ምእራፍ አንድ
የቪጋን መፍትሄ አለምን ለመታደግ
ነገሩ አስቸኳይ ነው። ራስን ማትረፍ ይቀድማል፣ ለዚህም የአለም ሙቀት መጨመርን ማቆም አለብን። ስለዚህ ለፕላኔታችን አካባቢያዊ ችግሮች፣ በህይወት ለመትረፍ፣ ለጤንነት፣ ለምጣኔ ሀብት፣ ወዘተ፣ ቪጋን ብቸኛው ቅጽበታዊ መፍትሄ ነው።
ፕላኔታችን ለነዋሪዎቿ ሁሉ ማለትም እንሰሳትን፣ ዛፎችንና እጽዋትን ጨምሮ በተሻለ ገንቢ ለውጥ ላይ መሆንዋን አምናለሁ።
ይህን እድል ተጠቅመን መጥፎ ልማዶቻችንን ፣እንደ ስጋ መብላትን፣ እጽ መውሰድን፣ስጋራ ማጬስን፣በአልኮሆል ራስንና ሌሎችን መመረዝን፣ሌሎች በርካታ አገሮች የስጋራ ማጨስ ልምድን እንዳስቆሙ ሁሉ፣እንደ አንድ ሰው ሆነን በህብረት ለለውጥ ብንንቀሳቀስ በፕላኔታችን ላይ ወዲያውኑ ተኣምራዊ ለውጥ ሲከናወን ማየት እንችላለን።