III. ህይወትን ለመታደግ ህይወት ስጥ
አንበሳ በሰላም በግቷን እንድተኛ ከፈለግን እኛ ሰዎች ያንኑ ቀድመን ማድረግ አለብን።
ስጋ መመገብ እንስሳቱን ሰውንም ይገድላል
ስጋ መመገብ ሰው በራሱ ላይም የሚፈጽመው ትልቁ የጭካኔ ተግባር ነው። እንስሳቱን ራሳችን እንኳን ባድንገድል ለሞታችው ተጠያቂዎች ነን።
ለስጋ ብለን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ እንስሳትን እንገድላለን። አስደንጋጭ 55-ቢሊዮን እንስሳትን፣ ስምንት እጥፍ የአለም የህዝብ ቁጥር ያህል እንስሳትን ለሰው ምግብነት በያመቱ እንገድላለን። 103 ይህ በቢሊዮን ቁጥር የሚገደሉትን አሳዎች አይጨምርም፣ በጠቅላላ ወደ 155-ሚሊዮን ይደርሳል በየቀኑ የሚገደለው የእንስሳት ቁጥር።
የወተት ምርቱም ከስጋ ተለይቶ አይታይም፣ ምክኒያቱም የጭካኔውና የማሰቃየቱ ነገር ተመሳሳይ ስለሆነ፣ እናም ለምስኪኑ እንስሳ ፍጻሜው ዘግናኝ ሞት ነው። በወተት እንዱስትሪውም ምንም ምህረት አይታይም።
በስጋና አሳ እንዲሁም ከእንስሳት ጋር በተያያዘ የአመጋገብ ስርኣት ምክኒያት በያመቱ ሰዎችም ይሞታሉ። በያመቱ ወደ 33-ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ከስጋ ጋር በተያያዘ በሽታ ሲጠቁ፣ በልብ በሽታ ካንሰርና በሌሎች ሁኔታዎች እስከ 90,000 የሚገመቱ ሰዎች በየቀኑ ለሞት ይዳረጋሉ።
ስጋ የአለም ሙቀት ጨማሪና ገዳይ ነው፣ እናም ይገድላል፣ ይገድላል። ስለዚህ ስጋ ገዳይ ነው፣ መቆም ያለበት ወንጀል ነው።
በተጻራሪው ደግም በምግብ እጦት የሚራቡ ብዙ ሰዎች አሉ፣ ምክኒያቱም እህሉ ለእርድ ለሚዘጋጁ እንስሳት መኖ ስለሚውል። ወደ 25,000 የሚገመቱ ሰዎች በተዘዋዋሪ መንገድ በስጋ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በረሃብ ይሞታሉ። 104
በስጋ ሰበብ በተፈጠረው የአለም ሙቀት መጨመር የተጠቁ በመቶ ሺቶ የሚቆሩ ሰዎች አሉ። ሌሎች በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ ምክኒያት ቤት አልባ ሆነዋል።
ይህ በስጋ ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክኒያት የሚሰቃዩትን ንጹሃን የዱርና የቤት እንስሳትን ሳይጨምር ነው።
እንስሳትን ማረድ፡ አለማቀፋዊ ወንጀል
አማራጭ እያለን ለራሳችን ደስታ ብለን ደስ የሚሉ ንጹሃን ፍጥረታትን በጅምላ ከመግደል የበለጠ ትልቅ የሞራል ቀውስ የለም። እንደዚህ አይነቱ የጅምላ ጭፍጨፋ አለማቀፋዊ ወንጀል ነው። ይህ የግድያ ሃይል/መንፈስ በተራው ቂም ወልዶና አጠናክሮ ሌላ አፍራሽ ሃይልና መንፈስ ያሰከትላል፣ ይህም የበለጠ ወደ መቀመቅ ይከትና አለማችንነ ሊያጠፋብን ይችላል።
በቢሊዮን የሚቆጠሩ የንጹሃን ፍጥረታት ህይወትን በማጥፋት፣ ባለፈው ምእተ-አመት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የራሳችን ዝርያ የሆኑ ሰዎችንም በመግደል ብዙ፣ ብዙ፣ በጣም ብዙ አፍራሽ ሃይል አፍርተናል። በቀጥታ በጦርነት፣ በተዘዋዋሪ መንገድ ደግሞ በምንፈጥራቸው እንደ ንፍፊት ወረርሽኝ፡ የሳንባ ወረርሽኝ፣ አሁን ደግሞ በአሳማ ጉንፋን ወረርሽኝ፣ የወፍ ጉንፋን ወረርሽኝ፣ በሽታዎች ።
ስጋ መብላት የአለም ሙቀት መጨመር መንስኤ መሆኑ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። በአለማችን ብዙዎቹ ግንባር ቀደም የጤና ችግሮች ከስጋ ጋር ተቆራኙ ናቸው። ሰለዚህ ስጋ መብላት በእንስሳት ላይ ጭካኔ መፈጸም ነው። ስጋ መብላት በደህንነታችን ላይ ጭካኔ መፈጸም ነው። ስጋ መብላት በልጆቻችን ደህንነት ላይ የሚፈጸም ጭካኔ ነው። ስጋ መብላት በፕላኔታችን ላይ የሚፈጸም ጭካኔ ነው። ቨጋን ሁን፣ እናም ከእንግዲያ ወዲህ ከመሰል ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ስቃዮች ብሎ ነገር አይኖሮም።
እንስሳትን ወይም ሰውን መግደል ማቆም አለብን። የእንስሳትን ውጤቶች ማምረት ማቆም አለብን። መጠቀሙንም ማቆም አለብን። ሦስት ማቆሞች፡ ግድያ አቁም፣ ማምረቱን አቁም፣ መጠቀሙን አቁም። እናም መብላቱን ማቆም፣ ስጋ መብላቱን አቁም ነው መልእክቱ።
ከእንስሳት ማራባትና ህይወታቸውን መስዋእት ማድረግ ጋር የተያያዙ መራር እውነታዎችን ሰዎች ሲረዱ የሌላውን የሞተ አካል መብላት አስፈላጊ እንዳልሆነ በቀላሉ ማየት ብቻ ሳይሆ በደም መጨማለቃቸውንም ይገነዘባሉ።
ከተፈጥሮ ጋር መተሳሰቡን/አንድነቱን መመለስ
ማስታወስ ያለብን ይህቺ ፕላኔት የሁላችን መኖሪያ፣ ውሃው፣ አየሩ፣ ሃብቱ፣ ምግቡ፡ ሁሉም ተፈጥሮ የጋራችን መሆኑን ነው፣ መተሳሰብና ያለውን መሰጣጣት/ share መካፈል አለብን። ቪጋን ሁን፣ አረንጒዴ ሁን፣ አናም ፕላኔታቸውን፣ የእንስሳቱም ፕላኔት ታደግ። በእውነት፣ ይህ ነው አካባቢውን ለመመለስና ከፍተኛ ሰላም ለማስፈን የሚያስችል እጅግ የተሻለው መንገድ።
“እኛ የምድሪቱ አካል ስንሆን እርሷም አካላችን ናት። መኣዛቸው የሚያውደው አበባዎች እህቶቻችን፣ አጋዘኑ፣ ፈረሱ፣ ትልቁ ጆፌ አሞራ ወንድሞቻችን ናቸው። ያለ እንስሳቱ ሰው ምንድርነው?
ሁሉም እንስሳት ቢጠፉ፣ የሰው ልጅ በመንፈሳዊ ብቸኝነቱ ይሞታል። የአለት ጫፎች፣ እርጥበታማ የገጠር መስኮች፣ በሰውና ፈረስ መካከል የሚፈጠረው አካላዊ ሙቀት - እነዚህ ሁሉ የአንድ ቤተሰብ ናቸው።
ምድር ለሰው የተሰጠች አይደለችም፤ ሰው ነው ለምድር የተሰጠው።”
—የሲኣ ልዝ አለቃ፣ የዱዋሚሽ ነባር ዜጎች አለቃ፣ በዋሽግተን ግዛት፣ አሜሪካ፣ የሲኣትል ከተማ ስያሜ መሰረት
እስቲ ፕላኔታችን ያለ እንስሳት ምን እንደምትመስል አስቡ። ሁሉም ውሾች የሉም፣ ድመቶች ጠፍተዋል፣ ወፎች የሉም፣ አሳ የለም፣ ጎሽ የለም፣ ዝሆኖች ጠፍተዋል፣ አስቡ፣ በህይወት ያለ ምንም እንስሳ የለም፣ እንዴት ነው የምትኖረው? ህይወታችን እንዴት ነው የተሟላ መሆኑን የሚሰማን? በጣም ደረቅና ትርጉም የለሽ ነው የሚሆነው።
ስለዚህ ሁሉንም ህይወት ብናከብር፣ ምንም ህይወት አናጠፋም። ምድሪቱ ለሰውና ለእንስሳቱ በቂ በረከት ትሰጣለች። ሌላውን ፍጥረት የሚጎዳ መንገድ መምረጥ አያስፈልገንም። ይህ ማለት ከእንስሳት-ነጻ የሆነ አመጋገብ መከተል፣ እንደገና፤ እንደገና።
የሰው ልጆች ሁሉ ከእንስሳት-ነጻ የሆነ አመጋገብ ቢከተሉ፣ የሁሉንም ህይወትና ተፈትሮን ቢያከብሩ በምድር ላይ ገነት ይኖረናል። ለማንኛውምን በደል/ነገር ይቅርታ ይደረጋል። ማንኛውም ነገር ደህናና መልካም ይሆናል። ፕላኔቷ ትታደሳለች፣ እንስሳቱ ምስጋናቸውን ይሰጣሉ፣ ሰውም ጤነኛ ይሆናል፣ እናም ሁለም ብሩክና ደስተኛ ይሆናል። ከኛ የሚጠበቀው ቪጋን መሆን ብቻ ነው።
እንስሳት ፍቅርን ወደ አለም ያመጣሉ
ሀቁ እንስሳት የመጡት የሰው ልጅን ሊረዱ ነው። መጽሃፍ ቅዱስ እንደሚለው “እኔ የሰራኋቸው/የፈጠርኳቸው (እንስሳቱን) ወዳጅ እንዲሆኗችሁ እናም እንዲረዷችሁ ነው።” እንደዚያ ነው። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ያንን እርዳታ መቀበል ሲችል እናም ያሳዝናል። በተጻራሪው ይገድላቸዋል። እግዚኣብሄር በምድር ላይ ያስቀመጠው ነገር ሁሉ ምክኒያት/ አላማ አለው። ምንም መግደል የለብንም። ከእጽዋት ውጪ ምንም መመገብ የለብንም።
እንስሳት ወደዚህ ምድር የመጡት የተለየ ሚና/ተልእኮ ይዘው ነው። ብዙዎቹ ከመንግተ-ሰማያት መለኮታዊ ሃይልን፣ ወይም ፍቅርን ይዘው ነው የወረዱት፣ እዚህ በመገኘታቸው ብቻ ምድርን ይባረካሉ። እንደፈረስና ጥንቸል የሚንከባከቧቸውን ሰዎች እርኩስ ሃይሎች መጠበቅ ይችላሉ፣ ወይም ጤናቸው እንዲጠበቅ፣ መልካም እድል እንዲገጥማቸው፣ የሃብትን ጸጋን ጨምሮ፣ ደስታን ወይመ መለኮታዊ መመንጠቅን ያበረክታሉ። በጽሞና ይከታተሉናል፣ እናም በረከቶታቸውን ከልብ ወደኛ ይሰዳሉ። ጥቂቶቹ ከከፍተኛ የንቃተ-ደረጃ የመጡ ናቸው፣ በእንስሳት ቅርጽ ወደ ምድር የመጡት የሰውን ልጅና ሌሎቹን ፍጥረታት ሊረዱን ነው።
በተጨማሪም እንስሳት በቁሳዊ አለምም የተከበረና እጅግ ጠቃሚ የሆነ ሚና አላቸው። አንዳንዶቹ እንስሳት፣ እንደ የሜዳ አህያ፣ ጦጣ/ዝንጀሮና የዱር ጉጉቶች ዘር ለመዝራትና ለማሰራጨት ይረዳሉ፣ ንቦችና ሌሎች ነፍሳት ሰብልንና ሌሎች እጽዋትን ለማዳቀል ይረዳሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ የደኑንና የውቅያኖሶችን ደህንነትና ጤና ለመጠበቅ ይረዳሉ። እንዲሁም እንስሳት በቀጥታም ሰውን ይረዳሉ።
ከጋዜጦች ላይ እንዳነበብኩት፣ ከሬድዮ እንደሰማሁት፣ ከቲቪ እንዳየሁት ብዙ የተባረኩ እንስሳት ሰዎችን ከአደጋ አትርፈዋል። የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ዝርያዎቻቸውንም አትርፈዋል። ከነዚህ ወርቃማ እንስሳት ብዙ የምንማረው ነገር አለ።
(ለታለቋ መምህርት ቺንግ ሃይ ውስጣዊ የእንስሳትና የሰው ልጆችን የNQ ና LQ ባህርያት እይታዎች እባክዎ እዝል 10ን ይመልከቱ)
ኤደንን በምድር ላይ ፍጠር
በኦርጋኒክ፣ ቪጋን የህይወት መስመር፣ እንደ የእያንዳንዱ ሰው ቆራጥ ተልእኮ አካል፣ ጥረቶቻችን በአንድነት በርግጥ መድህንን በማምጣት አለምን ለሁለቱም- ለሰዎችና ለተወዳጆቹ እንስሳት መታደግ እንችላለን።
ኤደን በምድር ላይ የመሰለ- እያንዳንዱ በአገልግሎቶቹና ሃብቶቹ ለመጠቀም እኩል እድል የሚያገኝበት ኤደን በምድር ላይ ተፈጠረ ማለት ነው። ሁሉም ነገር በተስተካከለ መልኩ ይሰራጫል። እያንዳንዱም ሌላውን ያከብራል፣ ይወዳል፣ ይጠነቀቅለታል።
በታላቋ መምህርትና መካከል የተደረገ ውይይት
ጥ፡ መምህርት፣ በእንስሳትና ሰዎች መካከል ያለው በፍቅር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት
ፕላኔታችንን እንዴት ይነካታል ብለሽ ትገልጸለሽ?
መምህርት። ደህና፣ ያ ለምድር ታላቅ ሰላም ይሆናል፣ ማለቴ ትልቅ ሰላም።