IV. መያዶች የቪጋንን እንቅስቃሴ ያበረታታሉ
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሊረዱ የሚችሉበት ከሁሉም የተሻለው መንገድ ሁላችሁም በአንድነት ተንቀሳቅሳችሁ እንድ ቁጥር መፍትሄውን ሲታበረታቱ ነው፣ እናም እጅግ ውጤታማ የሆነውን - የቪጋን አመጋገብ - የአለም ሙቀት መጨመር ለማስቆም፣ ምክኒያቱም አሁን የአረንጓዴ ቴክኖሎጂን ውጤት ለማየት የመጠበቅ ብዙ ጊዜ የለንም። ይህን ብናደርግ እንኳን አረንጓዴውን ቴክኖሎጂ ለመትከልም ብዙ ጊዜ ይጠይቃል።
ስለዚህ የቬጅ አመጋገብ ቁጥር አንድ (መፍትሄ) ነው፤ ምክኒያቱም የስጋው እንዱስትሪ በፕላኔታችን ላይ የሚለቀው ከፍተኛውን ሙቀት ማመቅ ችሎታ ያለውን ጋዝ ነው፣ ብክለቱ እንኳን - ከ50%. የበለጠ ነው።140 እስኪ አስብ ከ50%. በላይ ጎጂ ጋዝ ብናስወገድና፣ ከዚያም ፕላኔታችን ቢያንስ 50%. ያህል ወዲያውኑ ትቀዘቅዛለች።
ወደ የኦርጋኒክ አመራረት ዘዴ ብንገባና፣ በፕላኔቷ ላይ የሚገኘው መታረስ የሚችለው መሬት ሁሉ ለኦርጋኒክ እርሻ ብንጠቀም፣ ይህ ራሱ 40% የሚሆነውን ካርቦንዳዮክሳይድ ከከባቢ አየር በተጨማሪ ሊያስወግድልን ይችላል። በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው በአንድነት ፕላኔቷን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊያቀዘቅዟት ይችላሉ።
ይህ ምንም ምስጥር ወይም አስማት አይደለም፤ ሳይንሳዊ እንጂ። ይህ በሚገባ የተረጋገጠ ነው፣ ግልጽም ነው።
ስለዚህ በኮፐንሃገኑ የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ የመንግስታቱን ትኩረት ለመሳብ በአንተና የማደራጀት፣ መረጃ የመስጠትና በግልጽ የመናገር ችሎታህን ነው የምተማመነው። እባክህ የተሻለህን ሁሉ አድርግ። አንተን ከሰሙ በኋላ መንግስታቱም መፍትሄውን የበለጠ አጉልተው ሊያወጡ ይችላሉ።
በአለም ውስጥ እንዴት ገንቢ እንቅስቃሴ መጀመር እንደሚገባቸው መያዶች በሚገባ ያውቃሉ። ለፕላኔታችን በጣም፣ በጣም አስፈላጊና በጣም ጠቃሚ ናቸው። ተግባራቸውን አንዴ ከጀመሩ ሁሉም መያዶች ለሰው ልጆችና በህይወት ለመቀጠልም በጣም፣ በጣም ጠቃሚ ናቸው። እናም በዚህ ቅጽበት/ጊዜ የሁሉንም የመያዶች፣ የመንግስት፣ የብዙሃን መገናኛ/ሚዲያ፣የህዝቡ፡ የእነ,ያንዳንዱ ግለሰብ ጥረትና ተሳትፎ አስፈላጊ ነው።
ፕላኔታችን በመቃጠል ያለች ቤት ናት። ተባብረን በአንድ መንፈስ ካልሰራንና እሳቱን ካላጠፋን ከንግዲህ ወዲህ መኖሪያ የሚባል ቤት አይኖረንም። መቶ በመቶ የአለም ህዝብ በአስቸኳይ ቪጋን በመሆን ፐ/ላኔቷን መታደግ አለበት።
የልቀቱን ግብ መምታት እንችላለን፣ ነገር ግን በብስለት ቅድሚያ መስጠትና ማስፋፋት/ማሳደግ አለብን። በመጀመሪያ ብቸኛውንና ትልቁን ሰው-ሰራሹ የሚቴን ምንጩን ማለትም እንስሳቱን ማስወገድ ነው። የእንስሳት እርባታን አቁም፣ ከዚያም የአለም ሙቀት መጨመርን እንገታለን - በጣም ቀላል ነው። ምክኒያቱም የእንስሳት ተዋጽኦ የአለም ሙቀት መጨመር መንስኤ ነው። ይኸው ነው፣ በጣም ቀላል፣ እቅጩ ይህ ነው፣ ምንም ምስጢር የለውም፣ ምንም አስቸጋሪም አይደለም።
በውነቱ አሁን እንደአተያሀው ከሆነ ፕላኔቷን መታደግ አንችልም። በእንቅስቃሴያችን የዘገየን ነን፣ አለምን ለማዳን ዘግይተናል። ስለዚህ መጀመሪያ ቬጅ መሆን አለብን፣ ምክኒያቱም ይህ አረንጓዴም መሆን ነውና። ከዚያም ሌላ ማንኛውምን የአረንጓዴ ቴክኖሎጂን መስራትና መትከል እንችላለን።
እናም ገነትንም በምድር ላይ ይኖረናል፣ ምክኒያቱም ቬጅ መሆን ሁሉንም ነገር በቅጽበት ይቀይረዋል/ይለውጠዋል፣ ከአካባቢ እስከ የሰዎች አስተሳሰብ፣ ረሃብ የከሰመበት፣ በእውነት የሰውልጅ ወንድማማችነት ያሰፈነበት፣ ደረጃውን ወደ ጠበቀና ሰላም የሰፈነበት አለም ይኖረናል።
ሙቀቱ የተረጋጋበት፣ ስነ-ምህዳሩ ሚዛኑን የተስተካከለ፣ እንስሳት በሰላም የሚኖሩበት፣ ሰዎችም ጤናቸው የሚጠበቅበትና ደስታን የጎናጸፉበት፣ አዳዲስ ነገሮችን የሚሰሩበት/የሚያገኙበት፣ ከዚህ በፊት አስበን የማናውቀው ህልም የሚመስል ገነት እንፈጥራለን።

Supreme Master Ching Hai International Association Members
promoting the vegan solution during COP15 in Copenhagen, Denmark, 2009.