• ምእራፍ አራት. የቪጋን ፖሊሲና ህግ ማውጣት> በሰው ኣዝጋሚ እድገት ውስጥ አቅጣጫ የመቀየር ቅጽበት
      • I. በሰው ኣዝጋሚ እድገት ውስጥ አቅጣጫ የመቀየር ቅጽበት

        በትክክለኛው አቅጣጫ የእያንዳንዳችን አንድ ትንሽ እርምጃ መውሰድ እንደ የሰው ዘር እድገት ትልቅ ምጥቀት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ትንሹ እርምጃም በጣም ቀላል ነው፡፡ አለ መገድል ብቻ ነው፡፡ ኑር አኑር በሚለው መርህ መኖር ነው፣ ህይወት ስጥ ህይወት ለማግኘት በሚባለው የዩኒቨርስን ህግ መገዛት ነው፡፡ ምክኒያቱም ተመሳሳይ ነገሮች እንደሚሳሳቡ ምናውቀው ነዋ፣ ይህ የቪጋን አመጋገብን የሚጨምር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

        ሰው ልጆች ከልባቸው ለጋሶችና ሰላማዊ ናቸው፣ ሁላችንም መረጃ ያለ ማግናት ጉዳይ ነው ነገሩ፣ ለረጂም ረጂም ጊዜያት ያለ መረዳታችን ጉዳ ነው፡፡ ስጋ ጥሩ ነገር መስሎን ነበር፣ ወተት ጥሩ መስሎን ነበር፣ አሳ ጥሩ መስሎን ነበር፣ እንቁላል ጥሩ መስሎን ነበር፡፡ የተሳሳተ ነገር ነው፡፡ ተቃራኒው ነው፡፡ እነዚህ ጥሩ ናቸው ተብለው የተነገሩን ነገሮች - እንደ ስጋ፣ አሳ፣ ወተት፣ እንቁላል፣ ማንኛውም የእንስሳት ውጤት ጥሩ ናቸው” – ተብሎ የተነገረን የተሳሳተ መሆኑን ተረጋግል፡፡ የጥሩነት ተቃራኒ ናቸው፡፡ ስቃይን፣ በሽታንና ትልቅ የገንዘብ ኪሳራን ነው ያመጣብን ለህክምነናና ለተያያዙ ስራዎች፡፡ስለሆነም ለረጂም ረጂም ጊዜያት ወደ በተሳሳተ አቅጣጫ ስንመራ ቆይተናል ማለት ናው፡፡ አሁን ምርምር ማካድ አለብን፡፡ አዋቂዎቹን ዶክተሮችና ሳይንቲስቶች የሚሉትን መስማት አለብን፡፡ የምርምር ውጤቶቻቸውን፡ ስጋና የእንነስሳት ተዋጽኦዎች በርግጥ፣ በርግጥ መርዝ የመሆናቸውን ማየት አለብን፡፡ አሁኑኑ ማቆም አለብን፣ በተለይም ለልጆቻችን ስንል ማቆም አለብን፡፡ ከእግዲህ ወዲያ ምንም አቅም.ረዳት የሌላቸውንነ ልጆቻችንን በመመረዙ መቀጠል የለብንም፡፡ ምስኪኖቹ ህጻናት እኛን ነው የሚተማመኑት፣ እኛ የተሻለ የምናውቅ ይመስላቸዋል፣ ነገሩ የኛ ስህተት አይደለም፡፡ መመለስ ነው/ ዘወር ብለን ማየት ነው ያለብን፡፡

        ለምንድርነው የኛ ስህተት ያልሆነው? ምክኒነያቱም እንደዚያ ነው የተማርነው፡፡ አያቶቻችን፣ ቅድመ-አያቶቻችን እንደዚያ ነው የተማሩት፡፡ ለእለታዊ ኑሮኣችን ስለምንሯሯጥ፣ ሥራ ስለሚበዛብን ምርምር ለማካሄድ ጊዜ አላገኘንም፣ በመሆኑም እነዚህ ነገሮች በእውነት መርዝ መሆናቸውን አልተረዳንም ነበር፡፡

        ከሁሉም በላይ ፕላኔታችንን እየበላናት ነው፡፡ ሰው መግደል ብቻ አደለም፣ እንስሳት መግደል ብቻ አይደለም፣ ፕላንታችንን መግደል ነው፡፡ እናም አለማችንን ለማዳን ይህን ማቆም አለብን፡፡ መመለስ ነው ያለብን፡፡ በተቃራኒው አቅጣጫ መራመድ ነው ያለብን፣ ማንንም ሳናሰቃ፣ በትክክለኛው ጎዳን ነው መሄድ ያለብን፤ ፍጥረታትን ማፍቀርና መንከባከብ እንጂ፣ ተጨማሪ ህይወት ሳናጠፋ ማለት ነው፡፡ ያ ነው የሰው ልጅ የምሻው ምጥቀት፡፡

        ይህንን ምጥቀት እውን ካደረግን በፍጹም ልዩ ስሜት ይኖረናል፡፡ በንቃተ-ሂሊና ከፍተኛ ደረጃ እንደደረሰን ይሰማናል፡፡ እሰቲ ጥልቅ፣ ጠንካሮች፣ ኢንተሌጀንትና ችሎታ ያለን እንደሆን አስብ፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ለምግብነት መትከል/ማምረት እንችላለን፣ እናም ሌሎችን ለማጥቃትና ለማዋከብ፣ ለማሰቃየት፣ ምንም ጉዳት ያላደረሱብንን፣ ንጹሃኑን፣ ምስኪኖችና ትንንሾቹን እንነስሳት ፍትረታት ለመግደል የበላይነታችንን/ሃይላችንን፣ ኢነተሌጀነሳችንን፣ ችሎታችንን መጠቀም የለብንም፡፡ በህግ ፊት ንጹሃን ናቸው፡፡ እናም ንጹሃን ፍትረታትን ከገደልን እኛ ነን ማቀጣት የሚገባን፡፡ አስቀይሜያችሁ ከሆነ አዝናለሁ፣ ነገር ግን ይህ እውነት ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ትረዱኛላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡

        በዚህ የእድገት ምጥቀታችን፣ ይህንን ፍራቻና መስገብገብ የተጠናወተውን ኑሮ ትተን ወደ እውነተኛው ሰላም፣ ፍቅርና ብሩህ የተሞላበት - ከግድያ፣ስቃይና አመጽ አዙሪት ወደ ፍቅራዊ ደግነት፣ እንክብካቤና ደስታ ለመሸጋገር እንችላለን፡፡

        ደካማው ጠንካራውን የማይፈራበት፣ አመጽ የሌለበት፣ በአጎራባቾችና በተራራቁም ወገኖች መካከል ጦርነት የማይኖርበት፣ የምታደርገውን በማጣት በሀዘኔታ በተጨበጠች እናት ፊት አንድም ህጻን በረሃብ፣ በውሃ ጥማት ወይም በህመም በየጥቂት ሰኮንዶች፣ በየቀኑ የማይሞትበት አለም ማሰብ እንችላለን?

        ደካማው ጠንካራውን የማይፈራበት፣ አመጽ የሌለበት፣ በአጎራባቾችና በተራራቁም ወገኖች መካከል ጦርነት የማይኖርበት፣ የምታደርገውን በማጣት በሀዘኔታ በተጨበጠች እናት ፊት አንድም ህጻን በረሃብ፣ በውሃ ጥማት ወይም በህመም በየጥቂት ሰኮንዶች፣ በየቀኑ የማይሞትበት አለም ማሰብ እንችላለን?

        አሁን በመናገር ላይ እለሁ በሂን ቦታ ብዙ ህጻናት እለቁ ናቸው፡፡ በየጥቂት ሰኮንዶች ውስጥ፣ አንድ ህጻን በረሃብ ይሞታል፡፡ ይህን እያየን/እያደረግን መቀጠል አንችም፡፡ መቆየት አንችም፡፡ ህይወት ማዳን አለብን - የእንስሳትን ህይወት ብቻ ሳይሆን፣ የልጆቻችንን ህይወት እንጂ፤ የራሳችን ልጆችም ባሆኑ፣ የሌሎት ሰዎችን ልጆች ማዳን አለብን፡

        ስጋ በርካታ ስቃዮችን መሰረት ነው፣ ምክኒያቱም የረሃብና ጦርነት መንስኤ ነው፡፡ ያለንን እህል፣ ጥራጥሬና አኩሪ አተርና ጥሩ ጥሩ ሃብቶቻችንን፣ መሬትና ውሃ የስጋ እንዱስተሪን ለመደጎም ስለምናውለው አለም የምግብና ውሃ እትረት አጋጠማት፡፡  ስለዚህ ህይወትን ማዳን ከፈለግን የስጋ እንዱስትሪን ማቆም አለብን፡፡

        አሁን የምንኖርበት መንገድ የዘቀጠና ከማንነታችን ጋር የማይመጥን ነው፡፡ በመሰረቱ እኛ የእግዚኣብሄር ለወጆች ነን፣ በፍቅር የተሞላንና ደጎች፡፡ የገነት ወራሾች ነን፡፡ ረስተን እኮ ነው እንጂ፡፡ ወደዚህ አለም መጥቶ ያገኘውን ሁሉ ለመብላት የሚፈልግ እግዚኣብሄርን ማሰብ እንችላለን? እንደዚህ ያለ እግዚኣብሄር ካለ የእርሰ ልጅ መሆን አልፈልግም፡፡ የዚያ አይነት  እግዚኣብሄር ልጆች መሆን ትፈልጋላችሁ? እሺ፣ አትፈልጉም፡፡ አመግናለሁ፡፡ አመግናችለሁ፡፡ እንዲህ ደጎች ናችሁ፡፡ እግዚኣብሄር መሃሪ፣ ርሁሩህ፣ ሁሉንም አፍቃሪ ከሆነና እኛም የእግዚኣብሄር ልጆች ከሆን፣ እንግዲውስ እንደ የ እግዚኣብሄር ልጆች በምድር ላይ መራመድ እንዳለብን ማሰብ የለብንምን?

        በፍቅርና በርህራሄ መራመድ አለብን፡፡ አባታችንን መወከል አለብን የእርሰን ስም ታላቅነት ለማሳየት ከፈለግን፡፡ በየቀኑ ሁልጊዜ እንጸልየለን፣ ስምህ በሰማይ እንደተቀደሰች እንዲሁም በምድር ትቀደስ፣ነገር ግን ስሙን ለመቀደስ ምን ማድረግ ይኖርብናል?፡ እርሰን መወከል/ሆነን መገኘት፡፡

        ሁልጊዜ ወደ እግዚኣብሄር እንጸልያለን፣ ምክኒያቱም እግዚኣብሄር መሃሪ፣ ጠባቂ፣ ርሁሩህና ፍቅር ስለሆነ ነዋ፡፡ እኛ የእግዚኣብሄር ልጆች ስለሆን የእርሰን እሴቶቸ መወከል አለብን፡፡ እኛ እነዚህ እሴቶች ነን፡ ፍቅር ነን፡፡ በተሳሳተ አቅጣጫ ተመርተን፣ በተሳሳተ መረጃ ተሞልተንና ረስተን ነው እንጂ፡፡ እባካችሁ ይህንን አስታውሱ፡፡ እነዚህ እሴቶች በጥልቀት እውስጣችን ይገኛሉ፣ ስለዚህም በዙሪያችን ከምናየው የተሻለ ነገር እንዳለ እናውቃለን፡፡

        በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ የህይወት አርአያነታቸው ሰውን ቀና እንዲል የሚረዱና ዛሬም የሚያንጸባርቁ - መንፈሳዊ መምህራን ብቻ ሳይሆኑ እንደ ፕላቶ ያሉ የፍልስፍና ሰዎች፣ አንደ ሶቅራጠስ ያሉ የስነ መንግስት ያሉ፣ እንደ ፓይታጎረስ ያሉ የሂሳብ ሊቆችና አሜሪካዊው ገጣሚ ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን ነበሩ፡፡ እነዚ ሁሉም ቬጀታሪያን ነበሩ፡፡ ተገረምክ/ተደነቅህ ዴ? በፍጹም፣ አልተገረምክም፡፡ ለኔ የተገረምክ አትመስልም፡፡ ያን ሁሉ ታውቃለህ ማለት ነው፡፡ ሁሉም ታላላቅ ሰዎች ቬጀታሪያን ወይም ቪጋን ናቸው፡፡ ስለዚህ በጥንቃቄ ብናጠና፣ መሰረታዊው የሰለጠነ ኑሮ አስተምሮታቸው የቪጋን አመጋገብ መሆኑን እናያለን፡፡

        የቪጋን አመጋገብ የመጀመሪያው፣ ታላቁ የርህራሄ ተግባራት አንዱና የሌላውን ህይወት የማይጎዳ፣ አካባቢውን እን  የማያበላሽ ነው፡፡ በስጋ ላይ የተመሰረተ አመጋገብን ከቪጋን ጋር ብናነጻጽር [በስጋ ላይ የተመሰረተ አመጋገብ] አስራ አራት ጊዜ ያህል የበለጠ ውሃ፣ ስድስት ጊዜ የበለጠ እህል፣ አስር ጊዜ ያህል የበለጠ ኢነርጂ፣ እና ከሃያ ጊዜ በላይ የበለጠ መሬት ይወስዳል፤ ብዙ ጊዜ ውዱን የዝናብ ደን በማውደም፡፡

        ቪጋን መሆን፣ ብቸኛውን ቤታችንን ከማትረፍም በላይ ጸጋ የተሞላበት ጥሩ ስራ ነው፡፡ ፕላኔታችንና ነዋሪዎቹን ያነሰ መጉዳትና ማበላሸት ያነሰ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ አሁን የምንከፍለው ግን በጣም ውድ ዋጋ ነው፣ የስጋ/የእንስሳት እንዱስትሪን ካላቆምን የበለጠ ዋጋ እንከፍላለን፡፡

        የበለጠ ፍቅራዊ ደግነታችንን በመሰንዘርና ሁሉንም ፍጥረታት በመንከባከብ ቁጥር የበለጠ በአለም ታላቆች እንሆናልን፤ በልባችንና በመንግስተ-ሰማያት የበለጠ የትልቅነት ስሜት ይኖረናል፡፡ ስለዚህ ነው የቀድሞ ማስተሮችና የተከሰተላቸው ነብሶች ለመጎዳት ካልፈለግህ ሌላውን ፍጥረት አትጉዳ ብለው ያስተማሩን፡፡ በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ ብታይ፣ ሁሉም የሚሉት አንድ ነው፣ ይህን አረፍተ-ነገር፣ ይህን ትርጉም ነው ያለው፡፡ ለኛ መልካም የሆነ፣ ለሌሎቹም ማድረግ አለብን፤ የዘራነውን ነው የምናጭደው ያለ ምንም ሳንካ፡፡ ለዚህ ነው እንስሳትን እንዳንገድልና ቪጋን እንድንሆን የሚያስተምሩን፡፡

        ይህንን ምጥቀት እውን ካደረግን፣ በአመጋገባችን ላይ በጣም ትንሽ ለውጥ ካደረግን፤ ከስጋ ይልቅ፣ ከእንስሳ ፕሮቲን ይልቅ የአትክልት ፕሮቲንን ከመረጥን፣ አንደኛ ደረጃ ነውና፡፡ የእንስሳ ፕሮቲን ሁለተኛ ደረጃ ነው፣ ለምን? ምክኒያቱም አንደኛ ደረጃ የሆነውን አትክልትን፣ እና ፍራፍሬ ተመግበዋልና፤ ከዚያም ስጋቸውን በሉ፡፡ ያ ሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ እኛ ሰዎች ነን፣ ለምንድርነው ሁለተኛ ደረጃ የሆነውን ነገር እንመርጣለን? አይጠቅንም፡፡ ስለዚህ ይህን ምትቀት እውን እናድርግ፡፡

        ክቡራንና ክቡራት፣ ይህን ምጥቀት እውን ማድረግ አለብን፣ ምክኒያቱም እውን ካደረግነው ወርቃማው ዘመን ከመቅስጽበት በመከሰት፣ ያለ ምንም ቀጣይ የህይወት ማጥፋት - ያለ ጊዜ በየአመቱ የአስር ቢሊዮኖች ሞትን! የሰላም ኑሮን ያበስራል፡ ለጊዜያዊ ደስታ ግዲያና ማሰቃየት፣ ያውም መተካት የምንችለውን፡፡ ስጋ መተካት የሚችል ነገር ነው፡፡

        ገና ያልደረስንባቸው ብዙ ምድራዊ ተኣምራት አሉ፣ ሊገለጹልን የሚገቡ በርካታ የሳይንስ እውቀቶች፣ ሊሰሩ፣ ሊዳብሩና ሊፈለሰፉ የሚችሉ  የማይታመኑ ቴክኖሎጂዎች አሉ! የተሻሉ የማህበራዊ ስርኣቶችም አሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ከወቅቱ የሎጂክ ደረጃችን በላይ እንዲያውም ከምናስበው በላይ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እውን ልናደርጋቸው የምንችለው ውስጣዊ ጥበባችንና የፈጠራ ችሎታችንን መጠቀም ስንችል ብቻ ነው፡፡

        ይህን ጥበብ ለመክፍት፣ መጀመሪያ ጎጂ፣ እንቅፋት፣ አፋኝ የሆኑ ነገሮችን፣ እንደ ስጋ፣ ወተት አሳ፣ ዶሮና በአጠቃላይ የእንስሳት ውጤቶችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ነገሮች ኢንተሌጀንሳችንን ያፍናሉ፣ እድገታችንን ያዘገያሉ፣ መንፈሳዊ፣ ሞራላዊ ብቻ ሳይሆን የቴክኖሎጂውንም፡፡

        በመጨረሻም፣ ለአዲሱ ወርቃማ ዘመን ከግል ፍላጎትና/መጓጓት ምክኒያቶቻች በተጨማሪ፣ ስለፕላኔታችንም ማሰብ፣ እንደምታውቁ እርግጠኛ ነኝ ፣ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን፡፡ ስለዚህ፣ ይህ የንቃተ-ሂሊና ምጥቀት ፕላኔታችንና ሁሉንም ሌሎች  ፍጥረታትን ለመታደግና ልንኖርባትን ለሚገባን የተዋደደ/የተሳሰበ አለም አስፈላጊ ነው፡፡

        ሁሉም ሰው ይህን ለውጥ ወይም ምጥቀት እውን ቢያደርግ ፕላኔታችንነ መታደግ እንችላለን፡፡ እግዚኣብሄር ምስክሬ ነው፣ ባለኝ ክብር ሁሉ ቃል እገባለሁ፡፡በተመሳሳይ ጊዜ ከፍ ከፍ እንላለን፣ ምንም እንኳን ብዙ የዘገየን ብንሆንም፡፡


        የሰው ልጅ በእድገት ለመራመድ ዝግጁ ነው


        የሰው ልጅ በንቃቱ ከፍ ከማለት የዘገየ ነው፡፡ የተቀደሱሩ፣ ደግና ርሁሩህ መሆን ነበረባቸው፡፡ ቬጅ ሁን፣ አረንጓዴ ሁን፣ መልካም ተግባር ስራ፣ ለፕላኔታችን ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ልጆች ክብር፣ መንፈሳዊ እሴቱም እንጂ፡፡ ለክብራቸው ሲባል ይህን መተግበር አለባቸው፡፡

        ለሌሎች ወደ ማሰብና ወደ ርሁሩህ ተፈጥሯችን፣ ወደ ውስጥ ልባችን መመለስ አለብን፡፡  ያ በጣም ቀላል ነው፡፡ ያ ነን እኮ፡፡ ርሁሩህ ነን፡፡ መሃሪዎች ነን፤ ለሌሎች አሳቢዎች ነን፡፡

        በእውነት እርሰ በርሳችን እና ከእንስሳቱ፣ ከተፈትሮና ከመንግስተ-ሰማየት ጋር መተሳሰብን፣ መቀራረብንና መዋሃድን ከፈለግን ራሳችን ያንን ሆነን መገኘት አለብን፣ ከልብ በመተሳሰብ መኖር መብላትም በዚሁ ስለሚካተት ወደ ጠረጴዛችን በምናመራበት ጊዜ ሁሉ ይህንኑ ማስታወስ አለብን፡፡ 

        የቪጋን ምርጫ ማድረግ እንግዲህ የሰው ልጅ ወደ እውነተኛ የመፈቃቀድን እርምጃት መጀመሩን አመልካች ነው፡፡ እንደምናውቀው ተመሳሳይ ነገሮች እንደሚሳሳቡ ሁሉ፣ መፈቃቀድ የበለጠ መሳሳብን ያመጣል፡፡ ይህን ርሁሩህነት ለሌሎች በማካፈል ሰብኣውነታችን የበለጠ መምጠቁ ብቻ ሳይሆን አለማችን ከፍ ትላለች እንጂ፡፡

         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *