተግባራትንና የርህራሄና የፍቅር አሴታችንነ የምናሳይበት ብቸኛው መገለጫ ስለሆነ ነው። የመጽና መጥፎ ካርማችንን አዙሪት መቀልበስ የምንችልበት መንገድም ነው። “የዘራኸውን ታጭዳለህ።” እናም ከአፍራሽ ቁሳዊ አወጥቶን በፍቅር፣በክብካቤና ምህረት ማእቀፍ ውስጥ ያስገባናል።
ስለዚህ የኦርጋኒክ ቪጋን ገበሬዎች ሌሎች ቁጥር ስፍር የሌላቸውን በመደገፍ ታላላቅ በረከት በጣም ዝቅተኛ ወይም ምንም አመጽ የሌለበትን ምግብ በማቅረብ ሌሎች ቁጥር ስፍር የሌላቸውን እየደገፉ ለረሳቸውም መንፈሳዊ በረከትነ ይጎናጸፋሉ።
አነስተኛ ገበሬዎችም በቬጀታሪያንነት ዙሪያ መለኮታዊ ድርሻ አላቸው።
የኦርጋኒክ ቪጋኒክ የኑሮ/ህይወት ዘይቤ አሂምሳን (ኢ,አመጻዊነት) መከተል ነው
ሌሎችን በማኖር ከኖርን፣ ሌሎቹን ፍጥረታት ሁሉ እንደራሳችን ከወደድን ይህ በራሱ ከፍተኛ መንፈሳዊ ምጥቀት ነው። ይህም ከምድር ታላላቅ ሃይማኖቶች አስተምሮት የወጣ አይደለም። ይህ መንግስተ-ሰማያትን ያስደስታል። ይህ እኛም ህይወትን ሁሉ እንድናከብርና እንድንንከባከብ ያስችለናል።
አየህ? ለዚህ ነው ሰላም የሚሰማን። በዙራህ ከሚገኙ፣ ከሁሉም ጋር መያያዝህ የሰመሃል ምክኒያቱም ሁሉም ከህይወት ጋር ልባቸው ይመታልና። ምድር ከፍቅርና ህይወት፣ ከዛፎች፣ ከእጽዋት ጋር ሁሉም በፍቅረ ህይወትን ይተነፍሳሉ። ዛፍ ስር በምንቀመጥበት ጊዜ ይህን ተንከባካቢ የፍቅር ሃይል ይሰማናል። ጣፋጭ ፍሬ በምንገምጥበት ወቅት፣ ይህ ከዛፉ በጣፋጭ ምግብነት የሚተላለፍልን ያልተገደበ ፍቅር ፍሰት ይሰማናል።
በኦርጋኒክ፣ ቪጋን ውስጥ ካለን ወይም በኦርጋኒክ ቪጋን አሰራር ዘዴ የምናበቅል/ተክል ከሆነ፣ የበለጠ ፍቅር ከተፈጥሮ፣ ከፕላኔት ምድር፣ ከዛፎች፣ ከሳር ጫፎች፣ ከአበቦች ይሰማናል። ከምንተነፍሰው አየርም ትልቅ ፍቅር ይሰማናል/እናገኛለበን። ከምንራመድበት መሬትም/ምድርም ትልቅ ፍቅር ይሰማናል። ይህን በምድር/በሰው ቋንቋ መግለጽ አይቻለንም። ግን ሊሰማን ይገባል። እኔ ሁልጊዜም ይሰማኛል፣ ነገር ግን ይህ መሎታዊ መልእክት ወደ ሌሎች ሰዎች ለማስተላለፍ አልችልም። እያንዳንዱ ሰው ራሱ ማየት/መሞከር አለበት።
በርሁርሁነት አንዴ ከተመለስን መንግስተ-ሰማያት ባቀደው የቪጋን የህይወት ዘይቤ የበለጠና ተጨማሪ ፍቅርና መተሳሰር ሁል ጊዜ ይሰማናል። ያለ-አመጽ/አሂምሳ ማለት ማንንም/ሌሎቹን ግልጽ ስሜት ያላቸውን ፍጥረታት አለጉዳት፣ በቪጋን አመጋገብ መጀመር ነው። ኦርጋኒክ፣ ቪጋን አመጋገብ እጅግ በጣም ጥሩ ነው። የዘራነውን እናጭዳለን። እነዚህን መልካም ዘሮች በምድር ላይ ከዘራን፣ በልባችን ውስጥ ከያዝን፣ እንደ ቪጋን የእንስሳትን ተዋጽኦዎች ማስወገድ አለብን።
ለምሳሌ አብዛኛው የወተት ምርቶች የበርካታ ስቃይ መንስኤ ናቸው፣ በመጀመሪያ እናት ላሞቹ እንደወለዱ ወዲያው ከጥጆቹ ይለያሉ። እኔንም ጨምሮ፣ ይህንን ብዙ ሰው አያውቅም። ከዚያም እነዚህ ጨቅላ ጥጆች/ጨቅላ ላሞች ይገደላሉ። የናታቸውን ወተትና ፍቅር ተነፍገው እንደተለዩ ወዲያው ለግድያ ይዳረጋሉ። ከዚያም ወተት ለሰው ለመስጠት ብቻ እናትየዋ በጉልበት ተሰንጋ ከመሳሪያ/ማሽን ጋር ተጠፍራ ለህመምና ስቃይ ትዳረጋለች።
የኦረጋኒክ ቪጋን እርሻ ጸረ-ተባይ መርዝ ስለማይጠቀምና ከእንስሳት ማርባት፣ ወተትና ከማንኛውም ጎጂ ተግባራት
ጋር ምንም ግንኙነት ስለሌለው በመንግስተ-ሰማያት እቅድና እንደ ቡድህዝምና ኮንፊዩሽዩዝምና በመጽሃፍቶቻቸው እንደ ተጻፈውና በበርካታ መንፈሳዊ መስመሮችና ሃይማኖታዊ አስተምሮት የርህራሄ ተግባር ተብሎ የሚወሰድ ነው።