ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባካሄደችው የቪዲዮ ኮንፈረንሶች፣ ከጋዜጠኞችና ከተከታዮቿ ጋር በባደረገቻቸው ስብሰባዎች ላይ የምድራችንን የወቅቱ አጣዳፊ የአየር ንብረት ቀውስን በተመለከተ እንዲህ በማለት እቅጩን
ተናግራለች፣ “ምድራችን በመቃጠል ላይ ያለች ቤት ናት᎓᎓ በአንድነት በተባበረ መንፈስ ተንቀሳቅሰን እሳቱን ካላጠፋን ቤት የሚባል ነገር አይኖረንም᎓᎓” በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ አንገቱን ቀና የሚያደርግ መፍትሄ ሰጥታለች፣ ይኸውም እያንዳንዱ ሰው በቀላሉ እውን ማድረግ የምንችለውን መፍትሄ፣ “ምድራችንን ለመታደግ ቬጅ ሁን᎓᎓” የሚለውን፡፡
ቀውሱ እየተባባሰ ሄዶ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የሰው ልጆችን ሕይወት እያጠፋና በሚሊዮን የሚገመቱ ሌሎችን ከመኖሪያ ቤታቸው እያፈናቀለ ነው፣ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረትም እያወደመ ነው᎓᎓ የባህር ከፍታ በመጨመር እስካሁን 18 ደሴት አገሮች ሰምጠዋል፤ ብዙ ሌሎች ደግሞ እጣ ፈንታቸውን በስጋት በመጠባበቅ ላይ ናቸው᎓᎓ በተጨማሪም የዝናብ መዛባትና የድርቅ መባባስ በብዙ የዓለም አካባቢዎች ላይ ተጽዕኖ አሳርፎ፣ የምግብና ውሃ እጥረትን በማባባስ ላይ ይገኛል᎓᎓ አንድ የአየር ንብረት ባለሙያ፣ የባሰ የአየር ጸባይ፣ ማለትም `ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የአለም ሙቀት መጨመር `ሊከሰት እንደሚችል የበኩሉን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል᎓᎓
በዚህ መጽሓፍ ውስጥ ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ የምታቀርበው ከዓለም ሙቀት መጨመር ጋር የተቆራኙ ዋና ዋና መንስኤዎችን በተለይም፣ መሰረታዊ ምክንያት የሆነውን፣ የእንሰሳት እንዱስትሪን ነው፡፡
በርግጥ ብዙ የሳይንስ ጥናቾች የታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ፣ ከሃያ ዓመታት በላይ ስታራምድ የቆየችውን ዕይታ ይጋራሉ፡፡ ለምግብ እንሰሳትን ማራባት ውድ የሆነውን ብዙ ውሃ፣መሬትና ሃይል ከማባከኑም በላይ አስደጋጭ የሆነ ከ51% የምድርን ሙቀት አማቂ ጋዞችን ያመነጫሉ፡፡ የእንሰሳት እርባታ ከካርቦንዳዮክሳይድ በጣም የበለጠ ሀይለኛ ሙቀት አማቂ የሆነውን ትልቁ ዋነኛ የከባቢ አየር ሚቴን ምንጭ ነው፣ ይሁን እንጂ ይህ ጋዝ በከባቢ አየር ውስጥ የመቆየት እድሜው አጭር ነው፡፡
ስለዚህ፣ ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ እንደምትለው፣ ሥጋ ማምረት ማቆምና ቬጅ በመሆን ወይም እጽዋትን መሠረት ያደረገ አመጋገብን በመከተል የዓለምን ሙቀት ወዲያውኑ መቀነስ፣ በእንሰሳት አማከይነት የሚፈጠሩትን የአካባቢያችንን በሽታዎች መፈወስ፣ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በትሪሊዮን የሚቆጠር ብር መቀነስ ይቻላል፡፡ ይህ ለውጥ እነዚህን ውጤቶች በምድራችንና በዓለም ማህበረሰብ ላይ ምንም አሉታዊ ተጽዕኖ ሳይኖረው መጎናጸፍ ይቻላል፡፡በታቃራኒው፣ ከእንዱስትሪውና ትራስፖርት ዘርፍ የሚመነጩ ተመሳሳይ የCO2 ቅነሳ በኢኮኖሚው ላይ አውዳሚ ውጤት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በተጨማሪም የአረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች ለማዳበር ብዙ ኣመታት መጠየቁ ይፈልጋል፣ ሚቴንን መቀነስ ግን በያንዳንዱ ቬጋን ማዕድ ወዲያውኑ የሚተገበር ነው፡፡ የቬጋ አመጋገብ ህይወት መከተል/መምረጥ ቀላል፣ ፈጣንና በትንሽ ወጪ የአየር ንብረት ቀውስን መፍትሄ መስጠት ሲሆን፣ ያለንም ብቸኛው መድህን ይህ ነው ምክንያቱም ጊዜ የለንምና፡፡
በርካታ የአየር ንብረት ባለሙያዎች፣ የአካባቢ ጠበብቶችና የመንግስት ባለስልጣናት ምድራችንን ከባሰ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ለመታደግ ይህን አቅጣጫ ማራመድ ጀምረዋል፡፡ የታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይን፦ እያንዳንዱ የመወሰን ስልጣን ያለው ሰው ይህን ለውጥ የሚያመቻች ቆራጥ ህጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል የሚለውን አስቸኳይ ተማጽኖ በማንጸባረቅ ይህም ሰኔ 2010 እ.ኤ.ኣ. በቀረበው የተባበሩት መንግስታት ከስጋና ወተት ነጻ የሆነ አመጋገብ የለውጥ ጥሪ ሪፖርት ውስጥ ተካቷል።
ምናልባትም ከካርቦን አሻራችን ይልቅ የበለጠ አውዳሚ የሚሆነው በየአመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሃን እንሰሳትን በመግደል በደም የተበከለው ድርጊታችን የአየር ንብረት ለውጥ ዋና ምክኒያት ነው። ታላቋ መምህርት እንደምታስጠነቅቀው ይህ አለማቀፋዊ ደረጃ የደረሰ ግብረገባዊ ወንጀል ለኢሰላማዊ ድርጊታችን በተፈጥሮ አደጋዎች አማካይነት አጸፋዊ ምላሹን እየሰጠን ይገኛል። “የዘራኸውን ነው የምታጭደው።” ይህ ነው በታላላቆቹ መጽሃፍት ውስጥ የሚገኘው አስተምሮት።
በርግጥ የሰው ልጅ እጅግ አሳሳቢ በሆነ የመጨረሻ ጫፍ ላይ ማለትም መልሶ ማስተካከል ከማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ምድሪቷን ለማዳን ያለን አንድ እድል ብቻ ነው ጊዜውም አሁን ነው። መልካምና ህይወት አዳኝ የሆነውን በእጽዋት ላይ የተመሰረተውን አመጋገብን በመከተል ያንዣበበብንን ጨለማ በቀላሉ መግፈፍ እንችላለን፡፡ ይህ ትንሽ እርምጃ በተራው የሰው ልጅን ወደ ከፍተኛ የንቃተ ህሊና ደረጃ ያሸጋግረዋል፡፡ በዚህም የምድርን ሚዛን በማስፈን ተፈቃቅደንና ተሳስበን ወደ ወርቃማው የሰላም፣ የውበትና የፍቅር ዘመን እንገሰግሳለን። በዚህም እንደ ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ቃል፣ በምድር ላይ ገነትን እንፈጥራለን።
ይህን እድል ተጠቅመን ዛሬውኑ ለለውጥ እንነሳ፡ ስልጣኔኣችንና ምድራችንን ከፍ ከፍ ማድረግ የሁላችን ምርጫ ይሁን።
የኢድተሩ ማስታወሻ
· ይህ መጽሀፍ ታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ካካሄዱት አለም አቀፋዊ የቪዲዮ ኮንፈረንሶች፣ ከጋዜጠኞች ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስና ከተከታዮቻተው ጋር ካደረገቸው ስብሰባዎች ላይ የተናገሩትን ያካተተ ነው፡፡ ምንጮቹን ለማጣቀስ በገጽ _____ ላይ የሚገኘውን “የታላቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ንግግር ማጣቀሻ ጥንቅር” ይመልከቱ፡፡
· ስለእግዚኣብሄር፣ ወይም ስለ ታላቅ መንፈስ ሲናገሩ እግዚኣብሄር ሴት ወይስ ወንድ ስለመሆኑ ያለውን ክርክር ለማስወገድ ታላቋ መምህርት ዋናውንና ጾታዊ ያልሆነን ቃል ትጠቀማለች።
እርሷ + እርሱ =እርሰ
እርሷን + እርሱን =እርሰን
የርሷ +የርሱ = የርሰ
ለምሳሌ፡ እግዚኣብሄር ሲፈልግ እርሰ ነገሮች እንዲፈጸሙ የሚያደረገው በየርሰ መልካም ፍላጎት መሰረት እርሰን እንደሚመች በማድረግ ነው።
· እንደ የስነ ጥበባዊ ንድፍ ፈጣሪነቷና እንደ መንፈሳዊ መምህርነቷ፣ ቺንግ ሃይ የውስጥ ቁንጅናን የሚገልጹ ነገሮችን በሙሉ ታፈቅራለች። በዚህ ምክንያትም ነው ቬትናምን ስትጠቅስ እንደ "ኣው ላክ" እንዲሁም ታይዋንን እንደ "ፎርሞሳ" ብላ የምትጠራቸው። ኣው ላክ የቀድሞው የቬትናም መጠሪያ ስም ሲሆን ትርጉሙም "ደስታ" ማለት ነው። እንዲሁም ፎርሞሳ የሚለው መጠሪያ ስም፣ ትርጉሙም "ቆንጆ" ማለት ሲሆን፣ በይበልጥ ሙሉ በሙሉ የሚያንጸባርቀው የደሴቲቱንና የነዋሪ ህዝቦቿን ቁንጅና ነው። ታላቋ መምህርት እነዚህን ስሞች መጠቀሙ ለመሬቲቱና ለነዋሪ ህዝቦቿ የመንፈስ ከፍታንና መልካም እድልን እንደሚያመጣ ይሰማታል።