• ምእራፍ አራት. የቪጋን ፖሊሲና ህግ ማውጣት> የኤደንን ህልም እውን ማድረግ
      • III. የኤደንን ህልም እውን ማድረግ


        አሁን አለም መቶ በመቶ ቬጀታሪያን ቢሆን፣ መልካም ውጤቱ ከመላ-ጎደል በ60 ቀናት ውስጥ ይታይ ነበር፡፡ ስምንት ሳምንታት ማለት ነው፡፡ ወዲየውኑ በስምንት ሳምንታት ውስጥ ውጤቱን እና ነበር፡፡ ወዲያውኑ ታያለህ፣ ወዲያውኑ ነው የሚታየው፡፡ ሙሉውን ለማየት ግን፣ ትልቁን ስዕል፣ በስምንት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ያንን መገንዘብ ትችላለህ፣ አጭር ስምንት ሳምንታት፡፡

        በስምንት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ አደጋዎች ሁሉ ይጠፋሉ፡፡ ገነት እንደዚያ ነው የተፈጠረችው፡፡ ምንታስባለህ? ገነት ከየት ነው የመጣው? ገነት ማለት ሁሉም ፍትረታት በተመሳሳይ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱበት ቦታ ነው፡፡ ሁሉም በአንድ አይነት መንገድ ማለቴ አይደለም፣ በተመሳሳይ የሩህሩህነት ደረጃ ማለቴ ነው እንጂ፣ ተመሳሳይ የፍቅርና የመንፈሳዊ እውቀት፣ የግንዛቤ ደረጃ፣ ተመሳሳይ ክብርና ቅዱስና፡፡ ያ ነው ገነት፡፡

        ገነት ዝቅ ብላ ልትቀበለን ዝግጁ ናት እኛ ደረጃውን ጠብቀን ወደርሱዋ ከተራመድን/ከተጓዝን፡፡ እናም ሁሉም ይህንነ መረዳት ቢችልና የጨቅላውን ህጻን የደረጃ ጉዞውን ቢጀምር፣ በአንድ ጊዜ አንድ ደረጃ ብቻ፣ አንድ ፕላኔታችንነ እድል የሚወስን ጠቃሚ ደረጃ፣ ያ የቬጅታሪያን ደረጃ ነው፤ ሌላ ማንኛውም ነገር ሁሉ ሳንጠይቅ ወደኛ ይመጣልናል፡፡ መሃሪዎች ከሆን ምህረትን እናገኛለን፡፡ የዩኒቨርስ ህግ ቦታውን አይስትም፡፡

        አፍራሽ፣ ገዳይነት፣ መጥፎ ኢነርጂ ወደ መልካምነት፣ ደስታ፣ አዝናኝ፣ እንስሳትን ጨምሮ ለሁሉም የፕላኔቷ ፍጡራን ደግነት፣ የሰው ልጆች ቀዳሚ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ይለወጣል፡፡

        እናቸም ምን አይነት ምድር ውስጥ ነው ምንኖረው? እንደገና ኤደን፡፡ ድንገተኛ ሰላምና የሁላችን አንድ የመሆን ግንዛቤ፣ በሁሉም ብሄሮችና አገሮች መካከል፣ በሁሉም ሰዎች መካከልና በእንስሳትና ሰዎች መካከል! ግንዛቤው ወገግ ይልልናል፡፡ምንመ መግለጫ አያስፈልግም፡፡ ሰዎች ሁላችንም እኩል መሆናችንን በቅጽበት ይረዳሉ፡፡ እኛና የፕላኔቷ ነዋሪዎች ሁሉ እንስሳትም በተመሳሳይ ሁኔታ እኩል ናቸው፡፡ እናም ሰዎች ለዛፎችና ለእጽዋትም ጭምር ክብር ይኖራቸዋል፡፡

        የኑሮ ዘይቤያችንን ወደ ተሻለ ገነታዊ ደረጃ ብንለቅጥ የላይኛው ኢነተሌጀንስ ከውስጣችን ይገለጥና ያልገመትነው የፈጠራ ስራዎች ችሎታዎች መፍጠር እንችላለን፡፡ የሚበር መኪና ኖረናል፣ አሁን በሚሰራው ማለቴ ሳይሆን የተሻለና የተመቻቸ እንጂ፡፡ እንዲያውም እንደሌሎቹ ፕላኔቶች የበረራ ቀበቶ ሊኖረን ይችላል፡፡

        የሳይንስና ቱክኖሎጂ ግንዛቤያችንም ከምድራዊው ባሻገር የተራመደ ይሆናል፡፡ ምክኒያቱም ከፍ ያለ፣ ርህረሄ የተሞላ ከባቢ፣ ከነርሱም በመማር፣ እውቀቶቻችንን ለመለዋወጥ የበለጠ ከመጠቁት የፕላኔት ሰዎች ጋር መገናኘትም አንችላለን፡፡

        እያንዳንዱ አገር በቂ ሃብት ይኖረዋል፣ ከልቡም ከሌሎች ጋር ይለዋወጣል፣ ይረዳዳልም፡፡ በዚህ መንገድ ያለ ገንዘብ ማእከልነት እውን የሆኑ ስርኣቶች አሉ፣ ከፍ ካሉትና ካደጉት የዩኒቨርስ ማህበረሰቦች፣ ከሌሎች ፕላኔቶች ያየሁት መሰረት በማድረግ፡፡ ሰዎች ናቸው፣ የህይወት ጽንሰ-ሀሳባቸው፣ መጀመሪያ የማህበረሰቡ ጽንሰ-ሀሳብ መለወጥ ይኖርበታል፣ የህዝቡ ጽንሰ-ሀሳብ፡፡ አንዴ ወደ ማህበራዊነት ከተለወጡ፣ ወደ ጎረቤታማነት፣ የበለጠ አለማቀፋዊ ቤተሰብነት፣ ከተለወጡ ያ የመለዋወጥ/መቀየር ስርኣት በራሱ እውን ሆኖ ይከሰታል፡፡

        እያንዳነዱም እርስ በሱ ይፋቀራል፣ ይካፈላልም፡ ፍቅር፣ መዋደድና ሃበነትን፡፡ ከዚያም ደስተኛ ኑሮ ይኖረናል፣ በጣም ጥቂት የተቸገሩ፣ በጣም ጥቂት ቤት የሌላቸው ሰዎች፣ በጣም ትንሽ ብቻ ወይም ምንም የተራቡ፣ በጣም ትንሽ ወይም ምንም በበሽታ የተጠቁ ህጻናት ይኖሩናል፡፡ እንስሳትም ይጠበቃሉ/እንክብካቤ ያገኛሉ፡ ስጋ በሊታዎች ከእንግዲያ ወዲህ አይኖሩም፣ ቬጀታሪያን ወይም ቪጋን ብቻ፡፡

        ዘወትር በፈገግታ ሰላምታ ትለዋወጣለህ፣ በስራም የመወዳደር መንፈስ አይኖርም፣ ሁሉም በሌላወ ጣልቃ አይገባም፣ ፍቅርና ጓደኝነት ብቻ! የእናም ፕላኔቷ ከፈ ያለ ፕላኔ ንቃተ-ሂሊና ማለት የበለጠ የዚህ አይነት ኢነርጂ፣ ፍቅርና ደግነት ነው፡፡


        በአለም ዙሪያ ቪጋን መሆን ማለት ከመቀመቅ በመውጣት የሚያስተባብረን፣ እንነስሳትን ጨምሮ ለሰው ልጅ ሰላምና መረጋጋት የሚያመጣ የርሁርህት ምጥቀት ማለት ነው፡፡ ግዲያን በመተውና ለሁሉም ህይወት ክብር መስጠት የሚገኘው ውስጣዊ ሰላም በአለም ዙሪያ እንደ ማእበል ይሰራጭና ሰው ልጅን ልብ በማንሳት የመተሳሰብ/የመፈቃቀድ ኤደን በምድር ላይ ይፈጥርልናል፡፡ ያ ዘላቂ ወርቃማ ዘመን ያመጣልናል፡፡

         


         Previous      Next   

    • Home  |   Author   |   News  |   Columns  |   Reviews  |   Quotes  |   Resources  |   Download  |   Feedback  |   Read in HTML for slow internet connection
    • For the latest urgent messages, please visit www.SupremeMasterTV.com For other publications and Artworks by Supreme Master Ching Hai, www.LoveOceanCreative.com
    • © 2011 The Supreme Master Ching Hai All rights reserved. *