II. የምድራችን ወደ ከፍተኛ ጋላክቲክ ስልጣኔ መምጠቅ
የፕላኔታችን መምጠቅን በሚመከለከት፣ ያ የፕላኔታችን ልትደርስት የሚገባ ዩኒቨርሳዊ እቅድ አካል ነው፤ ወደ ከፍተኛው የመለኮታዊ እድገት መምጠቅ ይኖርብናልና፡፡ ያ እቅድ አለ፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ ፍላጎቱን ለማራመድ ነጻ ነው፣ ይህን ነጻነት ግን በአግባቡ አልተጠቀመበትም፡፡
ከማርስና ቬኑስ ተማር
በጋላክሲ ውስጥ የምድራችን ከሌሎች (ፕላኔታች) ጋር መዋሃድ - ያ ትልቅ ራዕይ ነው፡፡ በአጎራባች በሚገኙ ፕላኔቶችን ነው ማየት ያለብን፡፡ ማርስና ቬኑስ፣ ራዕዩ ደብዛዛ ነው በማለት፣ ትክክለኛ ምርጫ ካላደረግን፣ አሁኑኑ ትክክለኛ ለውጥ ካላደረግን አደገና ነው፡፡
ማንኛውም የፕላኔቷ ሳይንቲስት እንደሚያውቀው በታርካቸው ውስት ማርስና ቬኑስ አስገራሚ የከባቢ አየር ለውጦችን አስተናግደዋል፣ እኛ አሁን ማስተናገድ የጀመርነውን አይነት ማለት ነው፡፡ ጥንት፣ ከረጂም ጊዜ በፊት ማርስና ቬኑስ እንደኛዋ ፕላኔት - ውሃ፣ ህይወትና ሰዎችም ነበራቸው፡፡ ነገር ግን የማርስና ቬኑስ ነዋሪዎች ከመጠን ያለፈ እንስሳትን በማርባት የመኖሪያ ፕላኔቶቻቸውን አጠፉ፤ የተለቀቁት ጋዞች ማቆሚያ የሌለው ሙቀት አማቂ ጋዞችን አስከተሉ፣ በተጨማሪም በማርስ ላይ መርዛማው የሃይድሮጂን ሰልፋይድ ተለቀቀ፡፡ ስለዚህ ነው ዛሬ መሬትና ውቅያኖስ የነበሩበትን ቦታዎችን የምናየው፡፡
እንደ ቬኑስና ማርስ ሁሉ ወደ አምስት ቢሊዮን የሚጠጉ ፕላኔቶች በተመሳሳይ ሁኔታና አጋጣሚ ጠፍተዋል፡፡ ነዋሪዎቻቸው በዝቅተኛ የንቃተ-ህሊና ደረጃ ላይ የሚገኙ ፕላኔቶች ናቸው የወደሙት ወይም የጠፉት፣ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉት አይደለም፡፡
እናም በቬኑስ ላይ የከባቢ አየሩ በመሞቅና በCO2 በመታፈን—ካርቦንዳዮክሳይድ ሳይነቲስቶች “ያልተገራ የአለም ሙቀት መጨመር” ብለው የሚጠሩት ነው፣ እናም ይህ ምድራችን ወደፊት የሚገጥማት የሚችል ማለት ነው፡፡
እንደ ቬኑስ ያሉ ከጥፋት የዳኑት ፕላኔቶች ነዋሪዎቻቸው ቪጋን በመሆናቸው - የተረፉትን ማለቴ ነው፡፡ አራት ቬኑሶች እንደነበሩ ነግራችኋለሁ - ሁለቱ ብቻ ናቸው የተረፉት፣ ምክኒያቱም ህብተሰቦቻቸው ቪጋን ነበሩ፡፡ ሌሎቹ ሁለቱ ቬኑሶች ወደሙ - አንድዋ እነዳለች ጠፋች፣ ሌላኛዋ እየፈላች፣ እየተንቦገቦገች ነው፤፣ ህይወት አልባ ናት፣ ምክኒያቱም ቪጋን ስላልነበሩ ነው፡፤
አብዛኛው የማርስ ህዝብ የቬጅ አመጋገብ መፍትሄው መሆኑን አላውቀም ነበር፣ አላዳመጠምም፡፡ ማርሳዊያን ያጋጠማቸውን ጥፋት/ ውድመትና ስቃይ የሚረሱት አይደለም፣ የደግነት መልእክታቸውን ለሰው ልጆች ወደ ምድር ልከውልናል፡፡ መልእታቸው፡ መልካም ተግባራትን ስሩ፣ ጊዜው ከመዘግየቱ በፊት ቤታችሁን ታደጉ የሚል ነው፡፡
መጨረሻውን ተቃርበናል፣ ከማንመለስበት ጫፍ ላይ ደርሰናል፡፡ ለዚህ ነው አሁን በተከታታይ የመፍትሄውን መልእክት የምናሰራጨው፡ የቪጋን አመጋገብ፡፡ ይህ የአለም ሙቀት መጨመርን ለመግታት አካላዊ ሃይልን ይሰጠናል፣ ምክኒያቱም የሞራል ሃይል አለውና፡፡ እንደ “ተመሳሳይ ነገሮች ይሳሳባሉ” ያሉ ሳይንሳዊ ሃይልም አለው፡፡ ህይወትን ማክበር አለብን፣ እናም ህይወትን እናገኛለን ማለት ነው፡፡
የተቀደሱ/የተከበሩ የጋለክሲ ጓደኞቻችን እየጠበቁን ናቸው
ብዙ ቬጀታሪያን ያልሆኑ ፕላኔቶች እነዳሉ ሁሉ ቬጀታሪያን ፕላኔቶችም አሉ፡፡ ብዙ፣ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ በጋለክሲያችን ብቻ በጣም ብዙ አሉ፡፡ እነዚህ የቬጀታሪያን ህብረተሰብ ፕላኔቶች ከኛ የበለጠ የመጠቁ ናቸው፡፡ የመጓጓዣ ቀበቶዎችም አሏቸው፡፡ ከምናስበው በላይ ናቸው፡፡
በነዚያ ህብተሰቦች ውስጥ የሚገኙት ህዝቦች በአብዛኛውን ጊዜያቸውን በመዝናናት ነው የሚያሳልፉት፣ ሆቢያቸውንና ችሎታቸውን በማዳበር ዋናውን ችሎታቸውን ለመጠቀም ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በእነዲህ አይነቱ ህብረተሰብ ብዙ አስገራሚ ፈጠራዎች ይፈለፈላሉ፡፡ እናም ብዙ አስደናቂ ነገሮች ይከሰታሉ፣ ምክኒያቱም ሰዎቹ ሳይጨነቁ በመዝናናት የተሻለ ሊሰሩ የምችሉትን ነገር ስለሚሰሩ ነው፡፡ ማንም ስለቁሳዊ ነገሮች እጦት አይጨነቅም፤ በመሆኑም ህይወታቸው በደስታና በነጻነት የተሞላ ስለሆነ፡፡ ይህ አያስደንቅም? በጣም ደስ አይልም?
እነዚህ ማህበረሰቦች ሁሉም ቪጋን መሆናቸውን ነግራችኋለሁ፡፡ የህይወት ጽንሰ-ሀሳባቸው ግልጽ ነው - በጣም ግልጽ፣ በጣም ለሌላው የሚያስቡ፣ ያለምንም ለራስ ጥቅም፣ በጣም ኢንተሌጀንት ናቸው፡፡ ቪጋን ማህበረሰብ ያልሆነ፣ እንደዚህ አይነት የመጠቀና ደስተኛ፣ ፈንዳቂ የሆነ አንድም ስልጣኔ አላየሁም፡፡
መግደል አንዴ ካቆምን በጋላክሲው ውስጥ ለሚገኙ የተከበሩና የተቀደሱ ፍጡራን የበለጠ የፍቅር፣ የደግነትና ጋባዥ አካባቢና ሁኔታን በመፍጠር ምናልባትም ወደኛ እንዲመጡ ወይም ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ እንችላለን፡፡
እንደምንም ብልን የዚህ አይነቱን ፕላኔት ለማወቅ እድሉን ካገኘን ወይም እንደዚህ ያደገ ፍጡር ካወቅን የዚያ ፕላኔት ወይም የሰዎቹ ደስታና ሰላም፣ ስለዚህ አለም ቁሳዊ ሃብትና ዝና ባለመጨነቅ፣ እዚያ እንድነገኝ ስሜት ይጭርብናል፡፡ እነርሱን ለማግኘት እድሉ ከገጠመን ይህንን አለም በማንኛውም ጊዜ መተው እንተዋለን፡፡ ነገር ግን እንደነርሱ ያደግን ስላልሆን - በመንፈስ፣ በአዕምሮና በስነ-ልቦናና በመልካም ተግባራት አኳያ- ጥቂቶቻችን አይደለንምና፣ ወደነርሱ መጠጋት አንችልም፣ እነርሱን መቀላቀልም አንችልም፣ ፕላኔታችንም በነርሱ ደረጃ የምትመደብ አይደለችም፡፡
ስለዚህ እነርሱ በጉጉት ነው የሚጠባበቁን፡፡ እነርሱ ከደረሱበት እንድንደርሰ፣ ከመላው ጋላክሲ ጋር እንዲንቀላቀል የእድገት ፍጥነታችንን እነድንጨምር መልእክቶች እየላኩልን ነው፤ የመንፈሳዊ ደረጃችን ግንዛቤያችን፣ አዕምሮኣዊ ችሎታችን እንዲሁም ቴክኖሎጂኣችን ከፍና እነድናድግ እነርሱ ምንጊዜም እኛን ለመርዳት ቆመው ነው የሚጠብቁን፡፡
ፍላጎታቸውን በኛ ላይ መጫን ኤፈልጉም፡፡ እየጠበቁን ናቸው፣ እየጠበቁንና መዘጋጀታችንን እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ዩኒቨርስ በሚጠይቀው ከፍተኛ ደረጃ መሰረት ኑሯችንን መራት ካልመረጥን ውስጣዊ ሰላምን ማግነት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ፣ በዩኒቨርስ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ፍጡራን ጋርም ተመሳሳይ ሁኔታ ይገጥመናል፡፡ ከአጎራባች ፕላኔቶች ነዋሪዎች ጋር ያለው ግንኙነትም ይቋረጥና መሆራቸውንም ልንዘነጋ እንችላለን፡፡
ሆኖም ይህንን ሁሉ መቀየር አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ማድረግ ያለብን ወደ ቀድሞው እኛነታችን፣ አፍቃሪነታችን መመለስ ነው፣ ምክኒቱም እኛነታችን ያ ነዋ! እኛ ፍቅር ነን፡፡ እኛ ሩህሩህ ነን፡፡ እኛ የዩኒቨርስ ምርጦች ነን፡፡ ረስተን ነው እኮ፡፡