ምዕራፍ ስድስት
የሰው ልጅ ወደ ወርቃማው ዘመን መመንጠቅ
እንደ ባለመብቱ የፍጥረታት ዘውድ፣ መልካም አስተዳዳሪዎችና ጠባቂዎች፣ እና በምድር ላይ የገነት ልጆች፣ የለውጥ፣ መነሳት፣ እድገትና ቀና ብሎ የመቆም ወቅት እየመጣልን ነው፡፡ ተደርጎ የማይታወቀውን ወደ ወርቃማው ዘመን ምጥቀትን፣ የርህራሄ፣ የመተቃቀፍ፣ የደግነት፣ የሚጠብቀንን እውነተኛ ሰላም አብረን እውን እናድርግ፡፡ ይህን እውን ማድረግ እንደምንችል አውቃለሁ፡፡