• ምእራፍ አራት. የቪጋን ፖሊሲና ህግ ማውጣት > II. መንግስታት አፋጠኝ እርምጃ መውሰድ አለባቸው

      • II.  
        መንግስታት አፋጠኝ እርምጃ መውሰድ አለባቸው


        የየአገራቱ መሪዎች አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው። የሁሉም አገር ህዝቦች አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው። ዝም ብለን ተደላድለን በመቀመጥ ማውራት፣ በኛ አካባቢ የውሃ እጥረት ወይም የምግብ ዋጋ ማሻቀብ አልታየም ማለት እነዚህ ችግሮች አይደርሱብንም ማለት አይደለም።

        አንድ ነገር በማድርግ በቢሊዮኖች ላይ እየተከሰተ ያለውን አሳዛኝ ነገር ማስወገድ አለብን። በአየር ንብረት ለውጥ፣ ውሃና ምግብ እጥረት ምክኒያት ከአንድ ቢሊዮን ሰዎች በላይ ለረሃብ ተዳረገው ይገኛሉ። እባካችሁን ተገቢውን አፋጣኝ እርምጃ አሁኑኑ ውሰዱ፣ በጣም ቀላል ነው። ቬጅ መሆን ነው። ቬጅ ሁኑ፣ ለአሁኑ ይህ በእውነት በቂ ነው፣ ለመጪው ረጂም ጊዜም በቂ ይሆናል።


        ስለእጽዋትን-መሰረት ያደረገ ህይወት መረጃ አሰራጭ



        እንደእውነቱ ከሆነ ሰዎች በገበታቸው ላይ ስለሚቀርበው ምግብ በቂ መረጃ የላቸውም። በአብዛኛው ጊዜ በገበታቸው የምትቀርበው ትንሿ የስጋ ጥቅል ከመጣችበቱ አትመሳሰልም።

        ልማድ የሚባለው ነገር ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ይሄዳል። መላው ህብረተሰብም እንደተፈጥሮ ህገ ተቀብሎት ድጋፉን እይቸረው ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ ሰዎች ንቃተ-ህሊናቸውን በማሳደግ በእንስሳት ላይ የሚፈጸመውን ጭካኔ እየተገነዘቡ የመጡ ይመስላል። ስለዚህ እኛ፣ ሰዎች ርሁሩህና የሁሉንም ፍጥረታት ህይወት ወደ ማክበር እንሸጋገራለን ብዮ አስባለሁ።

        ብዙዎች የእንስሳት እንዱስትሪ ምን ያህለ ጎጂ ጋዝ እንደሚለቅ  ወይም የገደለ ይገደላል የሚባለውን፣ እናም ስጋ ሌላው መርዘኛ የሱስ አይነት መሆኑን  አይገነዘቡም። ስጋ ፕላኔታችንን እየገደለ መሆኑን አይረዱም።

        አሁን ጉዳዩ አስቸኳይ/አጣዳፊ መሆኑንና ሰዎች ስጋ መብላት እንዲያቆሙ፣ መንግስታት ጎጂነቱን ለህዝቦቻቸው ማስረዳት አለባቸው። ይህ የግል ምርጫ ጉዳይ አይደለም። የፕላኔታቷ የሞትና ህይወት ጉዳይ እንጂ።

        በአሰጊ አደጋ ጊዜ መንግስታት ተጎጂዎችን በአስቸኳይ ማውጣት አለባቸው። በጦርነት ወቅት ሰዎች ራሳቸውን እንዴት መከላከል እንደሚገባቸው ይነገራቸዋል። እንዲያውም መንግስታት አዲስ የጦር አባላት/ወታደሮች በመመልመል ህዝባቸውን ይከላከላሉ ወይም ያዘምታሉ።

        ስለዚህ ይህ ጉዳይ እንዲያውም ከጦርነት የበለጠ አስቸኳይ ነው። እርፍጠኛ ነኝ መንግስት ለዚህ ችግር መፍትሄ ይሰጣል። እርፍጠኛ ነኝ ሰዎች መረጃ ሊሰጣቸው ይችላል። መንግስት ይህን ለማድረግ የተጣለበት ሃላፊነት አቅምም አለው።

        መንግስታት መርዳት አለባቸው። መረጃ በማሰራጨት ሰዎች ቬጄታሪያን እንዲሆኑ በማበረታታት አዲስ ርሁሩህ፣ በፍቅር የተሞላ ጤናማ ሃያል በማሳጨት መሳተፍ ይችላሉ። ደጋፊ አበረታታች ሃይል አስፈላጊ ነው።

        በየቦታው ማስተዋወቅ አለባቸው። ሰዎች እንዲያነቡ በራሪ ወረቀቶችን ማሰራጨት፣ ይህ ህዝባዊ ሃላፊነት መሆኑን መገንዘብ ይገባል። ይፋ እውቅና መስጠትና ሁሉም ሰው የቬጄታሪያን ፋይዳ እንዲረዳ ማድረግ ይገባል። በነጻ ለቬጄታሪያን ምግብ መዘርዝር ድረ-ገጽ ማዘጋጀት፣ የቬጄታሪያን ምግብ አዘገጃጀት ስልጠና መስጠት፣ የቬጄታሪያን ክበቦች ማቋቋም።

        ይፋ ማድረግ፣ ከዚያም ሁሉም በደስታ ይከተላል፣ ጥቂት አዲስ ለውጥ በአለም መጣ ማለት ነው።

        በጣም አስፈላጊው ነገር የሰው ልጅና በአለም ዙሪያ ያሉ ዜጎች ሁሉ የቬጄታሪያን አመጋገብ መከተል አለምን ለመታደግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ማወቅ አለባቸው። ወቅቱ ምን ያህል አደገኛና አስቸኳይ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ያ ነው ትልቁ ቁም ነገር።

        ሌላው ማወቅ ያለብን  የቬጄታሪያን አመጋገብ ፋይዳ፣ የያለ-መግደል አመጋግብ ከፍተኛ የ ሞራል እድገት ማምጣት መቻሉ ነው። በመጀመሪያ  የቬጄታሪያን አመጋገብ ለጤናችን መልካምና ፕላኔቷን ለመታደግ የሚሰጠው ጠቀሜታ፣ ከዚያም ልጆቻችን ለወደፊቱ የሚኖሩበት ቤት ያገኛሉ ማለትነው።

        ያለን አንድ ቤት፣ ይህችው ምድር ናት። እርሷ ከጠፋች፣ ሌላ መገንባት አንችልም፣ ተራ ቤት እንደገና መገንባት እንደምንችል፣ ምድር ከጠፋችን ከእንደገና መግንባት አንችልም። እንዲህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ መንግስታት ማድረግ ያለባቸው ትልቁ ነገር መረጃውን ለህዝቦቻቸው ማስተላለፍና ማሰራጨት ነው።


         ልክ ሲጋራ ማጨስ እንደታገደ ስጋን ማገድ ይገባል


         

        ቬጄታሪያንነት የህይወታችን መንገድ መሆን ይገበዋል። ምንም ምክክር/ንግግር/ውይይት/ ጭቅጭቅ አያስፈልግም።

        ስጋን ማገድ አለብን። ማገድ ያለበን ሰዎች እንዴት የቬጄታሪያን ምግብ መብላት፣ ማዘጋጀት እንዳለባቸው በማሳየት ነው። በሁሉም መንገድ በመውጣት። በእውነት ይህ የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ነው። የስጋ መብላት አደገኛኝነትና የመፍትሄውን መረጃን ለሰዎች ማድረስ የህይወትህ ተልእኮ አድርግ።

        ሲጋራን አገዱ እናም ሲጋራ ማጨስ ታገደ። አደንዛዥ እጽ አገዱ እናም ታገደ። የአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲም ተመሳሳይ ነው። መልከሙ ነገር ምን እንደሆነ ተረዱና ያንን በስራ ላይ ካዋሉ፣ ፈጣን እርምጃ ተወሰደ ማለት ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ እናገግማለን ወይም ተጸእኖውን እንገታለን።

        ምክኒያቱም ከእንግዲህ ወዲያ እንስሳትን ከላራባን ምድራችን በአስተማማኝ ሁኔታ ታገግማለች፡ (ከእንስሳት) ሙቀት-አማቂ ጋዝ ወይም ሚቴን አይኖርም፣ አይባዛምም። ያሉንን እንስሳት ማስወገድ የለብንም፣ መጠበቅና መንከባከብ፣ ሌላ ለትርፍና ለስጋ ማራባት የለብንም። እናም ከዚያም ምድራችን ታገግማለች። ከዚያ በኋላ ላምች በተፈጥሮው መንገድ መጓዝ ይጀምራሉ፣ መሬቱም በአትክልትና ዛፎች እንደገና ይሸፈናል።

        አዝማማውን እንደ ስጋ ሁሉ ገዳይ ከሆነው ከሲጋራ ጋር ብናነጻጽረው፣ ከ1950 በኋላ ብቻ፣ የምርምር ውጤቶች ትንባሆ የሳምባ ካንሰር መንስኤ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ካሳዩ በኋላ፣ መንግስታት ሲጋራ ማጨስን ማገድ ጀመሩ፣ እናም ቀስ በቀስ እየዸገ መጥቶ አሁን ከ80 በላይ የሚሆኑ አገሮች ከመላ-ጎደል ሲጋራ ማጨስን አግደዋል።106

        ጥናቶች እንደሚየያመለክቱት ሲጋራ ማጨስን ማገድ ማጨስ ያቆሙትን ብዙ ረድቷቸዋል፣ እናም ማጨስ ያቋረጡቱ በእገዳው ምክኒያት የበለጠ ደስተኛ ሆነዋል ምክኒያቱም ሱሱ ለጤናቸው መጥፎ እንደነበር ይረዳሉና።

        በተመሳሳይ ሁኔታ ስጋን ማገድ፣  ሁላችንም ከጥናቶች እንደምንረዳው እኛንና ልጆቻችንን፣ የምንወዳቸውንና ፕላኔቷን የሚገድል፣ በጣም መጥፎ ሱስ/ልማድ ነውና።

        ስለዚህ ስጋን ማገድ ወደ ቪጋን አለም የሚያደርሰን ጠንካራ ጎዳና ይሆናል።

        ምክኒያቱም መልካም መሪ ለህዝቡ መጥፎ የሆነውን ማገድ/ማስቆም፣ ጥሩ የሆነውን ማስፋፋት ነው። መሪዎች እጽዋትን መሰረት ያደረገ አመጋገብ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎች ስለጤና፣ ህይወት-አዳኝነቱን፣ ወዘተ በህዝባዊ ዘመቻ፣ በብዙሃን መገናኛ፣ በየት/ቤቱ ማሰራጨት ይችላሉ። 


        ሌላ ምርጫ/አማራጭ የለንም


        መለወጥ ወይም አዲዮስ

        በቅድሚያ ማወቅ ያለብን ነገር ከመለወጥ ሌላ ምንም አማራጭ/ምርጫ እንደሌለን ነው፣ ወይ ያን ወይ ፕላኔቷን። መለወጥ ወይም ሁላችንም መነጎድ። ከንግዲያ ምንም ምርጫ የለንም።

        እንስሳት ማርባትና ስጋ መብላትን ካላቆምን/ካላስወገድን ፕላኔቷን፣ እነርሱንና የስጋ ብዝነሳቸውንም ጭምር ለመታደግ አንችልም። ስለዚህ፣ እኔ እንደማስበው ምርጫችን ከህይወታችንና ከስራችን አንዱን ነው። መጀመሪያ መኖር ያለብን ይመስለኛል። የፕላኔቷን ሰዎች ሁሉ ማሰብ አለብን፣ ሰለስራችን ብቻ መሆን የለበትም። ጉዳዩ ይህን ያህልአጣዳፊ ነው።

        በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ፣ እነዚህ ከስጋ እንዱስትሪ ጋር ኢኮኖሚያቸው የተያያዘ ሰዎች መረጃው በትክክል ቢደርሳቸውና ስራቸውንና የህይወት መንገዳቸውን ቢለውጡ ምን ያህል እንደሚጠቀሙ ቢረዱ ወዲያው ሊለወጡ ይችላሉ። በርካታ ማነቃቂያዎች ያገኛሉ። ለምሳሌ መጀመሪያ ፕላኔቷን ከአየር ለውጥ አደጋ ያድናሉ፣ በአለም የሚኖሩ ህይወቶችን ሁሉ ይታደጋሉ።

        ካላቆምን ግን ወደ ጥፋት የሚወስደንን ጎዳና ላይ መጓዙን ከቀጠልን በስጋው ብዝነስና መጓጓዙ ውስጥ ወይም ከስጋ እንዱስትሪ ጋር ከተያያዙ ስራዎች ውስጥ ኖርክም አልኖርክም እያንዳንዳችንን የሚመለከት ወደ ጠቅላላ ጥፋትና ጅምላ ውድመት ነው።


        እንስሳትን መግደልና ጦርነትን አስወግድ እናም አገርህን መልሰህ ገንባ

        ጉዳዩ መሪዎች ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገር ማወቁ ላይ ነው። ፕላኔታችን እየጠፋች፣ ስለጦርነት መጠበብ ወይም ስለስልጣን ወይም ስለ ማንኛውም ሌላ ነገር መጨነቅ ምንድርነው? በአሁኗ ሰኣት መሪዎች ሁሉ ማተኮር ያለባቸው ፕላኔቷን መታደጉ ላይ፣ እናም መረጃውን ማዳረሱ ላይና ህዝቦች መልካም ኑሮ እንዲመሩ አዳዲስ ህጎችን ማውጣቱ ላይ ነው ትኩረት ማድረግ ያለባቸው።

        እንዲያውም ምንም ህግ አያስፈልግም፣ ምናልባት ህግ የተሻለ ሊሆን ይችላል፣ ተጨባጭ የሆነ፣ ካለበዚያ ህዝቦች ዝግጁ ናቸው። መንግስታት ጥቂት ህጎችን ብቻ መተግበርና ሰዎች መልካምና እንስሳት ያለመግደልና የፍቅር ህግን እንዲያከብሩ እንዲሆኑ፣ እንስሳተን አለመብላት፣ እንስሳትንና ሰውን ወይም አካባቢን አለመጉዳት ማስታወስ መጀመር ነው።

        የበለጠ ተጨባጭና ቀልጣፋ/ጠንካራ/ጎበዝ ተግባር መሆን አለበት። ከሁሉ አስቀድሞ ጦርነቶች ሁሉ መቆም አለባቸው።  ገንዘብና ቁሳቁሶች ፍጥረታትን ሁሉ ለማኖርና ለማመመገብ ብቻ መዋል አለባቸው - የፕላኔቷን ቁሳቁሶቹን ሁሉ ለሁሉም ማከፋፈል ይገባል። ለምሳሌ ጦርነት እንኳን ባይኖር፣ ይህ ገንዘብ የአለም ነዋሪዎችን ሁሉ ለአስርተ አመታት በነጻ ሊመግብ ይችላል።

        እናም ግድያዎች ሁሉ፣ ሰውን ወይም እንስሳቱን ማሰቃየቱ መቆም አለበት። የደን ጭፍጨፋ፣ አካባቢውን መጎዳቱና ዛፎችን ማጥፋቱ ይህ ሁሉ መቆም አለበት። መሪዎች መልካሙን፣ ጠቃሚውንና ሰላማዊውን እንዲሁም፣ መንፈሳዊውን ሁሉ፣ ለሁሉም፣ ጥቅም መስጠት እንጂ ምንም ጉዳት እንደሌላቸው እውነተኛ መንፈሳዊ ቡድኖች ኣይነት መንከባከብና ከተቻለ በህግ መጠበቅ አለባቸው።  

        ሃብትን ከሁሉም ጋር መካፈል፣ ለሁሉም ማከፋፈል፡ በቂ ምግብና ልብስ ለፈላጊ ሰዎችና እንስሳት አካፍል። ለሁሉም መሸሸጊያ የሚሆን ተገን መገንባት፣ ለሰዎችና እንስሳት - ሁሉንም ፍጥረታት ጠብቅ፣ ተንከባከብ። ደኖችን መልሶ መገንባት፣ ወንዞችን፣ ሀይቆችንና ውቅያኖሶችን ማጽዳትና መንከባከብ፤ የእንስሳት ተንከባካቢዎንና የአረንጓዴ ቡድኖችን መሸለም። የእንስሳትን ተዋጽኦዎችን፣ ስጋን፣ እጽንና አልኮሆልን ማስወገድ፣ ማጽዳት። በእንስሳት ላይ ጭካኔን የሚፈጽሙ የቤተ-ሙከራ ስራዎችን ማስቀረት አለብን። የእንስሳት እርሻን ፋብሪካዎችን ማሰቀረት ይገባል። እስረኞች ወይም ወታደሮች ሄደው ሰዎችን እንዲረዱ፣ አትክልት እንዲተክሉ መልካሙን ሁሉ እንዲሰሩ ማድረግ አለብን። የኦርጋኒክ አትክልት እርሻን መርዳት፣ ማበረታታት አለብን። ለትምህርትና ለጤና ነክ መስኮች ድጎማ ማድረግ አለብን።

        እንዲሁም የመሰሪያ ምርት/ማምረት ወደ ዜሮ ደረጃ ዝቅ ማለት፣ መቆም አለበት። አደገኛና የማይጠቅሙ የህብረተሰባችን ተግባራትና ምርቶችና መቆም አለባቸው። በመሰረታዊ ነገሮችና ትምህርት እጦት አፍራሽ ነገር እንዳይፈጽም ለእያንዳንዱ ሰውና ለሁሉም ምቾትና ደህንነት መመስጠት ይገባል። የደረጃ መበላለጥና ወሰን ማጥፋትና ለሁሉም ተመሳሳይ ደረጃና የዜግነት ክብር መስጠት አለብን።

        መንግስታት ወታደሮች እንዲኖራቸው ቢፈልጉ እንኳን በአደጋና በአጣዳፊ ጊዜና እንደ አስፈላጊነቱ መኖሪያ ቤቱን መልሰው በመገንባት ህዝቡን ለመርዳት እንዲችሉ ወታደሮቹን እንደገና/መልሰው ማሰልጠን አለባቸው። እነዚህ ሁሉ የበለጠ መሰራት አለባቸው። ሌላውን ሰው የምጠቅም ነገር ሁሉ ዜጎችን፣ እንስሳቱንና አካባቢውን ስለሚጠቅም፣ ሁሉም መንግስታት፣ መሪዎች እንዚህን ተግባራት ለማስፈጸም መሞከር፣ አሁኑኑ በተግባር መተርጎም አለባቸው።


        የስጋ እንዱስትሪ አክሳሪ ስራ/ብዝነስ ነው


        በሃይልና ሃብት አጠቃቀም ረገድ አባካኝ ነው

        እንዱስትሪው መጥፎ ነው፣መጥፎ ነው፣መጥፎ ስራ ነው፣ እናም ለማንም፣ ለፕላኔቷም ጭምር በፍጹም አትራፊና አጓጊ አይደለም። ምርቱን ለማምረት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይልን፣ ውሃንና ጥራጥሬ/እህልን የሚጠይቅ፣ በጣም አክሳሪ ስራ ነው፣ ተመሳሳይ መጠንና መተካት ከሚችል ምግብ ጋር ሲነጻጸር። ከስጋ የተሻለ ምግብ እኮ አለን።


        በድጎማና በታክስ ገቢ ላይ የተንጠለጠለ ነው

        ለምሳሌ መንግስታት ለስጋ እንዱስትሪ ድጎማ ካልሰጡ እኮ ደንን በመመንጠር የሚመረተውና አንዳንድ ሰዎች የሚበሉት በህንድ የእንድ ሃንበምገር ዋጋ $200 ዶላር ያወጣል!107

              

        የመረጃ ምንጭ፡ የሀኪሞች ኮሚቴ ተጠያቂነት ያለው መድሃኒት፣አሳማና ጤንነት፡ የእርሻ ህግ ላይ የምክር ቤት አባላት ክርክር፣መልካም መድሃኒት ቅ 16 ቁ 4 (ጸደይ 2007)


        ከአሳማ ጉንኑ ወረርሽኝ ተጽእኖ በፊትም፣ በዩኤስ አሜሪከ የአሳማ እንዱስትሪ ብዝ ቢሊዮን ዶላሮች ክሳራ ላይ ወድቆ ነበር። ለምን? ምክኒያቱም የእህል ዋጋ ንረቱ እንስሳቱን ለመመገብ አስቸግሯቸው ስለነበር ነው፣ የእህል ዋጋው እየናረ፣ እየመጠቀ ይገኛል አሁንም። እንግዲያውስ እንዴት ነው በስራው/ብዝነሱ ሊቀጥሉ የቻሉት? በታክስ ለመንግስት ገንዘብህ ትከፍላለህ፣ መንግስትም ይህንን ገንዘብ ይደጉማቸዋል። ስለዚህ ስራው አክሳሪ ነው።

        የትም፣ ከአሜሪካ እስከ ቻይና፣ መንግስታት የእንስሳት ገበሬዎችን ቢያንስ በአስር ሺህ ቢሊዮኖች የሚገመት ዶላር በድጎማ መልክ በያመቱ ያፈስላቸዋል!108 ነገር ግን ያ የምትበላው እኮ የራስን ገንዘብ ነው! ያንን በልተህ ጤናማ፣ ተደሳች ብትሆን ጥሩ ነበር። ነገር ግን ያ አልሆነም!

        የጤና ወጪው ከባድ ነው

        እነዚህ ሃንበርገሮች የተለያዩ የእንስሳት ክፍሎችን የያዙ፣ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ባክቴሪያዎችን የያዙ፣ ብዙ አይነት በሽታዎችን የሚያመጡ ናቸው።109 ከህክምና መጽሄቶች ወይም ከሳይንቲስቶች መረጃ ከፈለክ ይህንን ሁሉ ይነግሩሃል።

        ለእንስሳት እንዱስትሪ ድጎማ የታክስ ገንዘብ መክፈል ብቻ አይደለም፣ ብዙ የታክስ ገንዘብ ለህክምና፣ የምናፈቅራቸውን ህይወት ለመግዛት፣ የምንወዳቸውን በማጣታችን ህይወታችን ሙሉ ልባችንን በሃዘን ይጨበጣል።


        በእንስሳት ላይ ከባድ ስቃይ ያስከትላል

        ይህ ሁሉ ስቃይ በቋፍ ላይ ለሚገኘው ሰውነታችን ሸክም አስፈላጊ አይደለም። ስጋን ካስወገድን ሁንም - የህክምናና መድሃኒት ወጪያችንን እናስቀራለን። ይህ ብቻ አይደለም፣ መድሃኒት ከማግኘታችን አስቀድሞ ብዙ እንስሳትን በሙከራ ቤት በስንጠቃና በኬሚካል እናሰቃያለን መድሃኒቱን ለማግኘት ብቻ። ይህም ለሰው አስተማማኝ ላይሆን ይችላል።

        ይህ ሁሉ ስቃይ፣ ይህ ሁሉ የታክስ ገንዘብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ይበተናል። በፍጹም ምንም ፋይዳ የለውም። ሃብት፣ ገንዘብና ብሄራዊ ሃይል ማባከንና፣ የሰው ጤናና ደስታን ማጣት ብቻ ይሆናል። ማባከን ብቻ ነው። በጣም፣ በጣም፣ በጣም መጥፎ ስራ/ብዝነስ ነው።

        የስጋ እንዱስትሪ በአሰቃቂ ሁኔታ ለሁላችን ከምናስበው በላይ ጎጂ ነው። ድጎማ ባይደረግላቸው ኖሮ የእንስሳት ገበሬዎች ማጠፊያው ባጠረባቸው ነበር። ከስረው ከስራቸው በወጡ፣ ድርጅታቸውን በዘጉ ነበር። ስለዚህ እኔ የምለው መንግስታት ምንም ድጎማ ለእንስሳት ማርባ እንዱስትሪዎች ማድረግ የለባቸውም ነው። በአንጻሩ እነዚህ ሰውች ወደ ቪጋንነት እንዲሸጋገሩ መርዳት አለባቸው።

         

        የስጋ እንዱስትሪ ስራ ሰራተኞችን አደጋ ላይ ይጥላል

        ከዚያ ሁሉ በተጨማሪ ለብዙሃኑ የስጋ ብዝነስ ሰራተኞች ጥሩ የስራ ቦታ አይደለም። ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉና ለኬሚካልና ቀሳፊና ገዳይ ለሆኑ እንደ እንፉሌንዛ፣ የአሳማ ጉንፋን፣ የወፍ ጉንፋንና የእብድ ላም በሽታ ለመሳሳሉ የተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጡ አገኛ ከሆኑ ስራዎች እንዱ ነው።

        አሁን ራሳችንን መጠየቅ ያለብን፡ ይህ ያዋጣልን? ይህን ስንል በስጋ ተመጋቢዎች ላይ የሚከሰቱትን - ካንሰር፣ የስኳር በሽታና የጤና ችግሮችንና የልብ ህመሞች ተጽእኖን ሳናወሳ ነው።በአብዛኛው ማለት ይቻላል፣ በስም መጥራት የምትችላቸው በሽተዎች ሁሉ ከስጋ ወይም ከተያያዙ ነገሮች የሚመጡ ናቸው። ስለዚህ ሌሎች የተሻሉ የህይወት አማረጮች እያሉ ለምንድርነው እኛንም ሆነ ሌሎችን የሚረዳ፣ ጤነኛ የሆነውን ስራነ ሙያ ባለመምረጥ ለህመምና ለያለ ጊዜ ሞት የምንዳረገው?

                             በእንዱስትሪ የሚመረት ምግብ ርካሸና አቅምን ያገናዘበ ነው የሚባለው ሃይለኛው
                              
        አባባል ተሰሚነት ያገኘው የአካባቢ፣ የጤናና ማህበራዊ ዋጋዎቹ ባለመካተታቸው
         
                              
        ነው።  እውነተኛ ዋጋውን ብናሰላ፣ ምግቡ ከርካሽነት በጣም የራቀ ሆኖ
        እናገኘዋለን፤
                               
        በዘመናችን የሚታየው የምግብ አመራረት ስርኣት ለቀጣዩ ትውልድና በኛም ላይ
         
                              
        ከባድ የግንዘብ ቻና እየፈጠረብን ይገኛል።
        110

                                                                                               — AlterNet.Org


        ብቸኛው ፕላኔቷን የመታደጊያ መንገድ ስጋን ማገድ ነው

        ማንኛውም ከርህራሄ የተሞላበት ህይወት ጋር የተያያዘ ነገር ማከናወን ለራሳችን መልካምና ለፈጣሪም አስደሳች ነው። ፕላኔቷንም ይታደጋል። በመልካም ስራነቱ ብቻ ሳይወሰን፣ አሁንም ሆነ ለወደፊቱም ፕላኔታችንን ይታድጋል፣ በስጋ ብዝነስ ስራ ላይ የተሰማሩትን ጨምሮ ብዙ ህይወቶችን ያድናል። ለዚህ ነው ቡድሃ የስጋን ስራ/ብዝነስ ሰዎች ሊሰማሩባቸው የማገቡ ከአምስቱ የስራ አይነቶች አንዱ አድርጎ የሰየመው።

        የስጋ ብዝነስ/ሰራ መጥፎ ብዝነስ ነው። ላንተም በጣም መጥፎ ስራ ነው። ሌሎቹ አራቱ ደግሞ፡ መሳሪያ ማምረት፣ ሰዎችን ማዘዋወር፣ የአሲካሪ ነገሮች ብዝነስና መርዛማ ነገሮች ስራ ናቸው። እነዚህ ጎጂ ሰራውች ሁሉ ላንተም መጥፎ ናቸው፣ አሁንም ለወደፊቱም።

         

        ኦርጋኒክ እርሻን ማበረታታት፣ መደገፍና መደጎም ይገባል


        ገበሬዎች እህልን እንዲያመረቱ ማበረታታትና ስጋን በመተካት አትክልት እነዲያመርቱ ድጎማ መስጠት (መንግስታት) ይችላሉ። የበለጠ ባመረቱ ቁጥር የበለጠ ድጎማ መስጠት። ለአለም ትልቅ መልካም ነገር እያደረጉ መሆኑን ገበሬዎቹ ለገነራቸው ይገባል።

        ስጋን ሳይሆን አትክልቶችን በማምረት ሰዎችን በመመገባቸው እንዲሁም እንስሳትን በመታደጋቸው፤ ታላቅ ጀግኖች ይሆናሉ። በተፈጥሮ ሂደት ወደ መንግስተ-ሰማያት እስከሄዱ ድረስ እንስሳቱን በርህራሄና በደግነት መያዝ እንደሚገባቸው መንግስቱ ሊነግራቸው ይገባል።

        በአሁኑ ወቅት ይህ መልእክት/አካሄድ በመንግስትና መገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭና ሲበረታታ አይስተዋልም። ስለዚህ በትንሿ አስተያየቴ፣ ገበሬዎች ገንዘባቸውን በስጋ ብዝነስ ላይ የሚያጠፉ ወይም በሽታን ለሚያስከትል ወይም ለተመሳሰሰይ ነገር ከመደጎም ይልቅ መንግስት የኦርጋኒክ ምግብ ገበያና ተፈላጊነት አግኝቶ በራሱ እግር መቆም እስከሚችል መደጎም ይገበዋል እላለሁ። ከዚያም ገበሬዎች ለሰውና ለፕላኔቷ ጤንነተ የሚጠቅም የበለጠ አትክልት ለማምረት በደስታ ይነሳሳሉ።

        መንግስት የአትክልት ዘርና የተሻለ የአመራረት ዘዴዎችን በስልጠና መልክ ሊሰጣቸው ይገባል፣ ምክንያቱም ገበሬዎች እንዳንድ ጊዜ ያለ ኬሚካል ማዳበሪያ ማምረት፣ እንስሳትን ማርባት፣ ኬሚካል ወይም የኬሚካል ማዳበሪያ ወይም የጸረ-ተባይ መርዝ ጉዳቶች መረጃና ግንዛቤ ላይኖራቸው ይችላል።

        ገበሬዎች በቂ መረጃ ስለሌላቸው የተሻለ አትክልት በማምረት ትርፋማ አይሆኑም። መንግስት የተለያዩ የመሬት ጥበቃና እንክብካቤ እርምጃዎችን እንዲያገኙ በመረዳት ገበሬዎች ምርቶቻቸውን በማሻሻል በደንበኞቻቸው ዘንድ ተቀባይንት እንዲያገኙ ማድረግ ይችላል። በተጨማሪም መንግስት የምስክር ወረቀት አሰጣጥ በማዘጋጀት የኦርጋኒክ፣ ቪጋን እንዱስትሪን የበለጠ ማበረታታት ይችላል።


        ኦርጋኒክ እርሻን ስራ ላይ ማዋል/መተግበር ቀላል ነው

        አሁን የኦርጋኒክ ምግብ በመለመድ ላይ ይገኛል። እናም ለሁሉም በጣም ጤናማ ነው። ትልቅ ፍላጎት አለ።

        በማህበራችን ወስጥ ያሉ ብዙ አባሎቻችን የኦርጋኒክ እርሻ ጀምረዋል። እናም ማንም መስራት እንደሚችል ተረጋግጧል። ማንም ስራውን መጀመር የፈለገ ሰው መረጃውን ከድረ-ገጻችን ማግኘት ይችላል። ቀላል ነው፣ ብዙ ውሃ አይፈልግም። ምግቡንም በፍጥነት ማምረት ይቻላል፣ ያለ ምንም ችግር አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ብቻ ብዙ ሄክታር መሬት ላይ መስራት ይችላሉ።

        ሰዎች የኦርጋኒክ እርሻ እንዲጀምሩ፣ እንዴት የዝናብ ውሃን፣ የከርሰ-ምድር ውሃን መንከባከብና ማጠራቀም፣ እንዲሁም ዝናብ ለመሳብ እንዴት መሬትን መንከባከብ፣ ዛፍ መትከል፣ ወዘተ እንደገባቸው እንመክራቸዋለን። በህንድ ራጃስታን በአልዋል ወረዳ አንድ ቀበሌ ተገቢ ስራ በመስራት በቂ ውሃ ወደ አምስት ወራጅ ወንዞች ተመለሶ እንዲገባ ለማድረግ ችሏል- በመጠን በላይ ውሃ በመጠቀምና በመሻማት ምክኒያት ቀደም ሲል ያለነበሩ/የደረቁ ናቸው።

        ፍላጎቱ ላላቸው ማንኛውንም መረጃ ለመስጠት www.SupremeMasterTV.com የተባለ ድረ-ገጽ አለን። ስራውን ለመጀመር እምብዛም ትልቅ የካፒታል ፍሰት አይጠይቅም። ካፒታል ቢያስፈልግ እንኳን ጎጂውን የስጋ ምርትን ከመደጎም ይልቅ መንግስት የኦርጋኒክ እርሻን መርዳት፡ መደጎም አለበት። የኦርጋኒክ እርሻን መርዳት ገበሬውን ጨምሮ ሁሉንም ሰው ይጠቅማል።


        የቪጋን ምሳ ለት/ቤት ማቅረብ እንዲሁም የአካባቢ የምግብ ህብረት-ስራ ማህበራትን መደገፍ

        ከምረዳው ት/ቤቶች በዘላቂነት ከግብርናው ጋር የተሳሰሩበት የተሟላ ስርኣት የተዘረጋ ቢሆንም በተግባር እምብዛም አልተኬደበትም።

        በአውሮፓና በጃፓን የተጀመረ አንድ መርሃ-ግብር አለ፣ አሁን ይህ መርሃ-ግብር  በአሜሪካም ተጀምሯል፣ እንደ ምግብ ህብረት-ስራ ማህበራት የመሳሰሉ የአንድዳንድ ቡድኖች ትኩስ ምርቶች ሊያቀርቡላቸው ከፈቀዱ ገበሬዎች ጋር ግኑኝነት ፈጥረዋል። እናም ገበሬዎቹ የተለያዩ የምግብ ምርቶችን በማምረት ሰዎች እነዚህን የተለያዩ ትኩስ ምርቶችን ይገበያሉ።

        ይህ እውቅና እያገኘ ነው፣ በአንዳንድ ቦታዎች እንዲያውም ወረፋ እያስጠበቀ ይገኛል። በመሆኑም እርሻዎቹ፣ ኦርጋኒክ እርሻዎቹ በአስተማማኝና ዘላቂ በሆነ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ናቸው። ይህ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል ምክኒያቱም ሰዎች ጤናማና የሚተማመኑበት ምግብ ከማግኘታቸውም በላይ የገበሬዎቹንም የህይወት መሰረት አጠናክረዋል፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ለአካባቢወም የተሻለ ድጋፍ ይሰጣሉ።

        እርግጠኛ ነኝ፣ መንግስት የኦርጋኒክ እርሻን ከደገፈ ጭር ጊዜ ሁሉም ሊከተል ይችላል።

        ይህ የአረንጓዴነት አቅጣጫና ፕላኔቷንም ለመንከባከብ የሚያስችል መሆኑን በማስረዳት መልእክቱን በማስተላለፍ መንግስት መንገዱን ከመራ ገበሬዎች የበለጠ የቪጋን ምግብ ለማምረት በደስታ ይነሳሳሉ።

        የኦርጋኒክ እርሻ ትግባራን ማሰራጨትና ማስፋፋት በብዙ መንገዶች ይጠቅመናል።

          

        የኦርጋኒክ እርሻ ፋይዳዎች


         

        ለሰዎች የኑሮ መሰረት፣ ለሰዎችና ለእንስሳት ጤና፣ ለተፈጥሮ ሃብትና ፕላኔታችን ለመንከባከብ የኦርጋኒክ እርሻ በርካታ ፋይዳዎች አሉት፣ እነዚህ ፋይዳዎች የሚናቁ አይደሉም፣ ለመዘርዘርም አንችልም። የኦርጋኒክ እርሻ ፕላኔታችን ለመንከባከብ ብቻ አይደለም የሚረዳን፣ ረሃብንም ለማጥፋት እንጂ።

        ወደ ዘልማዱ የኦርጋኒክ እርሻ ዘዴ መመለስ ለምሳሌ በአፍሪካ፣በአሜሪካ፣ በአወሮፓና በአውስትራሊያ በመሳሰሉ ቦታዎች ስኬታማ እንደሆነ ተረጋግጧል። ፍላጎት እየጨመረ ስለመጣ የኦርጋኒክ ቪጋን እርሻ እያደገ ነው፣ በጣም በጣም በፍጥነት ትርፋማ እየሆነ ነው። ሰዎች ስለስጋ መብላት ጉዳቶችና ስለቬጀታሪያን ፋይዳዎች የበለጠ መረጃ እያገኙ መጥተዋል። ስለዚህ ለማንኛውም ብዝነሱን ለመቀየር ለሚፈልግ ሰው ኦርጋኒክ፣ ቪጋን፣ የአትክልት እርሻ እጅግ በጣም ጥሩ ነው።

        እንዲሀም በአፍሪካ ክ/አለም በርካታ የኦርጋኒክ እርሻ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካ፣ በኬፕ ታውን አካባቢ ነዋሪዎቹ መቶ በመቶ (100%) ኦርጋኒክ የጓሮ አትክልቶችን በአካባቢው ከማሸጡ እህል ጋር ያመርታሉ።[i] ተመሳሳይ አካሄድ በኬኒያ ተጀምሯል። እንዲሁም በቅርቡ የኦርጋኒክ ማዳበሪ የተጀመረበቱ በኡጋንዳም በአፈር እንክብካቤውና በምርቱም ስኬት እየተመዘገበ ነው።112

        በሱፕሪየም ማስተር ቴሌቪዥን ስለ ኦርጋኒክ እርሻ ሙሉ ዝግጅት ይቀርባል፣ ድረ-ገጻችንም www.SupremeMasterTV.com። በዚህ ድረ-ገጽ ላይ አትራፊና ብዙ ውሃ የማይፈልግ፣ አድካሚ ያልሆነና ለጤናችን፣ ለሰራተኞችና ለፕላኔቷ ጠቃሚ ስለሆነው የኦርጋኒክ እርሻ በርካታ መረጃዎችን እንሰጣለን።

        ኦርጋኒክ አትክልት ብትበሉ ወደ ሆስፕታል መሄድ አያስፈልጋችሁም ለዚህ ሊጠፋ የነበረውን ገንዘብም ልጆቻችሁን በተሻለ ለማስተማር፣ አረጋዊያንን በተሻለ ለመንከባከብ፡ እንዲሁም ቆንጆ መንገዶች ለመስራት፣ ተጨማሪ መሳሪያ፣ አዳዲስ ነገር ለመስራትና ሁሉንም ነጻ አገልግሎት የሚውል ዘላቂ ሃይል ለመገንባት ማዋል ትችላላችሁ።  ሃይል በነጻ ለሁሉሞ፣ ለልጆቻችን ሁሉ ነጻ ትምህርት፣ ነጻ እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም አረጋዊያን እንዲሁም ነጻ ምግብ ለአንድ ቢሊዮን ሰዎች፣ ቢያንስ ለመላው የአለም ረሃብተኞች። ፋይዳዎቹ ተዘርዝረው አያልቁም።

         

        ዘላቂነትና ከፍተኛ ምርት

        በከፍተኛ ደረጃ ወደ ኦርጋኒክ እርሻ መለወጥ አለምን ሊመግብ እንደሚችል ተረጋግጧል። በዴንማርክና በሌሎች አገሮች በተደረጉ ጥናቶች መሰረት ቀደም ሲል በቂ ጥቅም በማይሰጡ መሬቶች ላይ የኦርጋኒክ እርሻ ከፍተኛ ምርት እንደሚሰጥ አሳይተዋል።113

        እንደእውነቱ ከሆነ ከተለምዶው እርሻ የሚገኘው ከፍተኛ ምርት በአፈሩ፣ በጤናችንና በአካባበውን ጉዳት ላይ በመጣል ነው። እንደ አኩሪ አተር/ሶይ የመሳሰሉት ግዙፍ ነጠላ ምርቶች(አንደ አይነተ እህል) በአብዛኛው የሚዘሩት ለስጋ ፐሚፈለጉ እንስሳትን ለመመገብ ነው፣ የሰው ልጆችን ለመመገብ አይደለም።

        የተመድ የአካባቢ መርሃ-ግብር በአፍሪካ አነስተኛ ገበሬዎች የኦርጋኒክ አስተራረስ ዘዴን ተጠቅመው ምርቶቻቸውን እጥፍ እንደደረጉ በጥናታቸው አረግጠዋል።.114 በዚህ መሰረት ማዳበሪያና ጸረ-ተባይ መርዝ ከመግዛት በኦርጋኒክ ትግበራ ማለትም እንደ ኮምፖሲትና ዘር በመቀያየር የእህልና የአፈርን ምርታማነት በማሻሻል የኦርጋኒክ እርሻ ገበሬዎች ገንዘባቸውን ምርጥ ዘር ግዢ ላይ ማዋል ችለዋል።

        በአመሪካ የተደረገ ሌላው ጥናት እንደደረሰበት የኦርጋኒክ እርሻ ዘዴ ሶስት እጥፍ ምርት እንደሚያስገኝ ነው። የዚህ ከፍተኛ ምርት አንደኛውና ዋናው ምክኒያት ገበሬዎቹና በየዘር ወቅቶቹ መካከል እርሻቸውን እንደ ባቄላ ወይም አኩሪ አተር ባሉ የተፈጥሮ ናይትሮጂን ወደ አፈር የሚመልሱ የሌጊውም ተክሎች በመሽፋናቸው ነው።115

         የአለም የምግብ እጥረት እየተባባሰ በመሄድ ተጨመማሪ ሰዎች በየቀኑ ለረሃብ ተዳርገዋል፣ ስለዚህ የእንስሳት እርባታን በማቆም፣ በቆሎውን፣ እህሉንና አትክልቱን ለእንስሳት መመገብ ብንተወው፣ አሁን የምናመርተው ምግብ ሁለት ቢሊዮን ተጨማሪ ሰዎችን ለመመገብ ይችል ነበር።


        የጸረ-ተባይ መድሃኒትና ማዳበሪያን መቀነስ

        የኦርጋኒክ እርሻ ለእንስሳትም ጥሩ ነው፣ በፕላኔቷ ላይ ለሚገኙ ዛፎችና መሬትንም ጨምሮ ለሁሉም ፍጥረታት፣አንድም  በአሜሪካየአካባቢ ጥበቃ ድርጅትና በአውሮፓ ህብረት እንደ ካንሰር መንስኤ የሚወሰዱና ንቦችን የሚያጠፉ፣ ሌሎች ስማቸውን እዝህ መጥቀስ የማንችላቸውን እንስሳትንም የሚገድሉ የኬሚካል  ማዳበሪያና ጸረ-ተባይ መርዝ አይጠቀምም።

        በአሜሪካ የተደረገ አንድ እንዲህ ይላል፣ አሜሪካ ስምንት-ሚሊዮን ኤከር ( ሄክታር) መሬት ወደ ኦርጋኒክ ብትለውጥ የወተት ተዋጽኦ ጸረ- ተባይ መርዝ ስጋት በ97% ትቀንሳለች። ይህን (በአይነ-ህሊና) ማየት ትችላለህ? በተጨማሪም የኬሚካል ማዳበሪያና ጸረ-ተባይ ፍሳሽ በውቅያኖሶች ለሙት ቀጠናዎች መፈጠር አስተዋጽኦ ያደረጋሉ። ፕላኔታችንን በኬሚካል ማዳበሪያና ጸረ-ተባይ እየገደልናት ነው።116

        በአለም ከአምስት(ሁለት ኪሎግራም) ቢሊዮን በላይ ጸረ-ተባይ በያመቱ ጥቅም ላይ ይውላል! እናም 10% — 10% —ብቻ ነው እታሰበው ቦታ የሚደርሱት። ሌሎቹ ወደ አየርና ውሃ በመግባት በካንሰር መንስኤነት ሰውንና እንስሳቱን ያጠቃሉ፣ በውቅያኖሶችም የሙት ቀጠናን ይፈጥራሉ።

        በአውሮፓ አንድ ጸረ-ተባይ በቢለዮን ለሚቆጠሩ ንቦች ማለቅ ምክኒያት እንደሆነ፣ ሌሎቹ ደግሞ የወፍ እንቁላሎችን ሽፋን በማሳሳት ሽፋኑም ተሰንጥቆ በመሰባበር ጫጩቶቹ ያለጊዜያቸው ወጥተው እንዲያልቁ መንስኤ ሆኗል።117

        በተጨማሪም የኦርጋኒክ ምርት ከጂኤም አካላት የጻ ነው፣ የምግብ ይዘቱም በተለምዶ ከሚመረቱት የፍራፍሬና አትክልት ምርቶች ከፍተኛ ነው።


        አካባቢንና አፈርን ማሻሻል

        በፕላኔታችን ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ፣ ገበሬዎች ሁሉ፣ መታረስ የሚችለው መሬት ሁሉ ወደ ቪጋን አስተራረስ ዘዴ ቢቀየሩ/ቢለወጡ 40% የሚሆነው ካርቦንዳዮክሳይድ (CO2) ወዲያውኑ ይመጠጣል።.118

        ወደ ኦርጋኒክ እርሻ መቀየር በተለምዶ አስተራረስ ተሟጦ የነበረውን አፈር ለምነት/ጤንነት ይመልሳል። የላይኛው አፈር ጠንክሮ እንዲቆይና በተሻለ ሁኔታ ጎርፍና ጠንካራ ንፋስ ለመቋቋም ይችለላል። የዱር እንስሳትና ስነ-ምህዳሩም ሰላም ያገኘሉ፣ ያሸንፋሉ። በታለቋ ቢሪታኒያ በአንድ ትልቅ የኦርጋኒክ እርሻ ላይ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያስረዳው፣ ከተለምዶው አስተራረስ ጋር ሲነጻጸር፣ የኦርጋኒክ እርሻዎች ከ85% በላይ የሆኑ የእጽዋት ዝርያውች 71%ዎቹ የበለጠ ረዣዥሞችና ወፋፍራሞች እንደሆኑና የዱር እንስሳት ዝርያዎችም በጤናማነት መመለሳቸው ተረጋግጧል።119

        በተጨማሪም የኦርጋኒክ ቪጋን እርሻ አደገኛ የሙት ቀጠናዎችን የሚፈጥረውን የኬሚካል ማዳበሪያ ፍሳሽን ይገታል።

         

        ኢነርጂና ሃብትን መቆጠብ

        የኦርጋኒክ ቪጋን እርሻ ምርታማ ሲሆን፣ ከተለምዶው አሰራር እሰከ 37%  የበለጠ ኢነርጂ ይቆጥባል፣ የበለጠ ውሃን ያድናል።120


        መንግስታት ገንዘብ መቆጠብ ይችላሉ

        ለእንስሳት ከሚደረገው (እንዳይከስሩና ከገበያ እንዳወጡ) ድጎማ ጋር ሲነጻጸር ለኦርጋኒክ ቪጋን እርሻ የሚደረገው ድጋፍ ኦጅግ በጣም አናሳ ነው።

        የኦርጋኒክ ቪጋን እርሻ መንግስታትን ከትልቅ ወጪ፣ በጣም ትልቅ ገንዘብ ከማውጣት ሊያድናቸው ይችላል፣ እስከ 80% የሚሆን።121

        እሰቲ በአይነ-ህሊናችሁ የቀረጥ/ታክስ ገንዘብ የተሻለ ለመስራት ተሞልሶ ወደኛ ሲመጣ ተመልከቱ፣ ለምሳሌ የሙቀት-አማቂ ጋዞችን ለመሰርየት በሚደረገው የወጪ ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክት።


        የገበሬዎች ትርፋማነት

        ወደ ኦርጋኒክ አትክልት አምራችነት የተሸጋገሩ አነስተኛ የላቲን አሜሪካ ገበሬዎች ላይ  የተደረገ ጥናት ገበሬዎቹ  ፊት ከመያገኙት የበለጠ ከፍተኛ ምርት እንዳገኙ አሳይቷል።122 እንደተከበሩት የደች ሳይንቲስቶች፣ አለም ወደ ቪጋንነት ከተሸጋገረች መንግስታት አስር ትሪሊዮኖች የአሜሪካ ዶላር ማዳን ይችላሉ።123

        በርካታ ጥናቶች በአሜሪካ፡ በህንደና በኒውዝላንድም ተደርጓል። ሁሉም ይህንኑ ነው ያረጋገጡት፣የትርፋማነት መሰረቱ የማምረቻ ወጪዎቻቸው ከተለምዶ እርሻው የበለጠ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ ነው።

        የበለጠ የእህል ዝርያ አይነቶች- በቆሎ፣ አኩሪ አተርና አልፋ-አልፋ መጠቀም፣ መቀያየርም ይቻላል። በተጨማሪም የኦርጋኒክ አመራረት ተፈጥሯዊ ስለሆነ ከወትሮው እርሻ የበለጠ ድርቅን መቋቋም ይችላል።


        የምግብ ደህንነት ማሻሻልና ጤና

        በመጨረሻም ሁላችንም ከተሻለ ጤና ተጠቃሚዎች ነን፣ ምክኒያቱም ኦርጋኒክ ምግብ ከመርዝ የጸዳና የምግብ ይዘቱም የበለጸገ፣ የጂም ንክኪና ካንሰር-አምጪ ጸረ-ተባዮች መረዝ የሌለው ስለሆነ። የካንሰር፣ የልብ በሽታ፣ የስኳር በሽታ፣ ከመጠን-ያለፈ ውፍረት ወዘተ መንስኤ ከሆነው ከእንስሳት ተዋጽኦ በተጻራሪ በአርጋኒክ የተመረተ ፍራፍሬና አትክልት በርካታ የምግብ ንጥረ-ነገሮች የያዙና እነዚህን ዘመናዊ ሁኔታዎችና በሽታዎች ሁሉ ማሰወገድ ይቻላል። በእውነቱ የኦርጋኒክ ቪጋን ምግብን ነው መተማመን ያለብን፣ የደህንነታችን አስተማማኑ እርሱ ነውና። በርግጥ ለልጆቻችን ዸህንነት ልንሰጣቸው የሚገባ አስተማማኝና ከሁሉም የተሻለ ምግብ ነው።

        የኦርጋኒክ ምግብ ይዘት ከተለምዶው የፍራፍሬና አትክልት ከሚመረተው ከፍ ያለ ነው።  ለዚህ ነው የኛ ቡድን አባላት በተቻለ መጠን የበለጠ ኦርጋኒክን የሚያመርቱት።

                                          

         


        የስጋ እንፉስትሪ ሰራተኞችን ወደ አዲስ ስራ ሽግግር መደገፍ


        በስጋ እንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ሌለ ስራ እንዲሰሩ መንገር አለብን፣ ሌላ አዲስ ስራ በመስጠት የአዲሱንም ስራ ፋይዳ፣ ጤናማነቱና በንቃት የተሞላ፣ ሰላማዊ፡ በፍቅርና በደስታ የተሞላ መሆኑንም ማስረዳት ያሰፈልጋል። ሁላችንም ያንን ቀን ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን። ቢያንስ መሞከር ይገባቸዋል። እናም አንዴ ከሞከሩ እንደሚሰራ ይረዳሉ። ሁሉም ሰው ከሞከረ፣ ጎረቤቶቻቸውም ይሞክራሉ፣ ጓደኞቻቸውም ይሞክራሉ፣ እናም ተደጋጋፊ ኢነርጂ ይኖርና መላው አለም ይለወጣል።

        ከእንግዲህ ወዲህ መግደል ቀርቶ እንስሳትን ማርባት፣ ሁሉንም ማቆም ነው። ፕላኔታችንን ለመታደግ እንስሳት ማርባት ማቆም አለባቸው፣ ማራባትና ማረድ ማቆምና ህይወት/ምህረት መስጠት ነው። መንግስት ያለውን ስልጣንና ሃይል ተጠቅሞ ካስረዳቸውና ተለዋጭ ስራ ከሰጣቸው ነገሩን ሊረዱ ይችላሉ። በቂ መረጃ፣ ማብራሪያና የሚያስፈልጋቸውን ድጎማ፣ አማራጭ ስራ ሊደረግላቸው ይገባል፣ አማራጭ አድል ሊያገኙ ይገባል። አማራጮች አሉን።

        እኔ የማቀርበው ሀሳብ የስጋ እንዱስትሪ ሰራተኞች እንስሳቶቹን - አሳማ፣ ወይም ላም እንደቤት/ፔት ማስቀርት ይችላሉ። እንዳይዋለዱ/እስተርላይዝ (እንስሳቱ) መደረግ አለባቸው፣ ካለበለዚያ ወደኋለ መመለሳችን ወይም የባሰ ስለሚሆን እንስሳቱ በብዛት እንዳይራቡ / እንዳይባዙ መደረግ አለባቸው።

        በአሁኑ ጊዜ ገበሬዎች፣ ቸርቻሪዎችና አጓጓዦች የተሻሉ እድሎች አሏቸው። ይህንኑ ማድርግ አለባቸው፣ አሳማዎችን ከማጓጓዝ ኦርጋኒክ አትክልቶችን፣ ወዘተ መጓጓዝ ነው። ወይም የገበሬ ቸርቻሪዎች፣ ከስጋ ቢዝነስ ወደ ኦረጋኒክ አትክልት መሸጋገር ይችላሉ።

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *