ቪጋን መሆን ዋነኛ የሙቀት አማቂ የሆነውን ሚቴን ጋዝን፣ ከ72 ጊዜ በላይ የካርቦንዳዮክሳይድ አጥፍ አቅም ያለውን፣ ከከባቢ አየር ወዲያውኑ የማስወገድ ውጤት ይኖረዋል። ቨጋን መሆን በርገጥ የበረሃነት መስፋፋትንን ያዘገየዋል፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንንም፣ እንደሀይቅና ወንዞች ያሉትን ያተርፍልናል፣ ደኖቻችንንም ይጠብቅልናል።
ሌሎች የአረንጓዴማነት የመፍትሄ እርምጃዎችንም ማለትም እንደ ዛፎችን መትክል፣ ወይም ወደ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂን መጠቀም መውሰድ ይቻላል፣ ነገር ግን እነዚህ እርምጃዎች ውጤት ለማምታት ረዘም ያለ ጊዜን ይጠይቃሉ። የቬጄተሪያን አመጋገብ ፈጣን እንዲሁም መግደል የመሳሰሉ መጥፎ ካርማን ይቀንሳል፣ ስለዚህም ጥቅሙ እጅግ ከፍ ያለ ነው።
70% የሚሆነውን ንጹህ ውሃ መቆጠብ/ማዳን፣ 70% የአማዞን ደንን ለእንሰሳት መዋያ ከመመንጠር ማዳን እንችላለን። በአመት እስከ 3.5-ሚሊዮን ሄክታር የሚሆን መሬት ነጻ ማድረግ እንችላለን። 760-ሚሊዮን ቶን የምግብ እህልን - ይገርማል ከግማሽ የአለም የምግብ እህል አቅርቦት በላይ የሚሆነውን። ከ2/3ኛ በታች የሆነ የነዳጅ ሃይል ብቻ ይጠቀማል ከስጋ ማምረት ጋር ሲነጻጸር፣ ካልተጣራ የእንሰሳት ቆሻሻ መበከልን ይቀንሳል፣ ንጹህ አየር ያስገኛል፣ 4.5ቶን የሚጠጋ በካይ ጋዝ ምንጮችን ከያንዳንዱ የአሜሪካ ቤተሰብ በአመት ያስቀራል። እናም 80% የሚሆነውን የአለምን ሙቀት ያስቀራል።
ስለገንዘብ ቁጠባም ብናነሳ፣ የኔዘርላንድ የሳይንስ ሊቃውንት እንደደረሱበት የአለምን ሙቀት ለማስቆም ከተገመተው የ$40 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር፣ 80%ውን ቪጋን በመሆን ማዳን ማዳን ይቻላል። ይህ $32 ትሪሊዮን ከስጋ መመገብ ፊታችንን በማዞርና የእጽዋትን ውጤቶች በመጠቀም የምናድነው ገንዘብ ነው።
ምድር ራሷን የምትጠግንበት ዘዴ አላት። እኛ ነን ፕላኔቷን ያጨናነቅናት እንጂ። በጣም በከልናት የካርማ መኣት ፈጥረን አከናነብናት። ስለዚህም፣ በነዋሪዎቿ መጥፎ ካርማ ምክኒያት ምድሪቱ ራሷን ልትጠግን አልቻለችም። ወዲያው ይህንን መጥፎ የመግደል ተግባር እንዳቆምን ምድሪቷ ዘወር በማለት ራሷን የመጠገን እድል በማግኘት ታገግማለች፣ ታብባለች፣ ትራባለች፣ ትለመልማለች፣ ህይወትም እንደገና ይቀጥላል። ሁሉም ነገር በካርማ ዙሪያ ያጠነጥናል ማለት ነው። ምድርን ከአቅሟ በላይ ተጫናት፣ ስለዚሀ ድርጊታችንን መቀልበስ ይጠበቅብናል ማለት ነው።
እንሰሳትን መግደል መጥፎ ካርማ ያመጣል
“ሰው የዘራውን ያጭዳል” “ተመሳሳይ ነገሮች ይሳሳባሉ።” በሳይንሳዊ አባባል፣ በመንፈሳዊ አባባል፣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል ማለት ነው። በምድራችን ዙሪያ የተከሰቱ አደጋዎች ሁሉ የሰው ልጆች አብረዋቸው ከሚኖሩት (እንሰሳትን ጨምሮ) ጋር ከሚያሳዩትና ከሚያደርጉት ክፋት ጋር የተያያዙ ናቸው። ይህ እንግዲህ ምንም ላልበደሉንና ንጹሃን ላይ ለፈጸምነው ግፍ የምንከፍለው ዋጋ ነው፣ እነርሱም (እንሰሳት) ሊረዱንና ጊዜያችንን ሊያደምቁ ወደ ምድር የተላኩ የእግዚኣብሄር ልጆች ናቸው እኮ።
ነገሩ የቴክኒክ ጉዳይ አይደለም፣ በቴከኒክ ላይ ብቻ ተዘፍቀን የሚያስቀረን ነገር የለም። የአጸፋ ጉዳይ ነው፣ የድርጊትና የአጸፋ ምላሽ ጉዳይን ነው ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን። የግድያ የደም ዋጋ፣ የአመጽ ዋጋ ከማንኛውም መኪና፣ የጸሃይ ፍንዳታ ወይም ከውቅያኖስ ፍንዳታ ወይም ከድምራቸው እጅግ የከበደ ነው ምክኒያቱም ለድርጊታችን ተጠያቂዎቹ እኛው ነንና። ማንኛውም ድርጊት የአጸፋ ምላሽ ያስከትላል። ስለዚህ ማድረግ ያለብን ግድያን ማቆም ብቻ ነው። በቃ ሰውና እንሰሳትን መግደል ማቆም አለብን።
ማቆም አለብን። እናም ሌላው ማንኛውም ነገር በድንገት ግልጽ ይሆናል።
እናም የአየር ንብረት ችግርን ለመቅረፍ የተሻለ ቴክኒካዊ መንገድ ማገኘት እንችላለን። የጸሃይ መፈንዳትም (ወላፈን) ሊቆም ይችላል። በቃ ውቅያኖስም አይፈነዳም። ታይፉንም (አደገኛ የባህር ላይ አውሎ ንፋስ) ሊቆም ይችላል። ሳይክሎንና የባህር ውሽንፍርም ጸጥ ይላሉ። የመሬት መንቀጥቀጥም በቃ ቀጥ ይላል። ማንናውም ነገር ወደ ሰላማዊ ኑሮ ይመለሳል። ምክኒያቱም ሰላምን ፈጥረናልና ሰላም ይኖረናል፣ ሰላም በሰዎች መካከል ብቻ ሳይሆን በሁሉም ነዋሪዎች መካከል ይፈጠራል። ለዚህ ነው እንግዲህ እኔ የቬጀተሪያንን ምግብ፣ አመጋገብ ጉዳይ አጥብቄ ሳራምድ የቆየሁት። ይህ የሰው ልጅ የሞራል ህግ ነው። የትልቅ ሰው መለያ ምልክት ነው።
የሩህሩህነት ሃይል ማንኛውንም ነገር መለወጥ ይችላል
የቬጄተሪያን ምግብ መልካም ነው፣ አስደሳች ሃይል ይሰጥሃል፣ ይህም በተራው ተጨማሪ ደስታን ይወልዳል፣ ተጨማሪ ደስታን ይስባል እናም ደስተኛ ስትሆን ሁሉም ነገር የተሻለ ይሆናል። የተሻለ ታስባለህ፣ የተሻለ የአጸፋ ምላሽ ይኖረሃል፣ ህይወትህ የተሻለ ይሆናል። ልጆችህ የተሻሉ ይሆናሉ፣ ሁሉም ነገር የተሻለ ይሆናል።
እናም ከፍተኛው የጋራ፣ የመላው አለም ቅንና የፍቅር ሃይል ወደኛ እየገሰገሰ ያለውን ጨለማ ይገፋልናል። ይህ ነው ያለኝ ብቸኛው መፍትሄ።
አያችሁ፣ ሁሉንም ነገር ለመለወጥ የሚስችለን ሃይል አለን፣ በዙሪያችን እየተከናወነ ያለውን ነገር ማስቆም እንችላለን፣ ሃይሉን መጠቀም ይገባናል። ለሁሉም ሲባል መጠቀም አለብን። በአለም ላይ ላሉት መላው ፍጥረታት ጥቅም ሲባል ሃይላችንን መጠቀም መቻል አለብን። ሀሳባችን፣ ድርጊታችን፣ የተሻለች ፕላኔት፣ ስጋት የሌለበት ህይወት፣ የታደገች አለም እንደምንፈልግ ለዩኒቨርሳል ሃይል መልእክቱን ማስተላለፍ አለበት። ያኔ የዩኒቨርሳል ሃይሉም ይህንኑ ይሰጠናል፣ ተመሳሳይ ምላሽ ይሰጠናል።
ነገር ግን ተግባራችን ከዚህ ሃይል ጋር የተወሃደ መሆን አለበት። መልካም ነገር ከፈለግን መልካሙን ማድረግ አለብን። ህይወትን ከፈለግን፣ ህይወትን ማትረፍ አለብን። ስለዚህም የምንፈጥረው መልካም ሃይል እነዚህን ነገሮች መፈረም ይችላል ብቻም ሳይሆን ብዙ ታምራትን ይሰራል። እንደመላው አለም ያለን ርህራሄና ፍቅር ብዙ፣ ብዙ ታምራትን መፍጠር፣ ማድረግ ይችላል።
የተፈጥሮን ህግጋት ከጠበቅን የምንፈልገውን ማንኛውንም ነገር መፍጠር እንችላለን። ይህ ነው እንግዲህ ቪጋን የመሆን ሃይል። ምክኒያቱም ህይወትን እናተርፋለን፣ ህይወትን እንፈልጋለን፣ ገንቢ ሃይል እንፈልጋለን፣ ጥፋትን አንፈልግም። ስለዚህ ቪጋን ተገቢ ምላሽ ነው፣ መፍትሄው ቪጋን መሆን ነው።
የሰው ልጅ በመንፈስ የበለጠ ከፍ ከፍ እያለ ከሄደ፣ የአለም ሙቀት መጨመር እየቀነሰ ይሄዳል። የሰው ልጅ በመንፈሳዊነት እየመጠቀ ከሄደ ለሁሉም ሰው የበለጠ ፍቅር ይኖረዋል፣ በማንኛውም ጊዜ ለሁሉም ፍጡሮች ፍቅር ይኖረዋል፣ በሁሉም ቦታ የአለም ሙቀት በየቀኑ እየቀነሰ ሄዶ በመጨረሻም እስካካተው ሊጠፋ ይችላል። ከዚያም በኋላ ሁሉም በአለም ላይ በደስታና እርስ በርስ በመፋቀር በሰላም መሆር ይጀምራል። ለዚህ እንግዲህ ሁሉም ቶሎ መንቃት አለበት።