• ምእራፍ አራት. የቪጋን ፖሊሲና ህግ ማውጣት > III. የተሳካ የእንስሳት አርቢዎች ወደ አማራጭ ስራዎች/ሙያዎች


      • III.  
        የተሳካ የእንስሳት አርቢዎች ወደ አማራጭ ስራዎች/ሙያዎች
              ሽግግር


        በአሜሪካ

        አንድ አሜሪካዊ የአሳማ አርቢ ገበሬ በቆሻሻ፣ መፈናፈኛ በሌለው የፋብሪካ ማጎሪያ ውስጥ የታጨቁ የብዙ አሳማዎች ባለቤት ነበር። በታዋቂው የቪጋን ጸሃፊ በጆን ሮቢንስ ከተጎበኘ በኋላ ታዋቂው የአይስ ክሬም ወራሽ ባለ ብዙ ሚሊዮን ዶላር የአባቱን የአይስ ክሬውም ቢዝነስ በመተው የቪጋን ን አለም ተቀላቀለ። ይህን ትልቅ የአሳማ እርባታ ጎበኘ፣ ከዚያም ይህ ገበሬ በድንገት በህጻንነቱ ጓደኘው የነበረ አንድ አሳማ ይወድ እንደነበረ አስታውሶ፣ ይህንን በወላጆቹና በህብረተሰቡ ግፊት እንድክድና እንዲረሳ ማደረጉን አስታወሰ።124

        ጉዳዩን እንደተረዳ ለአንድም ተጨማሪ ሴከንድ እንኳን ሚስኪነፀ አሳማዎቹን ሊያንገላታ አልፈቀደም። ለማቌረጥም ወሰነ። አሳመዎችን ማርባት ትቶ አንድ ትንሽ የኦርጋኒክ እርሻ ገዝቶ ኦርጋኒክ አትክልቶችን መሸጥ ጀመረ፣ እናም ጥሩ በመስራት ላይ ይገኛል። ኑሮውን ቀጥሏል። በንቁነት ልቡ የተሞላ ነው።

        ሌላም ሰው አለ፣ ሰሰር የቤት አሳማዎች ያሉት - አስሩን አሳማዎች ከቀድሞ እርባታ እርሻው ያመጣቸው ናቸው - እንስሳቱን ወደ ት/ቤት በመውሰድ ልጆች አሳማዎች ምን ያህል  አዋቂዎች/እንተሊጀንትና ወዳጅ እንደሆኑና ልጆች እነርሱን መብላት እንደሌለባቸው ለማሳየት ነው። ከእንግዲህ ወዲህ አሳማ አለማርባቱ ብቻ ሳይሆን ተቃራኒ አቅጣጨ በመከተል ለእንስሳቱ በቆርቆርና መንከባከብን መረጠ።

        ሌላው የቴክሳሱ አርቢ ነው። በቴክሳስ ብዙ ላሞችን ማርባት የተለመደ ነው፣ ካውቦይ የተባለው ቃል የተገኘው ከዚያ ነው። ሰውየው የላሞች እርባታ አለው፣ ነገር ግነ ካንሰር ከስጋ ስለያዘው ስራውን በድንገት ቀየረ። ከታከመ በኋላ ቪጋን ሆነ፣ አሁን የእንስሳት መብት ተከራካሪ ነው። ወደ ተለያዩ የቦታዎች በመሄድ ያስተምራል፣ ለሰዎች እውነቱን ይነግራቸዋል፣ ትክክለኛውን እውነት፣ መራሩን እውነት፣ የእንስሳት እርባታ መጥፎነት። ለእንስሳቱ ጠንካራ ተከራካሪ ነው። ስሙ ሀዋርድ ሊማን ይባላል። እንዴ ወይም ሁለቴ የሱፕሪየም ማስተር ቴሌዥን ታላቅ እንግዳ ሆኖ ቀርቧል።

         

        በመካከለኛው ምስራቅ

        በቅርቡ በኢራን የላም ወተት ልማት ገበሬ - ታሪኩን አስነብቦናል፣ እርሱም ስራውንና ሙያውን ለመቀየር በመወሰን ፕላኔቷን ለመርዳት በሂሊናው መመራት ጀምሯል። በመሆኑም ለላሞቹ ደህንነትና የተበረ ኑሮ ለማረጋገጥ  እንስሳቱን በጉድፈቻ ለመስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው። እናም አሁን በቪገን ምግብ ቤት ውስጥ በመስራት ላይ ይገኘል።


        በእስያ

        ሌላው የፎርሞሳው (ታይዋን)ታሪክ ነው፣ የአሳማ አርቢው የሱፕሪየም ማስተር ቴሌዥንን ከመከታተለ በኋላ አካባቢውን ለመጠበቅና የራሱንና የቤተሰቡን መጥፎ ካርማ ለማስወገድ እንዲችል ቪጋን ሆነ። በአሁኑ ወቅት አሳማዎቹን እንደቤተሰብ አባላት በማቀማጠል አብሯቸው ይኖራል። እርሱም ወደ ሌላ የእርሻ ስራ ተሸጋግሮ ይገኛል።

        በሁሉም ምሳሌዎች ሰዎቹ ጠጥሩ ሁኔታ እየሰሩ የተሻለ ኑሮ በመምራት ላይ ናቸው። በመጀመሪያ ስርና መያን መቀየር አስቸጋሪ መስሎ ሊታይ ይችላል፣ ድምዳሜው ግነ መልካም ኦደሆነ የበለጠ ጥሩ እንደሆነ ተመክክቷል። የልብ ነጻነት፣ የመንፈስ ነጻነትና የቤተሰብ ደስታና ጤንነት ነው።

         



         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *